• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

ቺቺንያ ሌላ፣ እኛ ሌላ!

‘ዳያስፖራ’ ነው፣ ከረምረም ብሎ ሊያየን ይመጣል፡፡ ከወዳጆቹ ጋር ማታ፣ ማታ ዞር፣ ዞር ይላል፡፡ እና በእሱ ድምዳሜ አገራችንን አያት፣ የቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ፣ የቺቺንያ አካባቢ ሌሊት ህይወት የእኛ ኑሮ መለኪያ ሆነለት፣ ወሰነም… “ተመችቷችሁ የለም እንዴ!” አለ፡፡

“ኸረ እባክህ አልተመቸንም! የእኛን ኑሮ ለማወቅ የሌሊቷን ቺቺንያ ሳይሆን የቀኗን የእኛን ጓዳ ጓዳችንን ተመልከት” ተባለ፡ በእጄ አላለም፡፡ እዚህ አገር እንዴት አስቸጋሪ እንደሆነችና እሱ እድለኛ እንደሆነ ምናምን ነገር ይነግሩታል፡፡ ለካስ እሱ አሜሪካ አልተመቸችውም፡፡ ምን በል ጥሩ ነው… “እናንተ ምን አለባችሁ!”

“እናንተ ምን አለባችሁ!” ብሎ ነገር ምንድነው? ብዙ፣ በጣም ብዙ ነገር አለብን እንጂ!ኑሮ እያደቀቀን፣ ብሶታችንን የሚሰማን እያጣን… “ኸረ ወገኖቻችን ከሰውነት ውጪ ሆኑ!” የሚል እያጣን ብዙ፣ በጣም ብዙ ነገር አለብን እንጂ!

መፈጠርን የሚያስጠላ ደረጃ የሚያደርስ የቤት ኪራይ አለብን፡፡ ያውም በየሦስት ወሩ የሚጨምር…ያውም አሮጌ ወንበር ስናስጠግን በታየ ቁጥር የሚጨምር…ያውም ግንባራችን ላይ የተንጠፈጠፈው ላብ የምቾት ሆኖ በታየ ቁጥር የሚጨምር፡፡

የሆነ ታሪክ ነው…እዚቹ አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ ሰውየው አንዲት በጣም ጠባብ የሆነች፣ እግር እንኳን ሙሉ ለሙሉ የማይዘረጋባት ክፍል ተከራይቶ ይኖራል፡፡ ያከራዩት እናት ማንንም ሰው እንዳያመጣ አስጠንቅቀውታል፡፡ አንድ ጊዜ የሆነ ወዳጁ ችግር ይገጥመውና ደብቆ ሊያሳደረው ቤቱ ይወስደዋል፡፡

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

“የመንግሥት ተግባር ጣፋጭ ማር ስኒ ውስጥ ማንቆርቆር ብቻ አይደለም…”

ኦፊሴላዊ ሪሴፕሽኖች ላይ ከሰው ጋር ለመቀላቀል መለኪያ ከመጨበጣቸው በስተቀር አልኮል በዞረበት አይዞሩም የሚባሉት ፑቲን ጠዋት ቁርሳቸውን ተመገበው ቡና ከጠጡ በኋላ ወደ አካል እንቅስቃሴ ነው የሚገቡት፡፡ ለሁለት ሰዓት ገደማ ይዋኛሉ ነው የሚባለው፡፡ ዋኝተው ሲጨርሱም ወደ ጂም ገብተው ክብደት ያነሳሉ…

እዚሀ ላይ አንድ አስገራሚ ነገር … ሰውዬው አገራቸውን በተመለከተ ብዙ ነገሮችን የሚያስቡትና እቅዶችን የሚነድፉት ውሀ ውስጥ እየዋኙ ባሉበት ጊዜ ነው…

ሮስቶቭ በምትባል የሩስያ ከተማ ነው፡፡ የሩስያው መሪ ቭላዲሚር ፑቲን ኮምባይን ሀርቨስተር እንዴት እንደሚያንቀሳቅሱ በሲሙሊቴር እየተማሩ ነበር፡፡ እናም ፑቲን መሪውን ጨበጡና እሳቸው ላይ ተደግነው ወደነበሩት ካሜራዎች ዘወር አሉ፣ ተናገሩም… “ነገሩ ሁሉ የሚበላሽ ከሆነ ከመጋቢት 2 በኋላ ኮምባይን ኦፕሬተር ሆኜ እሠራለሁ፡፡”

አሰልጣኝ የተባለው ሰውም “ምንም ችግር የለውም፣” አላቸው፡፡ የአገሪቱ ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ አር.ቲ ይህነኑ አስተላላፈው፡፡ ምዕራባውያኑም “ቀልዱን ተዉ፣” አሉ፣ “አሁን ማን ይሙት ፑቲን ነው ክሬምሊንን የሚለቀው ተባለ፡፡

ቢወጡስ ምን አለበት! የምራባውያኑ መገናኛ ብዙሀን “ሰውየው እኮ ቅልጥ ያለ ዲታ ነው፣” ይሏቸው የለም እንዴ! እንደውም ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር ገደማ አለው ነው የሚሏቸው፡፡
በእርግጥ በእርግጥ ይህን ያሀል ሀብት እንዳለቸው የሚያሳምኑ ብዙ ተጨባጭ የሚባሉ መረጃዎች እስካሁን አላቀረቡም፡፡ ፑቲን ግን ዶላር የሚያስነጥሰው ሀበታም ነው ሲሏቸው ዝም አላሉም፣ መልስ ነበራቸው… “አዎ፣ በአውሮፓ ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ትልቁ ሀብታም ነኝ፣ ስሜቶችን እሰበስባለሁ፡፡”

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የሬድዮ ነገር

“እሁድ፣ እሁድ ለዘማቹ ጓዴ ለጸጋዬ ኃይለ ማርያም፣ እያልሽ ዘፈን እንድትመርጭልኝ፣” ይላል የኦሮማዩ ጸጋዬ ኃይለ ማርያም፡፡ በነገራችን ላይ የዘፈን ምርጫው ነገር ሲታሰብ እኮ … አለ አይደል የተመረጠው ዘፈን ሁልጊዜ ዘማቹን ያስደስተዋል ማለት አይደለም፡፡ እሱ ቀበሮ ጉድጓድ አይነት ነገር ውስጥ ሆኖ ከዛሬ ነገ “ጦር ሜዳ እስካሁን ያገለገልከው ይበቃሀል፡፡ ወደ ከተማ ተመልሰህ በተቋማት ጥበቃ ላይ ትሰማራለህ እባላለሁ” ብሎ ልቡ ቆሞ እያለ ሚስት፣ “በእንትን ግንባር ለሚገኘው ውዱ ባለቤቴ ውረድ በለው ግፋ በለው የሚለውን ዘፈን መርጫለሁ” ስትል ይታያችሁ፡፡

“በሰላም ይመልስህ፣ ናፍቀኸናል፣ ምናምን ነገር እያለ … ጭራሽ ውረድ ‘በለው! ግፋ በለው!’ ስትል ባል ሆዬ “ይሄኔ ከዛ ከከይሲ የአብዮት ጥበቃ ሊቀመንበር ጋር ነገር ጀምራ እንዳልመለስ ፈልጋ ይሆናል…” ሊል ይችላል፡፡“አንዱ እጁን አውጥቶ ‘ሙዚቃው ሁሉ አሳደው፣ ግረፈው፣ ግደለው ነው የሚለው፡፡ ምን ማድረግ እንችላለን” ይላል ኦሮማይ ላይ፡፡ እናማ፣ ሬድዮ ለ“አትመልከች ሱፍ፣ አትዪ መኪና…” ብቻ ሳይሆን… ለ“አሳደህ በለውም” ያገለግል ነበር፡፡ ደግሞም… ‘ውሳኔ’ እንደሚሉት ፊልም አይነት እንባ በእንባ ለማድረግም ሬድዮን ማን ብሎት! “ወልደሽ ያሳደግሽኝ እናቴ ናፈቅሽኝ የሚለውን ዘፈን የዛሬ አሥራ ስምንት ዓመት ለተለየችኝ እናቴ…” ምናምን ይባልና አገር ለቅሶ በለቅሶ፡፡

የአሁኑን እንጃ እንጂ በፊት እኮ የሬድዮ የዘፈን ምርጫ የሚከታተለው ሰው ዘንድሮ ዛራ ቻንድራን መጀመሪያ አካባቢ ስንከታተል እንደነበርነው አይነት ነበር፡፡ (እግረ መንገድ … ስለሆነ ጉዳይ ለመነጋገር በተጠራ ስብሰባ ላይ ልክ አስራ ሁለት ሰዓት ሲሞላ “የዛራና ቻንድራ ሰዓት ደረሰ፣” ብለው ስብሰባውን በተኑት ሰለተባሉት ሰው የተቀለደው ነገርዬ መነሻ ቢጤ ነበረው እንዴ!”)
ሬድዮ አሁን “አንዳንድ ቀንማ ይሻላል ውሽማ…” አይነት ዘፈን ሊዘፈንለት፣ ስንት ዘመን ህዝቤ የፍቅር ዘፈን ሲናፍቀው ኖሯል፡፡ ለነገሩ ሁለት ነገር በአንዴ ማፍቀር ይቻላል እንዴ ! የአብዮት ‘ፍቅር’ አጡዞን እንዴት ብለን ነው የጠመንጃ ያዥ ሰፈሯን ደርበን የምናፈቅረው ! በፍቅር መውደቅ ብሎ ነገርን ከአገር ክህደት ጋር አመሳስለነው ነበራ፡፡ “ፍቅር መውደቅ ያለብህ ከአብዮትህ ጋር ብቻ ነው፡፡ ያኛው ፍቅር የንኡስ ከበርቴዎች ነው!” ተብሎ ነበር፡፡....

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የ‘ብላክ ፓንተርሷ’ ዋካንዳ እና የእኛዋ ኢትዮዽያ

ድፍን አፍሪካ ዳር እስከ ዳር ደስ ብሏታል፣ በ‘ብላክ ፓንተር’ ፊልም፡፡ ለምን ደስ አይበላት! ለምን “ኩራት፣ ኩራት አይልሽም ወይ?” አያሰኛት! ሆሊዉድ አፍሪካን በበጎ የመሳል ታሪክም የለውም…ያውም ጀግኖች አድርጎ፣ ያውም በቴክኖሎጂ የበለጸጉ አድርጎ! አፍሪካን በተመለከተ በቅኝ አለመያዝ፣ በቴክኖሎጂ መበልጸግ፣ ጀግነነት በሆሊዉድ ፊልሞች ላይ በአንድ አረፍተ ነገር ውስጥ የሚገቡ ቃላት አልነበሩም፡፡ ‘ብላክ ፓንተር’ ይህን ሁሉ ይለውጠው ይሆናል፡፡

በዚህም ተባለ በዛ የ‘ብላክ ፓንተር’ ነገር ዓለም አቀፍ ዝና ማግኘቱ፣ ገቢ በኩንታል መዛቁሸ አንዲትን ምናባዊ የአፍሪካ አገር ታስቦ በማያውቅ ሁኔታ በበጎና፣ በሚያስጨበጭብ መልክ ማቅረቡ ብቻ አይደለም…በተጨማሪ አትዮዽያን እንደገና በበጎ በዓለም አቀፍ መልኩ ስሟን እንዲነሳ ማድረጉም እንጂ፣ የጥንቷና በጊዜዋ ገናና የነበረችው ኢትዮዽያ ማንነትና ምንነት እንደገና ዓለም አቀፍ መወያያ እንድትሆን ማስቻሉ እንጂ፣ ታላቁ የአድዋ ድልና እምዬ ምኒልክ እንደገና በዝርዝር እንዲወሱና እንዲዘከሩ ማድረጉ እንጂ፡፡

በነገረችን ላይ ከበርካታ ወራት ዓለመ አቀፍ የእለቂትና የትርምስ ወሬ መለስ ብሎ አገራችንን እንዲህ ከፍ፣ ከፍ የሚያደርጉ ወሬዎች መስማት መቻላችን እፎይታ ነገርም አለው፣ ምንም እንኳን ጊዜያዊ ሊሆን ቢችልም፡፡ የክርክሩ ዙር እየከረረ ነው…የ‘ብላክ ፓንተሯ’ ምናባዊና ቅኝ ተይዛ የማታውቅ፣ የበለጸገችና በቴክኖሎጂ እጅግ የመጠቀች አገር መነሻ ሀሳብ ከየት ነው የመጣው የሚለው ክርክር፡፡

“ፊልሙን ያዩ ኢትዮዽያውያን ለ‘ዋካንዳ ሀሳብ’ ምንጭ የሆነችው አገራቸው እንደሆነች ይናገራሉ፣” ይላል የ‘ዋሽንግተን ፖስት’ ጽሁፍ፡፡ “እንደ አውነቱ” ሲል ጽሁፉ ይቀጥላል፣ “ኢትዮዽያ፣ ወይም በአንድ ወቅት ትታወቅ እንደነበረው አቢሲንያ፣ በመካከለኛዎቹ ክፍለ ዘመናት ለአውሮፓውያን እንቆቅልሽ የሆነች፣ እጅግ የበለጸገች እንቆቀቅልሽ የሆነች ክርስቲያናዊ አገር፣ በክፉ በሚያዩዋት የሙስሊም ሀገራት የተከበበች፣ ከተራሮች ጀርባ የተሸሸገችና የመናኙ ዮሀንስ (ፕሬስተር ጆን) አገር ነበረች፡፡”

“እንዲህ አይነት ገጸ ባሀሪያትን ብዙ ጊዜ ጥቁር ሲጨወታቸው የምታያቸው አይደሉም፣” ሲል የህግ ባለሙያዋ ብሌን ሳህሉን ይጠቅሳታል፡፡ በተለይም ብሌን የሹሪን ገጸ ባሀሪይ ትጠቅስለታለች፡፡ “የእሷ ሚና ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነች፣ ምን ያህል ብልህ እንደሆነች… ብላክ ፓንተር የሚጠቀመው ቴክኖሎጂ በእሷ አእምሮ የተፈጠረ ነው፡፡”

ተጨማሪ ያንብቡ: የ‘ብላክ ፓንተርሷ’ ዋካንዳ እና የእኛዋ ኢትዮዽያ

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

“ይቅርታ ተባሉ፣ አልተባሉ ምን እንዳያመጡ ነው”

በዛ ሰሞን ከአንዳንድ አቅጣጫዎች “ይቅርታ” የሚመስሉ ቃላቶች ሰማን ልበል! ዘንድሮ ነገሮች ሁሉ በቃላት ድሪቶና “እንዲህ የሆነበት ሁኔታ ነው ያለው…” በሚሉ የተለመዱ መቀነቶች ስለመዋጡ ምን እንደተባለና ምን እንዳልተባለ ማወቁም ግራ የሚያጋባ ሆኗል፡፡

ዳኛው ተከሳሹን…

“ለፈጸምከው ወንጀል ይቅርታ ከጠየቅህ በግሳጼ ትለቀቃለህ፣” ይሉታል፡፡
“ጌታዬ፣ ምን ብዬ ነው ይቅርታ የምጠይቀው?”
“ህብረተሰቡ ላይ ላደረስኩት ችግር ይቅርታ እጠይቃለሁ በላ!”
“ጌታዬ አኔ መች ችግር አደረስኩ?”

“ህገ ወጥ አልኮል ስታመርት ተይዘሀል፣ አይደል እንዴ!”
“እኔ፣ ጌታዬ! በጭራሽ እንደዛ አላደረግሁም፡፡”
“በጭራሽ ማለት ምን ማለት ነው! አልኮል ማምረት የሚያስችሉ መሳሪያዎች አሉህ አይደለም እንዴ?”
“እንደዛ ከሆነ ጌታዬ በአስገድዶ መድፈርም ይክሰሱኝ፡፡
“ለምን? የሆነች ሴት አስገድደህ ደፍረሀል እንዴ?”

“ጌታዬ አልደፈርኩም…ግን እንደዛ ማድረግ የሚያስችል መሳሪያው አለኝ፣” አለና አረፈው፡፡
በእርግጥ ይሄ ለፍርድ ያስቸግራል፡፡

ዘንድሮ እኛ ዘንድ ይቅርታ ሊጠየቅባቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች አሉ፡፡ ብዙ ጥፋቶች አሉ…ሆነ ተብለው ከቅንነት ጉድለት የሚፈጸሙ፣ በስልጣን ወይም በሀብት ሽፋን በማን አለብኝነት የሚፈጸሙ፣ ሳናውቅ የምናውቅ እየመሰለን በእውቀት ማነስ የሚፈጸሙ፣ “ሰለሰው፣ ስለሰው ቀድጄ ልልበሰው” በሚል አይነት አመለካከት በግዴለሽነት የሚፈጽሙ፡፡ ምነዋ ታዲያ ይቅርታ ጠያቂዎች አነስን!

በነገራችን ላይ… ይቅርታ ጥሩ ነገር ነው፡፡ የተበላሸውን ባይጠግንም ቢያንስ፣ ቢያንስ ጥፋትን አምኖ ይቅርታ ማለት መሸነፍ ሳይሆን ማሸነፍ ነው፡፡ ዝቅ ማለት ሳይሆን፣ ከፍ ማለት ነው፡፡ የመንፈስ ድክመትን ሳይሆን የመንፈስ ጥንካሬን የሚያሳይ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን በግለሰብም፣ በቡድንም ሆነ በድርጅት ደረጃ ይቅርታ መጠየቅ በራስ ላይ እድሜ ይፍታህ መፍረድ የሚመስላችው በዝተዋል፡፡

“ይቅርታ ተባሉ፣ አልተባሉ ምን እንዳያመጡ ነው” አይነት አመለካከት የብስለት ምልክት አይደለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: “ይቅርታ ተባሉ፣ አልተባሉ ምን እንዳያመጡ ነው”

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers