• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ

ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ የቆየ አና የተለመደ የአማርኛ ምሳሌያዊ አነጋገር ነው፡፡ ልጅ ለጉርምስና እድሜ ደርሶ ያልተለመደ ባህሪ ሲያወጣ፤ቤተሰቡ ያልጠበቀውን ችግር ሲያመጣ፤ ፀብ ሆነ ፍቅር ከጎረቤት ሲጎትት ይህም ላሳደጉት ወላጆቹ እንግዳ ሲሆን፤ የልጆች እድገት ቤተሰቡን ሠላም እና የተረጋጋ ህይወት ሲያናጋ ‹ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ› ማለት እንደሚቻል የተለያዩ ሰዎች የተለያየ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል የአማርኛ ምሳሌያዊ አነጋገር እና ፍቺዎቻቸው የሚለው የብርሀኑ ገብረፃዲቅ መፅሀፍ (ገፅ 44) ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ የሚለውን ምሳሌያዊ አነጋገር ‹ልጅ ዕድሜው ከፍ ካለ የቤተሰቡን ሀብት ያድፋፋል ግድ የለውም› ሲል ይፈታዋል፡፡

ልጅ ሲያድግ ቤተሰቦቹ ያልለመዱትን እና ያልጠበቁትን አመል ካወጣ ወይም የቤተሰቡን ሀብት ካድፋፋ ወላጆቹ ምን እያስተማሩት ነበር ያሳደጉት? በተለምዶ ደግሞ ልጆች ለቤተሰባቸው ሳይሆን ለጎረቤቶቻቸው ወይም ለአካባቢያቸው እንግዳ የሆነ ባህሪ ሲያመጡ ችግሩ የአስተዳደግ መሆኑ ላይ ይሰመርበታል፡፡ ስለዚህ ወላጅ ልጆቹ ‹አሳዳጊ የበደላቸው›፣‹ተንጋደው ያደጉ› ተብለው እንዳይሰደቡባቸው፣ ከእነርሱ የተሻለ የተሳካላቸው ዜጎች እንዲሆኑላቸው በተግባርም ቢሆን በምኞት የተቻላቸውን ያደርጋሉ፡፡ ልጆቻቸውን የተሻለ ወደሚሉት ትምህርት ቤት ይልካሉ፤ ጥሩ ያለብሳሉ፤ጥሩ ያበላሉ፤ ያዝናናሉ፤እነርሱ ያላዩትን ለልጆቻቸው ለማሳየት ገንዘባቸውንም ሳይሰስቱ ይመድባሉ፡፡ ብቻ ቀላል የሚባል ኢንቨስትመንት አልሆነም ልጅ ማሳደግ፡፡ ቀላል ባለመሆኑም ይመስላል Rreakonomics የተባለው የSteven D.Levitt & Stephen J.Dubner መፅሀፍ ሲል የሚጠይቀው፡፡ ከልጅ አሰተዳደግ የበለጠ ወደ ሳይንስነት ያደገ ምን ጥበብ አለ? እንደማለት፡፡በልጅ አስተዳደግ ላይ ምርምሮች ይደረጋሉ፤መፅሀፎች ይታተማሉ፣የስነልቦና ባለሞያዎች ይተነትናሉ፡፡እስካሁን ግን ባለሞያዎቹን አስማምቶ የልጅ አስተዳደግን ሳይንስ ያደረገ ጥበብ አልተደረሰበትም፡፡ ጥበብ እንደቤቱ ሳይለያይ አይቀርም፡፡

አንዳንድ ባለሞያዎች የልጆችን ማንነት ሀምሳ በመቶ(50%) የሚወስነው ተፈጥሮ እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡ በእኛም ሀገር ‹ፈጣሪ የባረከው ልጅ› የሚል ከእምነት ጋር የተያያዘ አባባል አለ፡፡ ልጅ ከወላጅ/ካሳዳጊዎቹ ከሚማረው ይልቅ እኩዮቹ፣ከሚውልበት ቦታ አካባቢ እና ትምህርት ቤት የሚማረው ማንነቱን ለማነፅ ሰፊ ድርሻ አለው ብለው የሚከራከሩም አልጠፉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለልጆች የተቃና ማንነት፣የተሻለ የትምህርት ውጤት፣ ስነምግባር፣የፈጠራ ችሎታ፣ ሌላው ቀርቶ አድገው ስለሚኖራቸው የደሞዝ መጠን ወሳኙ ወላጆች በልጆቻቸው ላይ የሚያፈሱት ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ትኩረት፣ቅጣት፣ጭቅጭቅ፣ ድርድር እንደሆነ የሚከራከሩ አሉ፡፡ እርስዎ የትኛው ወገን ትክክል ነው ይላሉ? ወላጆች በልጆቻቸው ማንነት ላይ ምን ያህል እጃቸው አለበት? ‹ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ› በሚለው ሀሳብ ላይ መነጋገር ይቻላል፡፡ ልጅ ደርሶ ቤት መፍረሱ በምን ያስታውቃል? በጉዳዩ ላይ ለማውራት ማነቃቂያ ታሪክ ይፈልጋሉ? እንግዳውስ ዛሬ (ታህሳስ ፲፩) በቅዳሜ ጨዋታ ፕሮግራም ላይ መተላለፍ የሚጀምረውን ‹ወፌ ቆመች› በእውነተኛ ሁነቶች ላይ መሠረት ያደረገ የሬዲዮ ድራማ ያዳምጡ፡፡ ድራማውን ደግመው ማድመጥ ከፈለጉ www.shegerfm.com ላይ ያገኙታል፡፡


ስም - አቶ አማረ
የቤተሰብ ሁኔታ - ባለትዳር እና የ፫ ልጆች አባት
ሚስት - ለጊዜው በአካል የለችም
ስራ - ለጊዜው ተባሯል
መኖሪያ ቤት - በቅርቡ ለልማት በመነሳት ባለ ሞጃ ሰፈር(ምናባዊ ሰፈር)
ስለልጆቹ የሚያውቀው - ስማቸውን
አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

እስቲ ወደራሳችን እንመልከት

ሰውዬው በተወለደበት ሀገር ኑሮውን ይገፋል አሉ፡፡ ይህ ሰው ፂሙን ማሳደግ የሚወድ አይነት ነው፡፡ እናም ይህ ዠርጋጋ ሪዙ መለያው ሆኖ፣ እሱም ወዶት ይኖራል፡፡ ይህ ሰው ምግብ ሲመገብ የተወሰነው ሪዙ ላይ ይንጠባጠባል ግን በፍፁም አፅድቶት አያውቅም፡፡ ከጊዜ ጊዜ ይህ ነገር ሲደጋገም ሪዙ ላይ የሚንጠባጠበው ምግብ ተበላሽቶ መጥፎ ጠረን ያመጣበት ጀመር፡፡ ይህ ሰው ምንድን ነው የሚሸተኝ እያለ ዙሪያውን ማሰስ ጀመረ፡፡ ከዛ ችግሩ ከከተማው ነው በማለት ወደ ሌላ ከተማ ተጓዘ፡፡ እዛም ቢደርስ ሽታው አልጠፋ ይለዋል፡፡ በመጨረሻም ከአንድ መደምደሚያ ላይ ደረሰ አለ፡፡ መደምደሚያውም ‹‹ዓለም ሸታለች ማለት ነው›› የሚል ሆነ፡፡ ግን እንደዚህ ሪዛም ሰው ወደራሳችን ማየት ተስኖን ወደ ውስጣችን መመልክት አቅቶን ትክክል ያልሆነ መደምደሚያን የምንሠጥባቸው አጋጣሚዎች በጣም እየበዙ እኮ ነው፡፡ በተመሳሳይ ቋንቋ መግባባት እኮ እየተሳነን ነው፡፡ ሁላችንም እናወራለን መሰማማት መግባባት የለምና፡፡ መጫጫህ ብቻ ወደራሳችን ማየት አንፈልግም፡፡ ከቤት እስከ ስራ ቦታ በሌላውም ኑሮአችን ችግራችንን ወደሌላው ማላከክ እንጂ ወደ ውስጣችን ማየት ችግሩ ከኔ ይሆን እንዴ ብሎ መጠየቅ የለም፡፡ ጓደኛሞች በአንድ ጉዳይ ላይ ሀሳብ ያነሳሉ ከዛ እንዲህ ብታደርግስ ይለዋል አንደኛው በዛ መሠረት ያደርጋል ግን ውጤቱ በተቃራኒው የማይሆን ሊሆን ይችላል በዚህ ጊዜ አንተ ባልከኝ መሠረት እንዲህ አድርጌ ውጤቱ እንዲህ ሆነ ብትሉ ያ ጓደኛችሁ አይቀበላችሁም፡፡ ምን አልባት እኔ ባልኩት መሠረት ላይሆን ይችላል ያደረጋችሁት አሊያም እኔ መች እንዲህ አልኩኝ ብሎ እርፍ ይለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: እስቲ ወደራሳችን እንመልከት

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ስለ ባንዲራዋ

በአንድ ወቅት ወደ አንዱ የሀገራችን የገጠር አካባቢ ለስራ ጉዳይ በሄድኩኝ ጊዜ ከዋናው መንገድ ዳር በማስታወቂያ ቦርድ ላይ ተፅፎ ያየሁት ነው፡፡ ፅሁፍ ምን ማለት ነው የሚል ስሜትን ፈጥሮብኛል፡፡ መልዕክቱ ‹‹እንኳን አደረሳችሁ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የወጣንበት ክብረ በዓል›› ብሎ ከጐኑ ቀን ከነ ወርና ዓመቱ ተፅፏል፡፡

የአካባቢውን ሰዎች ስለዚህ መልክት ጠየኩኝ ሰዎቹም በኩራትና በራስ መተማመን በፊት እዚህ አካባቢ መፀዳጃ ቤት ብሎ ነገር የለም፡፡ መንገድ ላይ ነበር የምንፀዳዳው አሁን ሁሉም ነገር ተለውጦ እኛም በመፀዳጃ ቤት ብቻ መጠቀም ጀምረናል፡፡ አታያየትም ባንዲራዋን አሉኝ፡፡ ወደተሠቀለው ነጭ አነስተኛ ባንዲራ እየጠቆሙኝ፡፡

በዚህ ቦታ ስለ አካባቢ ፅዳት ለማስተማር የሄዱ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች በየመንገዱ መፀዳዳት ስላለው ችግር ካስተማሩ በኋላ ነዋሪው በየቤቱ መፀዳጃ ቤት እንዲቆፍር እስካሁን የጠፋውንም እንዲያፀዳ ምክር ሰጡት ህዝቡም በሀሳቡ ተስማምቶ ይህንን ማድረግ ጀመረ፡፡ በየአካባቢው የታሠበው መሠራቱ ሲረጋገጥ ነጭ ባንዲራ ይሠቀላል፣ ይህም ማለት መንገድ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ወጥተናል ማለት ነው፡፡ በጐዳናው ላይ የተሠቀለው ማስታወቂያም አካባቢው ሙሉ በሙሉ ነፃ መሆኑን ማረጋገጫ ነው፡፡ እውነት ነው አካባቢውን ላየው ማስታወቂያው ይገባዋል ያስብሏል፡፡ እነዚህን ሰዎች በዛች የገጠር ከተማ ይህንን ማድረጋችሁ ምን ጥቅም አለው ብላችሁ ስትጠይቁአቸው በጤናው በኩል ያለውን ፋይዳ ነግረዋችሁ ሲያበቁ የኛንም አካባቢ እንደ አዲስ አበባ ለማሳመር ነው ይሉአቸዋል፡፡ ይህንን እየሠማው አዲስ አበባን በምናቤ ሳልኩአት በየቦታው የሚፀዳዱባት አፊንጫን የሚበጥስ ሽታ ያላት እንጂ እነሱ የሚሉአትን አዲስ አበባን ማሰብ ተሳነኝ፡፡ እነሱ የሚያውቋት አዲስ አበባ ያቺ በቴሌቪዝን ላይ ያለቸው ነችና አይፈረድባቸውም፡፡ አሁን አሁንማ የአዲስ አበባ የፅዳት ነገር እኮ ጭራሽ እየባሠበት መንገድ ዳር መፀዳዳትም ነውር መሆኑ እየቀረ የመጣ ይመስላል፡፡ በአንድ ወቅት ስለዚሁ በአዲስ አበባ ስለሚታየው በየመንገዱ የመፀዳዳት ችግር ሀሳብ ተነስቶ ከጓደኞቼ ጋር ሳወራ አንደኛው ወገን ህዝቡ እሺ የት ይፀዳዳ የህዝብ መፀዳጃ ቤት በየቦታው የለ የሚል ሀሳብን አነሳ፡፡ ይህ ሀሳብ ሁሌም የሚባል የሚያሳምን ጐን ያለው ቢሆንም ከሁለተኛው ወገን የተነሳው ሌላኛው ሀሳብ ግን የበለጠ አሸንፎኛል፡፡ ትልቁ የኛው የአስተሳሰብ ችግር ነው፡፡

የሰው ልጅ በባህሪው የተለየ ነገር ካልገጠመው በቀር በፕሮግራም መመራት የሚችል ነው፡፡ ጠዋት ከቤታችን ስንወጣ ታጥበን ቁርስ ከአፋችን አድርገን እንደምንወጣው ለመፀዳዳት ቦታ አንሠጥም የትም ይምጣ የትም አስወግደዋለው ብለን ስለምናስብ ለመፀዳዳት የተገደበ ጊዜና ቦታ የለንም ትልቁ ችግራችን ያነው የሚል ነበር ሌላኛው ሀሳብ፡፡ እነዚህ ሀሳቦች እንዳሉ ቢሆኑም ግን ስለ አዲስ አበባ የፅዳት ነገር ስናስብ ብዙ ግራ የሚያጋቡ እንደ ስልጣኔ መለኪያ ተደርገው የሚወሠዱ ግን አሳፋሪ የሆኑ ተግባሮች ይታያሉ፡፡ አሁን አሽከርካሪዎች የትም ቦታ ይሁኑ ጐማቸው ላይ ውሃ ሽንት ይሽኑ ተብሎ የተደነገገ እኮ ነው የሚመስለው፡፡ በቅርቡ መሀል ፒያሳ አያሌው ሙዚቃ ቤት ከተደረደሩ ታክሲዎች የአንደኛው ሹፌር ተሳፋሪን እየጫነ እሱ ግን በበሩ ተከልሎ ጐማው ላይ ውሃ ሽንት ይሸናል፡፡ ይህ መሀል ፒያሳ ላይ ያየውት ነው፡፡ የዚህ ወጣት ሽንት ጐማውን አርሶ በመንገዱ ምፅዋት የሚጠይቁ አዛውንት የዘረጉአት ጨርቅን አቋርጦ ጉዞውን አቅም አጥቶ ፀሀይ ባደረቀው አስፋልት ተመጦ እስኪቆም ቀጠለ፡፡ ሹፌሩም ይቅርታ አላለም፤ ምፅዋት ጠያቄው አዛውንትም ለምን ብለው አልጠየቁም፡፡ እኔም ሆንኩ ሌላው መንገደኛም ምን አይነቱ ነው ከማለት ወጪ ለምን ብለን አልጠየቀንም መልሱ ምን አገባህ መሆኑ ስለሚታወቅ እናም በየጐዳው ሹፌሮቻችን ከመንጃ ፈቃድ ስልጠናው ጋር አብረው የሰለጠኑት ይመስል መኪናቸውን እያቆሙ ጐማቸው ላይ ይሸናሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: ስለ ባንዲራዋ

አስተያየት ይፃፉ (4 Comments)

ኧረ በናታችሁ እንደማመጥ!!!

ብንድማመጥ ልንግባባ እንችላለን፤ ከተግባባን ደግሞ ሁሉም ጥሩ ይሆናል፡፡ ግን የምንደማመጥ ይመስላችኋልን? አብዛኛዎቻችን፣ ሌላው የሚናገረውን ከማደመጥ ይልቅ፣ የሚያሰበውን እናውቃለን ባዮች ለመሆን በመፈለጋችን ማዳመጥ ትተናል፡፡ የምናገረውን ስማ እንጂ የምትናገረውን ልስማህ ማለት አቅቶናል፡፡ ጠርጣሪ ስሜታችን አሸንፎናል፡፡ ስለዚህ የምንሰማውን ከማመን ይልቅ የተናገረውን ማንነት፣ ‹‹ልቡንና ኩላሊቱን›› ለመመርመር እንባጃለን፡፡ ስለዚህ የማዳመጥ ሃይላችንን፣የመረዳት አቅማችንን፣ ራሳችን አንቀን እየገደልነው ይመሰለኛል! ግን ለምን አንደማመጥም?

በተለይ የፖለቲካ እሳት በጋመበት ቦታ፣ ጓደኛሞች ጭምር ተረጋግቶ መደማመጥ ካቆምንም 40 እና 50 አመት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ‹‹ይቺ ሃሳብ ከየት እንደምትመጣ እናውቃለን!›› ‹‹ምን ማለት እንደፈለግህ ገብቶናል፤›› ‹‹ይኸ ሃሳብ ከአንተ በመምጣቱ አዝናለሁ …የሚሉ ውሳጣቸው የጥፋት እሳት የያዙ መልሶች መስማት የተለመደ ሆኗል፡፡
በተለይ፣ መስበርና መቀንጠስ የሚያስችል ሹመት ከተሰጠው ሰው፣ እንዲህ ያለ ግብረ መልስ ሲመጣ የበትሩ ሰምበር እንደሚያሰፈራራ ትረዱታላችሁ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ወትሮም ለማደመጥ የሚፈልጉ ስላልሆኑ ብትከራኩሩቸው መታነቂያችሁን ያዘጋጁላችኋል፡፡ ‹‹እሺ›› ብትሉ አያምናችሁም፡፡ ‹‹በልብህ የምታስበውን የማላውቅ ይመስለሃል?›› እያሉ ይደነፉባችኋል፡፡
ልብ መርማሪ ነን ስለሚሉ፣ ብትናገሩም አይሰማችሁም እሺ ብትሉ አያምናችሁም፡፡ ታዲያ የሌላውን ሃሳብ መረዳት ሳይሆን ማዳመጥ እንኳ እየቆጠቆጠን እንዴት ያለ ማህብረሰብ እንደምንገነባ መገመት ይቻላል?

ተጨማሪ ያንብቡ: ኧረ በናታችሁ እንደማመጥ!!!

አስተያየት ይፃፉ (3 Comments)

ታክሲ መቃቃሪያም መፋቀሪያም

ከክፋት እስከ ቅንነት በታክሲዎች ውስጥ የሁለቱም ጥግ ይታያል፡፡ የፊቱን እና አንደኛውን የጋቢና ወንበር አጥፎ ከኋላ ተጠጋግታችሁ ተቀመጡ ከሚለው ሹፌር ሙዚቃ ከፍቶ እባክህ ስልክ ላውራ አንዴ ትቀንሰው ስትሉት ይህ ታክሲ እንጂ ቴሌ ንተር አይደለም እስከሚለው እና የጐማው መተኛት የነዳጁ ማለቅ ሰው ሲጭን እስከሚታየው ሹፌር ሁሉም የታክሲ ውስጥ ትዕይንት ነው፡፡ በረዳቶች በኩልም መልስ ሲሉት ከሚቆጣው ድፍን ብር ነው የያዝኩት ትዘረዝረው ሲባል መፍትሔን መፈለግን ቶ ደግሞ ሊነጅሰኝ ገባ ብሎ ለፀብ እስኪሚጋበዘው አልፎም ትርፍ ለመጫን ካልተጠጋህ ወርደህ በሌላ ሂድ ብሎ እስከሚደነፋው ሁሉንም ይህቺው ሰሚያዊ እና ነጭ የተቀባች ታክሲ ይዛለች፡፡ በተሳፋሪው በኩልም ሌላ ቦታ የገጠመውን ችግር በረዳትና ሹፌር ላይ በመጮህ ለመወጣት የገባ ከሚመስለው ለሆነውም ላልሆነውም ታሪፍህን አሳየኝ እያለ ነገር እስከሚያከብደው እንዲሁም ሁሉም ረዳትና ታክሲ ሹፌር ያው ነው ‹‹ፀብና ገቢ አታሳጣኝ›› ብሎ ፀልዮ ነው ጠዋት ከቤቱ የሚወጣው ብሎ ማመን ቀና ለሚያናግረውም ቀና የማይመልሠው ሁሉንም በዚህች ታክሲ ውስጥ ታገኛላችሁ፡፡
ለማንኛውም ችግር ላለብን ቀናነትን እና ታጋሽ ልቦናን ይስጠን ብለን ወደ ሌላኛው ጉዳያችን እንለፍ፡፡
ልክ እንደክፋቱ እና አለመግባበቱ ሁሉ የፍቅር የመተዛዘን ጥግም እኮ እንደኔ እዚህቺው ታክሲ ውስጥ ነው የሚገኘው፡፡
ለምን ይህ መተዛዘኑ ታክሲ ውስጥ ብቻ የሚለው ደግሞ ይገርመኛል፡፡
ለሀሳቤ ማጠናከሪያ እንዲሆነኝ አንድ ሁለት እያልኩኝ ምሳሌ ላንሳ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: ታክሲ መቃቃሪያም መፋቀሪያም

አስተያየት ይፃፉ (3 Comments)
Leza Vote Banner
Sheger 102.1 AudioNow Numbers