ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ፗግሜ 01,2005:ታሪክን የኋሊት

ፗግሜ 01, 2005

ታንክ አይነቱ በዝቶ፤ ቅልጥፍናው ጨምሮ፣ ዘምኖ ዘመኖ፣ አሁን ከደረሰበት ምጡቅ የቴክኖሎጂ ጫፍ ተጠግቷል፡፡ የዘመኑ ትላላቅ የምድር ውጊያዎች፣ በአመዛኙ ያለ ታንክ አይታሰቡም፡፡ታንክ፣ በውጊያ ላይ መዋል የጀመረው በ1ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ነበር፡፡ ውልደቱም በዚያው ጊዜ ነው፡፡ በብሪታንያ፡፡ሊትል ዊሊ ወይም ‹‹ትንሹ ዊሊ›› የተሠኘ ስም የተሰጠው የመጀመሪያው ታንክ ተመርቶ የወጣው የዛሬ 98 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ የታንክ አስፈላጊነት የተፀነሰው የጉድባና ሠበርባራ መሬት ውጊያዎችን ለመቋቋም ሲባል ነው፡፡

በዚህ የውጊያ መሳሪያ ግንባር ቀደም ኃሳብ አፍላቂነት የዛን ጊዜው የብሪታንያ የመከላከያ ኮሚቴ አባሎች የነበሩት ኮሎኔል ‰ርኒስት ስዊንቶንና ዊሊያም ሄንኬይ ይነሳሉ፡፡

የባሕር ኃይል ሚኒስትር የነበሩት ዊንስተን ቸርችልም በኃሳቡ ተስማሙ፡፡ - የትንሹ ዌሊ ስራ ተጀመረ፡፡
የብሪታንያ የመከላከያ ሹሞች፣ የትንሹ ዌሊ ስራ እንዲጀመር ትዕዛዝ ሲሰጡ፣ በስራው ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ሠራተኞች አንዳቸውም ምን እየሠሩ እንደሆነ እንዳያውቁ ሚስጥሩ ተሸሸጓጋቸው፡፡
ሚስጥሩ ከሠራተኞቹ ሳይቀር እንዲሸሸግ የተደረገው ጠላቶች ስለ መሳሪያው ምንነት እንዳያውቁ፤እንዳይደርሱበትም ነበር፡፡ ለሠራተኞቹ የተነገራቸው የሚሰሩት የጦር መሳሪያ ሳይሆን፣ በጦር ሜዳ ውሃ የሚያቀብል ተሸከርካሪ ስለመሆኑ ነው ይባላል፡፡
የመጀመሪያው ስሪት ታንክ፣ ትንሹ ዌሊ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ይመስል ስለ ነበር ታንክ ተባለ፡፡ የመሳሪያው የወል ስምም በዚሁ ፀና፡፡
14ቶን የሚመዝነው ትንሹ ዌሊ ፍጥነቱ የዔሊ አይነት ቀርፋፋ ሲሆን፤ ፍጥነቱም በሰዓት ከ3 ኪሎ ሜትር ያልበለጠ ነበር፡፡
ትንሹ ዊሊ፣ በፈር ቀዳጅነት ቢመረትም፣ በነበሩበት ፈርጀ ብዙ ጉድለቶቹ የተነሳ ውጊያ ላይ ሳይሰልፍ በዛው ጡረታ ወጣ፡፡

ታንክ ለውጊያ ተግባር የዋለው፣ በትንሹ ዌሊ መነሻነት የተሻሻለው ቢግ ዌሊ ወይም ‹‹ትልቁ ዌሊ›› ተመርቶ ከወጣ በኋላ ነው፡፡

ትልቁ ዊሊ፣ ለውጊያ ቢውልም፣ ጩኸቱ ሙቀቱና አሁንም አሁንም ጠግኑኝ የሚል እንከናም እንደነበረው የታሪክ ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡
ዘመን አፈራሾቹ ታንኮች ከቅልጥፍናቸው፣ ከቴክኖሎጂ ርቀታቸውና ፀረ ታንክ አጥቂ መሳሪያዎችን የመቋቋም ብቃታቸው፣ ከፍተኛ እየሆነ በመምጣቱ፣ ነባሮቹን ታንኮች ቢያስናቋቸውም በየጊዜያቸው የነበሩት ታንኮች በአቅማቸው ከፍ ያለ አገልግሎት ፈፅመዋል፡፡
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ