• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣መጋቢት 20፣2009

የናዚ ጀርመን 4ኛው አርሚ…

ባለ ብዙ ክፍለ ጦሮችና ብረት ለበስ ኃይሎች ስብስብ የሆነው የ2ኛው የዓለም ጦርነት ዘመኑ የጀርመን 4ኛው አርሚ በታላላቅ ውጊያዎች በመካፈል ዝናው የገዘፈ ነበር፡፡

ወደ ጦርነቱ ማብቂያ ታሪክ ተቀየረ፡፡

የጀርመን 4ኛው አርሚ በሶቪየት ኃይሎች ዳግም እንዳይነሳ ሆኖ የተደመሠሠው የዛሬ 72 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡

ጀርመን ምስራቃዊቱን ጐረቤቷን ፖላንድን በመውረር በ20 ቀናት ውጊያ ሙሉ በሙሉ በእÍ አስገባቻት፡፡

ይሄው የጦር ክፍል የጀርመን ኃይሎች ፖላንድን ሙሉ ለሙሉ በእጃቸው ያስገቧት በ20 ቀናት ውጊያ ነው፡፡

ዋነኛው የዘመቻው ኃይል ገናናው  የጀርመን 4ኛው አርሚ ነበር፡፡

ጀርመን ፈረንሳይን ስትወርም ከሌሎች የአገሪቱ የጦር ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ቁልፍ ሚና ነበረው፡፡ 

ጀርመን በዘመቻ ባርባሮሳ በሶቪየት ህብረት ላይ ወረራ ስትፈፅም የአንበሳው ድርሻ የዚሁ የጦር ክፍል ነበር፡፡

በጦርነቱ መጀመሪያ ገናናው 4ኛው አርሚ በሶቪየቶች ላይ ታላላቅ የሚባሉ ድሎችን ተቀዳጀ፡፡ በበርካታ አውደ ውጊያዎች በለስ እየቀናው መጣ፡፡

 

ድል አድራጊነቱ ከሁለት ዓመት በላይ ሊዘልቅ አልቻለም፡፡ ዋነኛው ኃይል በስታሊንግራድ እንደተመታ ታሪክ መለወጥ ጀመረ፡፡

ግስጋሴው ተገታ ፤ ወደ እግር መንቀል ገባ፡፡ ያ ነባር ግስጋሴው ወደ ማፈግፈግ ተቀየረ፡፡ የውጊያ ዛር ሞተበት፡፡

ከማፈግፈግም አልፎ የእግሬ አውጭኝ ሸሽትን ስራዬ ብሎ ተያያዘው፡፡

በአውሮፓ ጦርነቱ ሊያበቃ ከ2 ወራት ያነሰ እድሜ በቀረው ጊዜ በምስራቃዊ ፕሩስያ የተሠበሰበው 4ኛው አርሚ የመጨረሻው ስብስብ የሶቪየት ቀይ ሠራዊት የሰነዘረበትን ብርቱ ማጥቃት መቋቋም ተሳነው፡፡ ክፉኛ ተፍረከረከ፡፡ ሲደመስስ የኖረው ይሄ የጦር ክፍል አብዛኛው ኃይሉ በሶቪየት ኃይሎች ተከቦ የመደመሰስ ወር ተረኛው ራሱ ሆነ፡፡

ለወሬው ነጋሪ የተረፉት የ4ኛው አርሚ ጥቂት ወታደሮች በእሬ አውጭኝ ተበታተኑ፡፡

የገናናው የጀርመን 4ኛው አርሚ ኃይል እንዳለ መደምሰሱ የናዚዎቹ ክፉ ሐሳብ ዳግም እንደይነሳ ሆኖ ወደ መቃብር እንደሚሸኝ የቅርብ ምልክት ሆነ፡፡

ከ4ኛው አርሚ መደምሰስ በኋላ የናዚዎች የጥፋት አውታር ተንኮታኮተ፡፡

ከንቱው የበላይነት ሕልማቸው መከነ፡፡

2ኛው የዓለም ጦርነት በሕብረቱ ኃይሎች የበላይነት ተደመደመ፡፡

የናዚ ቱባ ቱባ ሹሞች ለክፉ ኃሳብና ድርጊታቸው በኑረምበርጉ ችሎት እንደየጥፋታቸው የእጅ የእጃቸውን ተቀበሉ፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers