• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 16፣2009

“የሄሊኮፕተር ጅማሮ”

የኛ ሀገር ወታደሮች ከእናት ያመሳስሏታል፡፡ “እናት” በሚል ቁልምጫም ይጠሯታል፡፡

ይሄ ይጐረብጠኛል ያኛው ቦታ ይቆረቁኛል ሳትል በየአስቸጋሪው መልክዓ ምድር ሳይቀር በማረፍ እጅግ አስፈላጊያቸው ነች፡፡

ስንቃቸውን፣ ትጥቃቸውን፣ ውሃቸውን ታቀርባለች፡፡ ተዋጊያቸውም ተከላካያቸውም ሆና ታግዛለች፡፡

የወታደሮቹ “እናት” ሂሊኮፕተር ነች፡፡

ትውልደ ሩሲያ አሜሪካዊው ኢጐር ኢቫኖቪች ሲኮርስኪ የመጀመሪያውን የተሳካ የሂሊኮፕተር በረራ ሙከራ ያከናወነው የዛሬ 77 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሂሊኮፕተር ለጐማዎቿ ወይም ለብረት ክናዷ ማሳረፊያ እስካገኘች ድረስ ለማረፍ የግዴታ ሰፊ ደልዳላ ሜዳ ይሁንልኛ አትልም ስትነሳም መንደርደርም ሆነ ማኮብኮብ አያሻትም፡፡ ያው ካለችበት ቀጥ ብላ ወደላይ አየሩን ትቀዝፋለች፡፡

በአየር ላይ በአንድ ቦታ ሚዛኗን ጠብቃ መቆየት ከአውሮፕላን የምትልቅበት ቴክኒካዊ ብቃቷ ነው፡፡

በየገደላ ገደሉ በየሸለቆው መካከል መሹለክለክ ሽር ማለቱ ኧረ ስንቱ ይሄ ሁሉ የሂሊኮፕተር ገድል ነው፡፡

እንደ አውሮፕላን ሁሉ የሂሊኮፕተር መፈልሰፍ በሰው ልጅ አዕምሮ የተፀነሰው በቀደመውና በራቀው ዘመን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 15፣2009

የቦኒ ፓርከር ነገር

በአሜሪካ ሉዚያና ቦኒ ፓርከር ‹‹ጉዞው ተፈፀመ›› ስትል ግሩም የሆነ ግጥም ፃፈች፡፡ ግጥሟንም ለእናቷ  ላከችላት፡፡ እናትየዋም ለጋዜጦች ሰጠቻቸው፡፡ ጋዜጦቹም አትመው አወጡት፡፡

ፓርከር የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረችበት ወቅት የነበራት የስነ-ፅሁፍ ዝንባሌ እንዴት ያለች ታላቅ ደራሲና ግሩም ባለቅኔ ይወጣታል ተብሎላት ነበር፡፡

በመጨረሻ ግን መታዋቂያዋ ግጥምና ስነ-ፅሁፍ መሆኑ ቀርቶ ክላይድ ባሮው ከተባለ የዘራፊ ቡድን አለቃ ጋር የፍቅርም የውንብድናም ባልንጀራ ሆኖ ታሪኳ የውንብድና ሆነ፡፡

በውንብድናዋ የገጣሚነት ተስፋዋ በአጭሩ ተቀጭቶ ከነ ግብር አበሯ የተገደሉት የዛሬ 83 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በ1930ዎቹ መጀመሪያ በታላቁ የዓለም የምጣኔ ሐብት ቀውስ አገሩን አመሰው፡፡ በዚያ ላይ የነቦኒ ፓርከር መጠነ ሰፊ ዝርፊያና ውንብድና ለአገር ምድሩ አስቸገረ፡፡

ዘራፊው ቡድን በማዕከላዊ የአሜሪካ ግዛቶች ከስፍራ ስፍራ በመዘዋወር ገጠር ከከተማ  አራቁቷል፡፡

ከትናንሽ መደብሮች እስከ ታላላቅ የገበያ ማዕከሎች ድረስ ዘርፏል፡፡ በደርዘን የሚቆጠሩ ባንኮችን ካዝና ገልብጧል፡፡

ዘጠኝ ፖሊሶች ገድሏል፡፡ የጨረሳቸው ሲቪሎች ብዛት ቤቱ ይቁጠራቸው የተሠኘላቸው ናቸው፡፡

የሕዝቡ ምሬትና እምባው በዛ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 14፣2009

የአሜሪካ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ዩ.ኤስ.ኤስ ስኮርፒዮ

ስኮርፒዮን ቃኚም ሰላይም ተዋጊም ነበረች፡፡

በሙሉ መጠሪያ ስሟ ዩ.ኤስ.ኤስ ስኮርፒዮን የተሠኘችዋ የአሜሪካ ባሕር ሰርጓጅ መርከብ  10ኛ አመት ልትደፍን አንድ አመት ሲቀራት ጥገና ተከናወነላት፡፡

የጦር መሳሪያ ስርዓቷ ሁሉም አካሎቿ በወግ በውጉ ስለመሆናቸው ፍተሻ ተደረገላቸው፡፡ ልምምድም ተካሄደባት፡፡

ከዚያም ለተልዕኮ ወጣች፡፡ ማዳረስ ያለባትን አዳረሰች፡፡ ማካለል የነበረባትን ቦታዎች አካለለች፡፡

መርከቧ ከወራት ተልዕኮ በኋላ ወደ ማረፊያዋ እየተመለሰች ሳለ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በሳራጋሶ ባሕር ምሠራቃዊ ዳርቻ የሰጠመችው የዛሬ 49 ዓመት በዛሬው እለት ነበር፡፡

ከ99 ባሕረኞቿ ጋር መኖሪያዋን ከጥልቁ የውቅያኖስ ስርቻ አደረገች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ግንቦት 7፣2009

የአረቦችና እስራኤል ነገር

እስራኤልና አረቦች አነስተኛዎቹን ሣይጨምር ከአንዴም አምስት ጊዜ ታላላቅ ጦርነቶችን አድርገዋል፡፡

ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች ቀዳሚውን ታላቅ ጦርነት ማካሄድ የጀመሩት የዛሬ 69 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የታላቁ ጦርነት መጀመሪያ የዛሬ 69 ዓመት የዛሬዋ ዕለት ብትሆንም በፍልስጤም ምድር እሥራኤልና ፍልስጤማውያን ቁርቋሷቸው የጀመረው ከዚህ ጦርነት በፊት ነው፡፡

ከ70 ዓመታት በፊት ብሪታንያ የፍልስጤም ግዛት ሞግዚታዊ አስተዳዳሪነቷን ስትተወው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፍልስጤም በአይሁዳውንና በፍልስጤም አረቦች ይዞታነት እንድትከፈል ወሰነ፡፡

ከ69 ዓመታት በፊት የእስራኤል ነፃ አገርነት መታወጁን በፀጋ አልተቀበሉትም፡፡

የእስራኤል ነፃ አገርነት በታወጀ ማግስት ግብፅ ሶሪያና ዮርዳኖስ በእስራኤል ላይ ጦርነት ከፈቱባት፡፡

የኢራቅ ወታደሮችም በግብፅ፣ ሶሪያና ዮርዳኖስ ደጋፊነት በውጊያው ተሰለፉ፡፡

ይሄ ከሆነ ዛሬ 69 ዓመት ሆነው፡፡

ጦርነቱ ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ ለ10 ወራት ተካሄደ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 25፣2009

እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያሉ የጃፓን መንግስታት ደርሶ ጦረኝነት የሚያጠቃቸውና ወታደራዊነት የሚያመዝንባቸው ነበሩ፡፡

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከጀርመን ናዚና ከጣሊያን ፋሺዝም ጋር አብረው ተሰላፉ፡፡ ኢስያን ለማስገበር ተነሱ፡፡

ታዲያ የኋላ ኃላ እንደ ጦር አጋሮቻቸው የነሱም መጨረሻ አላማረም፡፡

ጥቅም ላይ መዋሉ እምብዛም አሳማኝነት ቢጐደለውም አሜሪካ ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ በተባሉ ከተሞቿ ላይ እስካሁን  አሻራቸው አልለቀቀም የተባላላቸውን የአቶሚክ ቦንቦች ብትጥልባቸው ሰበብ ምክንያቷ ጦርነኝነታቸው ነበር፡፡

ኃላም እንደ ሀገር ለአሸናፊዎቻቸው እጅ መስጠትን አስከተለባቸው፡፡

ከዛን ጊዜ ወዲህ ጃፓን በፍፁም ሰላማዊ አገርነትዋ ነው የምትታወቀው፡፡

ለዚህ ሰላማዊነቷ ዋስትና የሰጠውና ፈር የቀደደው አዲሱ ሕገ-መንግስቷ ስራ ላይ መዋል የጀመረው የዛሬ 70 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ሕገ መንግስቱ ጦረኝነት እርም ይሁንብን አለ፡፡ አነወረው፡፡

ከዚያ በፊት የጃፓኑ ንጉስ የፍፁም አዛዥ ናዛዥነት የአድራጊ ፈጣሪነት ስልጣን ነበራቸው፡፡ 

ሕገ-መንግስቱ ከመጣ በኋላ እርሶዎ የሀገር ተምሳሌት በመሆን ስልጣንዎ ይገደባል ተባሉ፡፡ እሳቸውም እሺ ብለው ተቀበሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers