• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

“ብታምኑም ባታምኑም ቀለበት ውስጥ ከተውናል”

“ንቀውናል፣ ደፍረውናል - ብታምኑም ባታምኑም በቁማችን ሞተናል” ተብሎ ነበር ያኔ፡፡ ዘንድሮም ደግሞ ‘ብታምኑም፣ ባታምኑም’ የሚባል ነገር አይመጣም አይባልም፡፡“ንቀውናል፣ ከበውናል፣ ብታምኑም ባታምኑም ቀለበት ውስጥ ከተውናል” የሚያስብል ነገር አይመጣም አይባልም፡፡ ታንኩ በቅርብ እየሰፈረ ነው፣ ከባድ መሳሪያው በቅርብ እየሰፈረ ነው፣ የጦር መርከብና ጀልባው ከማዶ እያጓሩ ነው፡፡ በአፍሪካ ቀንድ ጦር ሰፈሮች ለማቋቋም የሚደረገው ሽሚያ የሚመስል ጥድፊያ ጦፏል … አፍንጫችን ስር ማለት ነው፡፡

ያኔ ምድረ ቅኝ ገዥ “ከዚህ እስከዚህ የእኛ”፣ “ከዚህ እስከዚህ ደግሞ የእኛ” እያሉ አህጉሪቷን ይቀራመቷት በነበረበት ዘመን ‘ዘ ስከራምብል ፎር አፍሪካ’ የሚባል ነገር ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ‘ዘ ስክራምብል ፎር ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ’ የሚል ነገር እየተፈጠረ ይመስላል፡፡ቀደም ባሉት ዘመናት እኮ ጣጣ አልነበረውም…ወይ ሶቪየት ህብረት ነች፣ አለበለዚያም አሜሪካ ነች፡፡ አሁን ግን በተለምዶ ጦራቸውን ከድንበራቸው አስወጥተው የማያውቁና ‘ሀያላን’ የሚል ቅጽል ገና ያልተሰፋላቸው ሀገራት በአካባቢያችን ጦር ሰፈሮች እየመሰረቱ ነው … ዙሪያችንን ለመባል ምንም በማይቀረው ሁኔታ፡፡

በተለይ ነሀሴ ላይ ቻይና በጅቡቲ የጦር ሰፈር ስትመሰርት ታላላቆቹ የዓለም መገናኛ በዙሀን ሁሉ “ይሄ ነገር እንዴት ነው?” ማለት ጀመሩ፡፡ ቻይኖቹ ማብራሪያ ነበራቸው፡፡ “ይሄ የጦር ሰፈር ሳይሆን በአካባቢው ላለን የሰላም ማስከበርና ሰብአዊ ተግባሮቻችን የአቅርቦት ጣቢያ ነው፣” አሉ፡፡ ማንም “እንዳላችሁ” አላላቸውም፡፡ እንደውም ቻይና በአፍሪካ ቀንድ፣ በመላው አፍሪካም ላላት የመስፋፋት ፖሊሲዋ እንዲመቻት ያደረገችው ነው ተባለ፡፡

የቅርብ ማስረጃ ሲባል… የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የበቀደሙ ኮንግርስ ላይ ፕሬዝደንቱ “ቻይና ዓለም ላይ የመሪነት ሚና መጫወት አለባት፣” ያሉትን ይጠቅሳሉ፡፡ ሆኖም አሁን የቻይና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በተለይ የባህረ ሰላጤው ሀገራት በአፍሪካ ቀንድ መሰባሰብ ጥያቄዎችም፣ መላ ምቶችም እያስከተለ ነው፡፡የባህረ ሰላጤውን ፍጥጫ ወደ አፍሪካ ቀንድ እያስፋፉት ነው ተብሏል፡፡ እንዳጋጣሚ አካባቢው ያሉት ሀገራት በሁሉም መለኪያዎች ኋላ ቀር መሆናቸው በገንዝብ ለማማባልም አያስቸግሩም ነው የሚባለው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: “ብታምኑም ባታምኑም ቀለበት ውስጥ ከተውናል”

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“የገላጋይ ያለህ!”

ባለፈው ዘመን የሆነ ነው፡፡ በሁለት ጎረቤታም ሰፈሮች ልጆች መሀል ከፍተኛ ጠብ ነበር፡፡ ዝም ብሎ መቧቀስ ብቻ ሳይሆን በስለት እስከመጎዳዳት የደረሰ ጠብ…፡፡ ከመካረሩ የተነሳ አይደለም ወጣቶቹ፣ የአንዱ ሰፈር ሰው በሌላኛው ሰፈር ማለፍ የማይችልበት ደረጃ ይደረሳል … ልክ የሁለት አገሮች ጠብ ይመስል፡፡ “የገላጋይ ያለህ…” የሚያስብል ጠብ፡፡

ደግነቱ ጠቡ ከቁጥጥር ውጪ ከመሆኑ በፊት ገላጋይ አልጠፋም … የሁለቱ ሰፈር የሀገር ሽማግሌዎች ተሰባስበው ገሰጹ፣ መከሩ - “አንተም ተው፣ አንተም ተው” አሉ፡፡ የሁለቱ ሰፈር ወጣቶች በየአካባቢው ህዝብ ተከበው በአቅራቢያ በሚገኝ ድልድይ ላይ ተገናኙ፣ ተቃቀፉ፣ ተሳሳሙ፣ ታረቁ - የምዕራባውያኑን ምሳሌያዊ አነጋገር ለመዋስ ‘ቆንጨራቸውን ቀበሩ’

አለቀ…

ኧረ “የገላጋይ ያለህ…” ሲባል የአገር ሽማግሌዎችም “እኛ እያለን ሌላ ገላጋይ ከየት ሊመጣ ነው!” በሚል መንፈስ ህብረተሰቡ በባህልም፣ በታሪክም የሚጠብቅባቸውን ሚና ተወጡ፡፡

አሁንም “የገላጋይ ያለህ፣” እያልን ነው… “እኛ እያለን ሌላ ገላጋይ ከየት ሊመጣ ነው!” የሚል ውብ ዜማ መስማት እየናፈቀን ነው፡፡ የሀገር ሽማግሌዎቻችን የት ጠፉ ! ከሰማያዊ ቃል በታች ከቃላቸው ዝንፍ የማንለው ጎምቱዎቻችን የት ጠፉ ! ይህ ህብረተሰብ እኮ ለሀገር ሽማግሌዎች ታላቅ ክብር የነበረው ነው፡፡ የእነሱ ቃል “እናንተ ካላችሁ ይሁን !”

የሚባል ነበር፡፡ የሀገር ሸማግሌዎች “እኔ ምን አገባኝ” ብለው በካፖርትና በጋቢያቸው የሚጠቀለሉ ሳይሆኑ ከራሳቸው ምቾት ይልቅ ለህብረተሰብ ጥቅም የቆሙ ነበሩ፡፡ በታሪካችን በአገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብነት እኮ ብዙ ሰናይ ነገሮች ተከስተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: “የገላጋይ ያለህ!”

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

የኮንዶሚኒየም ነገር - “ተዋቸው፣ የኮንዶሚኒየም ልጆች ናቸው”

ልጆቹ የፕሬሚየር ሊግ ኳስ ለማየት አንድ ቤት ገብተዋል፡፡ ቀደም ብለው ገብተው የማያውቁበት ቤት ነው፡፡ የሚደግፉት ቡድን ድንገት ግብ ያስቆጥራል፡፡ ብድግ ብለው ይጮሃሉ፡፡ ይሄኔ ከቤቱ መደበኛ ደንበኞች አንዱ “እባካችሁ ድምጻችሁን ቀንሱ!” ይላል፡፡ እንደዛ አይነት አደጋገፍ እዛ ቤት ውስጥ የተለመደ አልነበረም፡፡ ሌላኛው ሰው ምን ይለዋል፣ “ተዋቸው፣ የኮንዶሚኒየም ልጆች ናቸው…”

የኮንዲሚኒየም ልጆች ?

መቼም ከመሬት ተነስቶ ሰው ላይ በቅጽል ልጠፋ የኤክስፐርት ችግር የለብንም፡፡ ‘የኮንዶሚኒየም ልጆች’ ግን ዝም ብሎ ቅጽል አይደለም፡፡ እንደዛ የተባለው ኮንዶሚኒየም ፎቆች ላይ የሚኖሩ ትናንሽ ልጆች እንደልባቸው መቦረቅ ስለማይመቻቻው … ብዙ ጊዜም ቤት ተቆልፎባቸው ነው የሚያድጉት የሚባል ነገር አለ፡፡

“ተዋቸው፣ የኮንዶሚየም ልጆች ናቸው”… ትንሽ ማጋነን ያለበት ቢመስልም አንድ እውነት ግን አለው፡፡ ልጆች መንደሮች ውስጥ እንደፈለጉት እንደሚሯሯጡት የኮንዶሚኒየም ኑሮ ይህንን ነጻነት አይሰጣቸውም፡፡ ከዓመታት በፊት ከኮንዶሚኒየም ፎቅ ላይ ሰለወደቁ ልጆች ዜና ሰምተናል፡፡

ለነገሩ የኮንዲሚኒየም ወይም የጋራ ቤቶች ኑሮ ይህን ያህል የሚመች ነው እንዴ! እንደስሙ እውነት ተሳስበን በጋራ እየኖረን ነው እንዴ… ለነገሩስ ለጋራ ኑሮ የሚያመቹ ነገሮች ሁሉ የተሟሉ ናቸው እንዴ ! ትናንሾቹ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ ሌላውስ በራሱ ላይ ቆልፎ አይደል እንዴ የሚኖረው!

“እዚህ ቤቶች፣ ሰው የለም እንዴ!”
“ኧረ አለን፣ እንደምን አደሩ እትዬ ቦጌ?”
“እግዚአብሔር ይመስገን፣ ነይ ቡና ፈልቷል፡፡”
“እሺ፣ መጣሁ፡፡”
“እግረ መንገድሽን ብርቄንም ነይ በያት፡፡”

ተጨማሪ ያንብቡ: የኮንዶሚኒየም ነገር - “ተዋቸው፣ የኮንዶሚኒየም ልጆች ናቸው”

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ባለዲግሪው የጎዳና ተዳዳሪ…

“ተምሮ ተምሮ ኑሮ እንደነጆሮ 

የማታ መኝታ እንደነኮሽታ…”

ምህረቱ ዘውዱ መሐመድ ትውልድ እና እድገቱ ሻኪሶ ነው፡፡ የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ አንደኛ ነበር የሚወጣው፡፡ በማትሪክ ውጤቱም ከ9 ትምህርት 7 A እና 2 B አምጥቷል፡፡ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በHuman Nutrition 3.31 አምጥቶ ነው የተመረቀው፡፡

የኋላ የኋላ ግን ለጎዳና ሕይወት ተዳረገ፡፡ የዚህ ሰበቡ ደግሞ ፍቅር ነው ነው የሚለው፡፡ በሚወዳት ልጅ እና ልጃችንን ነጠቅሽን ባሉት ቤተሰቦቹ መሃል አጣብቂኝ የገባው ምህረቱ የቤተሰቡ ማማረር ሲበዛባት ፍቅረኛው ጥላው ስትሄድ ጎዳና ወጣ…

ተጨማሪ ያንብቡ: ባለዲግሪው የጎዳና ተዳዳሪ…

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

አባባ ያሲን ሶማ ሐሚድ ሾፌር ናቸው...እናም ደግሞ በሚነዷት ሚኒ ባስ ውስጥ...

አባባ ያሲን ሶማ ሐሚድ ሾፌር ናቸው፡፡ እናም ደግሞ በሚነዷት ሚኒ ባስ ውስጥ ሕግና ደንብ አውጥተዋል፡፡ደንቡን ለሚተላለፈው ደግሞ ቢጫ እና ቀይ ካርድ አዘጋጅተዋል፡፡ ምን ይሄ ብቻ ፊሽካም አላቸው ይለናል የሸገሩ ወንድሙ ኃይሉ፡፡

ረጋ ብለው የሚያሽከረክሩት አባባ ያሲን ሶማ ሐሚድ ቶሎ በሉ ብሎ የሚያስቸኩላቸው ተሳፋሪ ከመጣ ከቢጫ የፕላስቲክ ባልዲ ቁርጭ የሰሯትን ቢጫ ካርድ ያሳዩታል፡፡ፊሽካም የሚይዙት አባባ ያሲን ሕግ የማያከብር አሸከርካሪ ካዩ ፊሽካውን ነፍተው አደብ ያስይዙታል፡፡

አባባ ያስን ታክሲ ላይ ቆዳ እና ዶሮ ይዞ መሳፈር እንዲሁም ስድብ፣ ሐሜት፣ ውሸት እና መበሰጫጨት ክልክል ነው፡፡ ገንዘቤ ነው ብሎ ነገር የለም የሚሉት አባባ ያሲን እኒህን ነገሮች ሲያደርግ ያገኙት ላይ ቢጫ ካርዳቸውን ይመዛሉ፡፡ አሁንም ካልታረመ ቀዩ ይደገማል፡፡ይህም አላስታግሰው ያለ ካለ ደግሞ አባባ ያሲን ከታክሲውም ሊያስወርዱት ይችላሉ ይለናል ወንድሙ ኃይሉ

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers