• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 4፣2009

የዩሪ ጋጋሪን የጠፈር ጉዞ

የዛሬዋ እለት በጠፈር ምርምርና ጉዞ ታሪክ ልዩ ቦታ አላት፡፡

ሩሲያዊው ጠፈረተኛ ዩሪ ጋጋሪን ቨስቶክ 1 በተባለችዋ መንኮራኩር ወደ ሕዋው የምድራችን ምህዋር የመጠቀው የዛሬ 56 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡

ይህም ጠፈረተኛውን በጠፈር ሳይንስ ታሪክ ወደ ሕዋው በመምጠቅ የመጀመሪያው ያደረገው ክስተት ነበር፡፡

ሕዋውን የተምነሸነሸበት ዩሪ ጋጋሪን በትምህርት ቤት ቆይታው የትራክተር ቴክኒክን አጠና፡፡

በስራ ዓለምም በወደብ የመርከብ እቃ ጫኝና አውራጅነትም በትርፍ ጊዜ ሠራተኛነትም አገልግሏል፡፡

ጋጋሪን በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ወደ አውሮፕላን በረራ አፍቃሪዎች ክበብ ብቅ ብቅ ማለት ጀመረ፡፡

የባለ ሁለት ሰው አነስተኛ አውሮፕላኖችን ማብረር ተለማመደ፡፡

ይሄ ልምምዱ ኋላ የሶቪየት ህብረት አየር ኃይልን እንዲቀላቀል አገዘው፡፡

በአየር ኃይል ስልጠናው በዘመኑ ዘመን አፈራሽ የነበረውን ሚግ 15 እንደልቡ የሚያቀለጣጠፍበትን ልምድ አስጨበጠው፡፡ በበረራው ተካነበት፡፡

በመጀመሪያ ምክትል የመቶ አለቃ ብዙም ሳይቆይ የመቶ አለቃ ሆነ፡፡

ጋጋሪን ከተዋጊ ጄት አብራሪነቱ በተጨማሪ የተለያዩ የስፖርታዊ ጨዋታዎችን ስራዬ ብሎ ተያያዘ፡፡

ሶቪየት ህብረት የቨስቶክ የጠፈር መጠቃ ሲወጠን ጋጋሪን ለዚሁ ተግባር ከተመረጡት ከ20 ከማይበልጡ ወጣት መኮንኖች አንዱ ሆነ፡፡

 

ተልዕኮው የተለያዩ ገፅታዎች የአካላዊ ቁመናን፣ ጥንካሬን፣ የመንፈስ ብርታትና ንቁነትን የሚጠይቅ ነበር፡፡

እንደ ተልዕኮው ክብደትም መምረጫ መስፈርቶቹም ጠጠር ያሉ ነበሩ፡፡

ተደጋጋሚ ማጣሪዎችን ማለፍ ጠየቀው፡፡

በእርግጥም የዓለማችንን የመጀመሪያውን የጠፈር ተጓዥ የመምረጡ ተግባር ቀላል አልነበረም፡፡

በበረከቱ መመዘኛዎችም ዩሪ ጋጋሪን ከ20ዎቹ መኮንኖች ተመራጩ ሆኖ ተገኘ፡፡

በቨስቶክ 1 የሠፈር መንኮራኩር ወደ ህዋው መጠቀ፡፡

የዓለማችንም ፈር ቀዳጅ ጠፈረተኛ መሆን ቻለ፡፡

የዛኔዋ ሶቪየት ህብረት ኩራት ተሠማት፡፡ ፈነደቀች፡፡

ዓለምም የዩሪ ጋጋሪንን ስኬት አደነቀ፡፡

ጋጋሪን ጀግና ተባለ፡፡ ተሞካሸ፡፡

ከጠፈር ተልዕኮው መልስ የአየር ኃይል ተልዕኮውን በጀመረበት ሚግ 15 ሲበር ባጋጠመው የመከስከስ አደጋ ከ49 ዓመት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ጋጋሪን ሀ ብሎ የጀመረው የጠፈር ጉዞ አሁን ላይ ወደ ላቀው ደረጃ ተሸጋግሮ የእለት ተለት ተግባር ያህል እየተቆጠረ ነው፡፡

የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers