ማስታወቂያ

programs top mid size ad

ነሐሴ 07, 2005:ታሪክን የኋሊት

ነሐሴ 07, 2005

የበርሊን ግምብ  የዚያን ጊዜዎቹን ምስራቅና ምዕራብ በርሊን መለያ ብቻ ሳይሆን  የቀዝቃዛው ጦርነትም የርዕዮት ዓለማዊ ክፍፍል ተምሳሌት ሆኖ ይታሰባል፡፡ ግንቡ ከታጠረ ዛሬ ልክ 52ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡  በአውሮፓ 2ኛው የዓለም ጦርነት በጀርመን ሽንፈት እንደተደመደመ ሀገሪቱ በአሸናፊዎቹ የህብረቱ ኃይሎች መዳፍ ውስጥ ገባች፡፡ የጀርመንን ግዛት አሸናፊዎች ሶቪየት ህብረት አሜሪካ፣ ብሪታንያና ፈረንሳይ በየድርሻቸው ተቃረጡት፡፡

ከጦርነቱ ማብቃት ጥቂት አመታት በኋላ ምዕራባውያኑ በይዞታቸው ስር የቆየው ክልል ተደባልቆ ምዕራብ ጀርመን እንድትመሠረት ፈቀዱ፡፡ ጥቂት ቆይቶም በሶቪየቶች ይዞታ ስር የነበረው ግዛት ምስራቅ ጀርመን ተባለ፡፡ ርዕሠ ከተማዋ በርሊንም እንደ መላዋ ጀርመን በኃያላኑ የመከፋፈል እጣ ገጠማት  ምዕራቡ  በምዕራባዊያን ምስራቁ ደግሞ በሶቪየት የተፅዕኖ ክልልነት ተሸነሸነ፡፡ ከምስራቅ በርሊን ወደ ምዕራቡ የሚኮበልሉ ጀርመናዊያን ቁጥር ከእለት ወደ እለት፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ፡፡ የምስራቅ ጀርመኖቹን  ዜጎች ኩብለላ የዚያን ጊዜው የሶቪየት ህብረት መሪ ኒኪታን ኩርቼየቭ አልወደዱትም፡፡

እንዲህ አይነቱ ኩብለላ እንዲቆም በሳቸው ጥላ ስር ለነበረው የምስራቅ ጀርመን መንግስት ቀጭን ትዕዛዝ ሰጡ፡፡

የዛሬ 52 ዓመት በዛሬዋ እለት ተኝተው የነቁ ጀርመናዊያን በሁለቱ በርሊኖች ወሰን ላይ እንግዳ የሆነ ክስተት  ገጠማቸው፡፡

ከ160 ኪሎ ሜትር በላይ እሾሃማ የሽቦ -አጥር- ታጥሮ- አገኙ፡፡

ቀስ በቀስም ባለ ሽቦ አጥሩ በየተወሰነ ርቀት መትረየስ የተጠመደባቸውና መቺ ኃይል የተመደበላቸው ረጅም የቅኝት ማማዎች በተገጠገጡበት ኮንክሪት ግምብ ተተካ፡፡ በታሪክም የበርሊን ግምብ ተባለ፡፡

ግንቡን ለማቋረጥ ሙከራ ሲያደርጉ በተደገኑት መትረየሶች የተረሸኑት የምስራቅ ጀርመን ዜጐች ቁጥር ከ160 ቢበልጥ እንጂ አያንስም ይባላል፡፡


በዚህ ግንብ የተነሳ የአንድ ቤተሰብ አባላት አንዱ እዚህ ሌላው እዚሆነው ቀሩ፡፡
አባት ምስራቅ በርሊን፤ ልጅ በምዕራብ እንዳሉ ተለያዩ፡፡

ግምቡ አጐትን እዚህ፤ አክስትን እዛ አድርጐ እንደለያየ ብዙ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡
ጊዜው እየተቀየረ መጣ፡፡

በ1980ዎቹ አጋማሽ  የሶቪየት ህብረት መሪ ለመሆን የበቁት ሚካኤል ጐርቫቾቭ ‹‹ግላስኖስት›› ግልፅነት ‹‹ፔሬስትሮይካ›› መልሶ ግንባታ አሉ፡፡  ለለውጥ ተነሱ፡፡

ሶቪየት ህብረት በምስራቅ ጀርን ላይ አሳርፈው የቆየችውን ተፅእኖ አላሉ፡፡

የምስራቅ ጀርመን ሕዝብ ለነፃነቱ እምቢ ብሎ ተነሳ፡፡ ስርዓቱ ተንኮታኮተ፡፡

የምስራቅ ጀርመን መንግስት ተናደ፡፡ አበቃለት፡፡ የበርሊን ግምብ ፈረሰ፡፡ በምስራቅ በምዕራብ ተከፋፍለ የቆየችው ሀገር ተዋሐደች፡፡ -

ጀርመን ምስራቅ ምዕራብ መባሏ ቀርቶ አንድ ሆነች፡፡
ቁልፍ ቃላት
ምላሽ