• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

ሸገር ልዩ ወሬ፣ዶሮ ማነቂያ

“ከዶሮ ማነቂያ ልድረስና አሁን፣
ተመግቤያት ልምጣ አስናቀች ወርቁን…”

ሸገር ልዩ ወሬ፣

የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ባሳለፍነው ሳምንት ለየት ያለ ወሬ ፍለጋ ወደ ዶሮ ማነቂያ ጎራ ብሎ ነበር፡፡
ዶሮ ማነቂያ ምን አገኘ ?

ከጠዋት እስከ ማታ ከአስናቀች ወርቁ ሙዚቃ ውጪ የማይከፈትባትና በተመጋቢው ዘንድ እጀግ ተወዳጅ የሆነ “አስናቀች ወርቁ” የተሰኘ ምግብ የሚሸጥባት አንዲት ምግብ ቤት !!

ለአስናቀች ወርቁ የተለየ ፍቅር ያለው የምግብ ቤቱ ባለቤት አስናቀች የችሎታና ብቃቷን ያህል አልተወደሰችም ባይ ነው፡፡ ስለዚህም የአድናቂነቱን አንድ ነገር ለማድረግ በሚል በስሟ የተሰየመ ምግብ አዘጋጅቶ የእሷን ሙዚቃ ብቻ እያስደመጠ ተመጋቢውን ያስተናግዳል…

የተፈጨ ሥጋ፣ እንቁላልና አይብ ኖሮት በቅቤና በቅመም ያበደው አንድ “አስናቀች ወርቁ” ምግብ በ60 ብር ይሸጣል ይለናል…

“እንደ እየሩሳሌም እንደ አክሱም ፅዮን፣
ተሳልሜው መጣሁ ዓይንና ጥርሱን”

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

“ሟቾች ለምን ይረሱ ? እኔም ነገ ሟች አይደለሁ”

ከላይ ያለውን የተናገሩት የ82 ዓመቱ የእድር ዕቃ ጠባቂ አቶ ደበበ ጉደታ ናቸው፡፡ በወር 300 ብር እየተከፈላቸው የንጋት ኮከብ እድርን የእድር ዕቃዎች የሚጠብቁት ጋሽ ደበበ “ሟቾች ለምን ይረሱ” ባይ ናቸው፡፡ የዕድር ዕቃዎቹን እየጠበቁ ወደሚኖሩባት የጭቃ ቤት ጎራ ብሎ ጋሽ ደበበን ያነጋገረው የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ “የጭቃ ቤቷ ግድግዳ በሟቾች ፎቶግራፍ ተሞልቷል” ይለናል፡፡

የሟችን ፎቶ ባያገኙ ከ40 ወይም የ80 ቀን መታሰቢያ ወረቀት ላይ የሟችን ፎቶ እየቀደዱ በዕቃ ቤቷ ግድግዳ ላይ ይለጥፋሉ የሚባሉት ጋሽ ደበበ፣ ከራሳቸው እድርም አልፈው የተጎራባች ሰፈር እድር ሟቾችንም ሳይቀር ለምን ይረሱ በሚል ፎቷቸውን ፈልገው ከመለጠፍ ወደኋላ አላሉም…

ተጨማሪ ያንብቡ: “ሟቾች ለምን ይረሱ ? እኔም ነገ ሟች አይደለሁ”

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ጋሽ ሰውነትን መሳዩ...የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝን የሚመስሉት እኚህ ሰው በየሄዱበት አክባሪያቸው ብዙ ነው…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (4 Comments)

Born Free የእንስሳት ማቆያ

የእንስሳት እግር ኳስ ጨዋታ በመናገሻው Born Free የእንስሳት ማቆያ…

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

አህያውን ፈርቶ ዳውላውን…

አህያውን ፈርቶ ዳውላውን…

የአዲስ አበባ፣ የቤላ አካባቢ ነዋሪዎችን ያማረረችው “አረጋሽ” ማናት ? የሸገር ልዩ ወሬ አዘጋጁ ወንድሙ ኃይሉ ወደ ቤላ ጎራ ብሎ የአካባቢውን ነዋሪ በንዴት ስለምታበግነውና አረጋሽ ስለተባለችው 13 ቁጥር አንበሳ አውቶብስ ያወጋናል፡፡ ከ3 እስከ 4 ሰዓታት ያህል እየዘገየች በምትመጣው በዚህች አውቶብስ ለዘመናት የተማረሩት በአውቶብሷ የሚጠቀሙ የአካባቢው ከብት አርቢዎች ናቸው አረጋሽ ሲሉ አውቶብሷን የሰየሟት፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች የስያሜውን ሰበብ አስመልክተው፣ ‘ወተት እያለቡ ፒያሳና መርካቶ ላሉ ደንበኞቻቸው የሚሸጡት የቤላ አካባቢ ነዋሪዎች በአውቶብሷ መዘግየት ሳቢያ ወተታቸው እየረጋ ስለሚበላሽ አውቶብሷን አረጋሽ እንዳሏት’ ይናገራሉ፡፡ እና መፍትሔው ምን ይሆን ? የሚመለከታቸው ኃላፊ ለችግሩ መፍትሔ ጨማሪ አውቶብስ መመደብ ነው ይላሉ፡፡

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers