• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር | ወግ

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከወንድሙ ሀይሉ ጋር የካቲት 28፣2007

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከወንድሙ ሀይሉ ጋር የካቲት 28፣2007

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

የጉለሌው ወርቀሉል

በድሮ ጊዜ ነው አሉ፡፡ ከጠላት ወረራ በኋላ ከተማዎቻችን እየተሰፋፉ መብራትና ውሃ በየቤቱ እየገባ የመብራትና የውሃ ቆጣሪዎች እየተሠማሩ ሂሳብ ያሰከፈሉ ነበር፡፡ እንደዛሬው መጥታችሁ ክፈሉ ለሁሉም የሚባል ነገር አልነበረም፡፡

ታዲያ አንድ በጠላት ዘመን ለሃገራቸው በዱር በገደሉ ሲዋደቁ የነበሩ ሰው የውሃ አልከፍፈም አሉ፡፡ ‹‹ለምን አይከፍሉም?›› ሲባሉ ለመብራቱ ይሁን ዘመን ያመጣው ጥሩ ጠቃሚ ነገር ነው እከፍላለሁ፡፡ ለውሃውም ቢሆን ውሃው ለመጣበት ብረትና ለመዘውሩ ግድየለም ልክፈል፡፡ …. እንዴ እኔ አምስት አመት ሙሉ በዱር በገደሉ የታገልኩላት የደማሁላት የቆሰልኩላት ሃገሬን ውሃ በነፃ ላልጠጣ ነወይ?›› ብለው በንጉሱ ጊዜ ‹‹ተውት አትጠይቁት!›› ተበሎላቸው የውሃ አይከፍሉም ነበር ይባላል፡፡

ወይ ቤተመንግስቱ ከፍሎላቸዋል ወይ በኋላ ወራሾቻቸው ከፍለው ይሆናል እንጂ መቼም የመንግስት ገንዘብ በብላሽ አይቀርም፡፡

በዛሬ ዘመንም ከተሞቻችን እያደጉና ያረጁ ያፈጁ መንደሮች እየፈራረሱ በኮንደሚኒየሞችና በዘመናዊ ፎቆች እየተገነቡ ናቸው፡፡ መንገዶች ባማረ ሁኔታ ባልነበሩባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተዘረጉ እናያለን፡፡ ነዋሪዎችም ከኖሩበት መንደር ‹‹ለልማት ይፈልጋል ተነሱ›› እየተባሉ ለልማትና ለተሻለ ኑሮ ከሆነ ይሁን እያለ እድርና እቁባቸውን እየበተኑ ጓዟቸውን ሸክፈው ሌላ ሰፈር ተዛውረዋል እየተዛወሩም ነው ወደፊትም ይዛወራሉ፡፡

ያውም ደስ እያላቸው የተሻለ መንድር የተሻለ ሃገር ማን ይጠላል፡፡ በተለይ የበቀደሙን ባቡር ያየ አሮጌውን ሰፈር ለመልቀቅ አይኑን አያሸም!

በሌላ በኩል ደግሞ ቤተክርስቲያኗ ልማት ስለፈቀደች እሱም ቢሆን ግን ለባቡር ለትላልቅ ኢንዱስትሪና መሰል ነገሮች እንኳን የተከራየነውን የሰራነውንም ቤት ለቀን እንዛወር ለሆቴልና ለገበያ መኖሪያን መልቀቅ ግን አግባብ ነወይ? ኑና በዙሪዬ ያኖራችሁትን የዘመዶቻችሁን አስከሬን አፅም እንድታነሱ እየተባለ ነው፡፡

በተለይ የቀድሞ ሰበካ ጉባኤያችንን ለቀን አዲስ ሰፈር ለሰፈርን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው የሆነብን፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? እኛስ ነዋሪዎቹ ለልማትና ለተሻለ ኑሮ ቦታ እንቀይር ወይም እንዲሁ ያሰነሱን ይሆን እያልን በሃሳብ እንወዝወዝ የሙታኑ እንኳ አፅም በሰላም ቢያርፍ ምን አለበት?

የዘንድሮ ልማት ነገር እንዲህ እንኳን ነዋሪ ቀባሪ የተቀበረም አይቅረኝ እያለ ነው፡፡

መቼስ ለልማት ከሆነ ምን ይደረግ! ለኛ ለነዋሪዎቹ ሲባል እሰከዛሬ የተለዩንን ሙታን እርም በልተን አፅማቸውን ዞር እናድርግ … ነገር ግን የእኛስ የወደፊት መውደቂያ መቀብሪያችን ነገር … እንዴት ሊሆን ነው?

በልማት ሳቢያ የማይቀየር ቋሚ የሆነ አፅም ማሳረፊያ ቦታ ካሁኑ ቢበጅልን አይሻልም?

ወይም ደግሞ አፅም ከመቃብር ወደመቃብር ስንቀይር ከምንኖር ዘልማዳችንን እንቀይርና እንደ አንዳንድ ሃገሮች ህዝቦች የአሰክሬን ማቃጠያ ቦታ ይሰናዳልንና እያቃጠልን አመዱን አባይ ላይ እንበትነው!

ጐበዝ አፅማችን እንኳ እፎይ ብሎ እርፍ ይበል እንጂ! ኖረንም ሞተንም ሰፈር ሰንቀይር ምን ይባላል? ለዚህ ሃገር የቆሰሉ የደማላት ውሃዋን እንኳ ላልጠጣ ነው እንዴ እንዳሉት ሰውዬ… የተሰደደው ሁሉ መቀበሪያዬ የሚላትን ሃገር እኛ ጉያዋ ሰር ኖረን የለፋን የደክምንላት ልጆቿ አፅማችንን እንኳ ማሳረፊያ ቦታ ልታሳጣን ነው እንዴ?

እናንተስ ምን ትላላችሁ? ሃሳባችሁን እንጠብቃለን!

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

መታሰር ያስፈራል?

ፍርሀተ- እስርቤት ወይም ፈረንጆቹ ስር የሰደደ፣ ምክንያት አልባ የሚሉት አይነት የመታሰር ፍርሀት(phobia) ገና ህክምናው እውቅና አልሰጠውም፡፡ ነገር ግን ሌሎች ህክምናው ቅጥ የለሽ ፍርሀት (phobia) ናቸው ከሚላቸው ጋር ሊዛመድ ይችላል፡፡ ለምሳሌ Cleithrophobia በተወሰነ ስፍራ ተቆልፎ መቀመጥ የሚፈጥረው የፍርሀት ዓይነት ነው፡፡ Claustrophobia የጠባብ እና የታጠረ ቦታ ፍርሀት ይባላል፤ Isoolophobia- ከሌላው ሰው የመነጠል ፍርሀት ነው፤ Monophobia - ለብቻ የመሆን ፍርሀት ይሉታል፤ Dikephobia ደግሞ ፍትህ የማጣት ፍርሀት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: መታሰር ያስፈራል?

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ለምን ግን አንሰለፈም

በአለም ከጫፍ እስከ ጥግ በኑሮ ውጣ ወረድ በየሁሉም ማዕዘን የፈለጉትን ለማግኘት የታለመውን ለመፍታት ከታሰበው ለመድረስ በየሁሉም መንገድ ችግሮች እንደ አሽን የበዙ ናቸው፡፡ መሰናክሎችን መዝለል እና ማለፍ ይደክማል ፈተናዎችንም መቁጠር ይታክታል፡፡ ታዲያ በዚ ሁሉ መመላለስ ግን ችግሮችን ለመፍታት ከማሰብ ይልቅ ለእክሎቹ መፍትሄ የሚሆኑ ሃሣቦችን ከመምዘዝ ውጪ እና የተፈጠሩትን ችግሮች በትዕግስት ጠብቆ ከመፍታት ባሻገር ባልተገባ አቋራጭ እና በተሰባሪ ድልድይ ላይ ለማለፍ መሞከር የእክሎችን ጐዳና ከማርዘም ውጪ አና የባሰ ዝፍቀት ውስጥ ከመክተት ባሻገር ትክክለኛ አማራጭ ሆኖ አይታይም፡፡ ታዲያ ችግሮችን ለማቅለል እስከጭራሹም ለመፍታት በግለሰብም ይሁን በማህበር በሀገርም ይሁን በአለም ደረጃ በሚደረጉ እቅንስቃሴዎች ሁሉ ሁሉም ግቡን አንድ እያለ ለማስቆጠር ችግሮችን ለመፍታት ተራው ደርሶ ከእልፍኝ ለመግባት የተፈለገው ላይ ለመድረስ መሰለፍ እንደአማራጭ ሳይሆን ግዴታ ይሆናል፡፡ ለምሣሌ በኑሮ ውጣ ወረድ ውስጥ አብዛኛው ማህበረሰብ የትራንስፖርት ተጠቃሚ ነው የታክሲ ፡ የአውቶብስና ሌላም ሊሆን ይችላል ፤ በማለዳ ሁሉም እንደደረጃው እንጀራውን እና የዕለት ጉርሱን ለማብሰል እንደየፊናው ተሰልፎ ጊዜ ቆጥሮ ባገኘው እና በተካነበት ሙያ ለመሰማራት ዕለቱን ሀ ብሎ ለመጀመር ወደ ሚሰራበት ያቀናል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: ለምን ግን አንሰለፈም

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

መቆየት ወይስ ታሪክ ማቆየት?

በኢትዮጵያ እና በኢጣሊያ መካከል ስለተወደረገው ጦርነት ስታስቡ መጀመሪያ ወደ አእምሯችሁ የሚመጣው በቪዲዮ ምስል የትኛው ነው? ወይም በየአመቱ የአርበኞች መታሰቢያ ወይም የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሲከበር ተደጋግሞ ለቴሌቪዥን ዘገባ ጥቅም ላይ የሚውል ባለ ነጭ እና ጥቁር ተንቀሳቃሽ ምስል? በእርግጠኝነት የጦር መሪዎች ፈረስ ላይ ተቀምጠው፣ወንዶች ጦር እና ጋሻ ይዘው፣ሴቶች አገልግል ተሸክመው ሲፎክሩ እና ሲሸልሉ ያያችሁት ይሆናል፡፡በርካታ ሰዎች ታሪኩ በተከሰተበት ወቅት የተቀረፀ የሚመስላቸው ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ የተሠረተችበት 100ኛ ዓመት በዓል በ1979 ዓ.ም ሲከበር ለበዓሉ ድምቀት ሲባል በድጋሚ መልሶ የተከወነ ነው፡፡ የታወቁ ተዋንያንን ጨምሮ ወደ 4000 ሰዎች እንደተሳተፉበት ይነገራል፡፡ ምስሉ በታዋቂው የቲያትር ዳይሬክተር አባተ መኩሪያ የተዘጋጀ አድዋ ድልድይ በሚባለው እና አሁን ላይ በዘመናዊ አስፋልት በተሸፈነው ሜዳ ላይ የተቀረፀ ነው፡፡ ድራማዊ የምስል ቀረፃው የከተማ ልደትን ለማክበር የታሰብ ብቻ ሳይሆን ታሪክን ለማቆየት የተደረገ ሙከራም ነበር፡፡

ይህ ጨዋታ ያለ ነገር አልተነሳም፡፡ ከተማችን አዲስ አበባ በፈጣን የለውጥ ሂደት ላይ ትገኛለች; በከፍተኛ የመልክ ወይም የገፅታ ለውጥ፡፡ ከጠባብ እና ኮሮኮንቻማ መንገድ ወደሰፋፊ አስፋልት እና ኮብል ስቶን ንጣፍ መንገድ፣ካዘመሙ የጭቃ መኖሪያ ቤቶች ባለድርብርብ ፎቅ ዘመናዊ ህንፃዎች፤እርስ በርስ ከተዛዘሉ እና ጣራቸው በሮ እንዳይሄድ በድንጋይ ከተጠበቁ ደሳሳ ጎጆዎች በስነህንፃ ውበታቸው ያማሩ፣የተራቀቁ፣ በመስተዋት ያሸበረቁ ሆቴሎች እና የገበያ ማዕከላት፣የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፣የቀለበት መንገድ፣የቀላል ባቡር መንገዶች፡፡ አዲስ አበባ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የነበራት ገፅታ እና ከ10 ዓመታት በኋላ የሚኖራትን መልክ ሁለት የተለያዩ ከተሞችን የማነፃፀር ያህል ሊከብደን ይችላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: መቆየት ወይስ ታሪክ ማቆየት?

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers