• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

እማማ ፊሽካ

እማማ ፊሽካን እናስተዋውቃችሁ፣

በእማማ ፊሽካ ምግብ ቤት ውስጥ እጅ ሳይታጠቡ ምግብ ልብላ ካሉ፣ ሳይመጥኑ ከጎረሱ … ፊሽካ ይነፋቦታል… - መባረርም አለ !

“ሳይታጠቡ ከጤና ጠንቅ፣
በትልቁ ጎርሰው ከመታነቅ” … ፊሽካዬን እነፋለሁ… የሚሉት እማማ ፊሽካ አዲስ አበባ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ አንዲት አነስተኛ ምግብ ቤት አለቻቸው፡፡ እድሜዬ 70 ዓመት ነው የ7 ቤተሰብም አስተዳዳሪ ነኝ የሚሉት እማማ ፊሽካ ታዲያ በምግብ ቤታቸው ውስጥ ጥብቅ ደምብ አውጥተዋል - ሳይታጠቡ ዘሎ ምግብ ላይ ጉብ ማለት፣ ሳይመጥኑ መጉረስ ክልክል ነው፡፡

እንዲህ ካደረጉ እማማ ፊሽካ የማስጠንቀቂያ ፊሽካ ይነፋሉ፡፡ ተመጋቢው ደምቡን አክብሮ እጁን ታጥቦ ካልበላ ወይም በልኩ ካልጎረሰ ከቢጫም ቀይ ካርድ ድረስ ተሰጥቶት ሊባረር ይችላል ይላሉ እማማ ፊሽካ…

ታክሲ አሸከርካሪዎች እንዲሁም በቀን ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ወደሚያዘወትሯት ወደዚህች ምግብ ቤት ጎራ ያለው የሸገሩ ወንድሙ ኃይሉ ስለ ምግብ ቤቷ ይነግረናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: እማማ ፊሽካ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

በዘንድሮ ጥምቀት ደስታን አየንበት

በዘንድሮ ጥምቀት ደስታን አየንበት…

ጥር 5 ቀን 2009 ዓ.ም በአርብ ምሽት የሸገር ልዩ ወሬ መሰናዷችን ላይ ወንድሙ ኃይሉ ታሪኳን ያስደመጠን ዘውዳየሁ ጌታሰው አሁን በተመረቀችበት ሙያ ስራ ማግኘቷን ያበስረናል፡፡

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፅሁፍ በዲግሪ ተመርቃ በአካል ጉዳቷ ሳቢያ በተመረቀችበት ሙያ ስራ ማግኘት ስላልቻለች እዚያው በስድስት ኪሎ ካምፓስ በር ላይ ሲጋራና ማስቲካ ለመሸጥ የተገደደችው ዘውዳየሁ እንዲህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ችግሯ መልስ ያገኛል ብላ አስባ እንዳልነበር ትናገራለች፡፡

በጥር 12 ቀን 2009 የአርብ ልዩ ወሬ ፕሮግራማችን ወንድሙ ኃይሉ ዘውዳለም በተመረቀችበት ሙያ የ2000 ብር ደሞዝ የሚከፈላት ስራ ማግኘቷን ይነግረናል፡፡ የሥራ እድሉን የሰጣት የፊልምና የማስታወቂያ ሰራተኛው ተስፋዬ ማሞ፣ “በሬድዮ ፕሮግራማችን ላይ ስለ በጎነትና ስለመስጠት ተናግራናል፣ ሁላችንም እዚህ እንድንደርስም የበርካቶች እርዳታ ደግፎናል … ስለዚህም እኛም በበኩላችን የምንችለውን ማድረግ አለብን … የመስጠትና የበጎነት አካል መሆን አለብን” ይላል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

የማስታወቂያ ነገር

ተጋንነው ስለሚነገሩ፣ በአሻሚና ግልፅነት በሚጎድላቸው ቃላት እንዲሁም የሚነገርበትን ቋንቋው ሕግ ሳይከተሉ ስለሚሰሩ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች ጉዳይ ባለሞያ አነጋግሮ ዘገባውን ያቀረበው የሸገሩ ተህቦ ንጉሴ ይህ ነገር ሊስተካከል ይገባዋል ይለናል…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ቁጥሮቻችንን ምን ያህል ያውቋቸዋል?

የራሳቸው ፊደላትና ቁጥሮች ካሏቸው ጥቂት የዓለማችን ሐገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች፡፡ ቢሆንም ግን በተለይም ቁጥሮቻችን ከመዘንጋትም አልፈው ወደ መረሳቱ እየተንሸራተቱ እንደሆነ ይታያል፡፡ጉዳዩን አስመልክቶ የሸገሩ ተህቦ ንጉሴ ያጠናቀረው ዘገባ ይህን ክስተት በትኩረት ተመልክቷል፡፡ ቁጥሩን ያውቁ ይሆን በሚል ከጠየቃቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አብዛኞቹ ቁጥሩን እምብዛም አይለዩትም አያውቁትምም፡፡ተህቦ የዚህ አንድምታው ምንድነው ተጠያቂውስ ማነው በሚል የሥነ ልሳኑን ፕሮፌሰር ባዬ ይማምንም አነጋግሯል፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ሸገር ልዩ ወሬ፣የቄጠማ ሰልባጅ ነገር

የቄጠማ ሰልባጅ ነገር…

“አቅም ላጣ ለቸገረው - የቄጠማም ሰልባጅ አለው”

ስለልብስ ሰልባጅ አይደለም የማወራው ይለናል የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ፡፡ ወንድሙ ባሳለፍነው ሳምንት ወደ ጨርቆስ ጎራ ብሎ ከተጎዘጎዘ በኋላ ደርቆ የተጣለ ቄጠማን ከቁሻሻ ውስጥ ሰብስበው፣ ወንዝ ውስጥ አጥበው ለገበያ የሚያቀርቡ ሚስኪኖችን አነጋግሮ ነበር፡፡

“5 ብር የሚሸጠው ትኩስ ቄጠማ፣ ተጎዝጉዞ ከተጣለ በኋላ ታጥቦ ዳግም በስልባጅነት አንድም ሁለትም ሶስት ብርም ይሸጣል” ይሉናል በዚህ የሚተዳደሩቱ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers