• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 10፣2009

የሂሳብና የፊዚክስ ሊቁ አልበርት አንስታይን ከሊቅነትም በላይ በሊቀ ሊቃውትነቱ ይታወቃል፡፡ይሄ ስሙም ዝናውም ስራውም የገዘፈ ሊቅ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የዛሬ 62 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡አነስታየን ከአይሁዳዊ ቤተሰብ የተወለደው ጀርመን ውስጥ ነው፡፡
ሕፃን ተማሪ ሳለ አባቱ የአቅጣጫ ማመልከቻ የኪስ ኮምፓስ ያሳየዋል፡፡ ሕፃኑ አነስታየን መርፌ መሳይዋ የኮምፓሱ አቅጣጫ አመላካች ቀስት ወዲህ ወዲያ ስትል አስተዋለ፡፡
 
አንስታይን የአቅጣጫ አመላካቿ ወዲህ ወዲያ ማለት ያለ ምክንያት አይደለም አለ፡፡
 
ማሰላሰል መመራመሩን ተያያዘው፡፡
በወጣትነቱ በሲዊዘርላንድ በዙሪክ ፖሌቴክኒክ ኢንስቲትዩት ለማመር የመግቢያ ፈተና ወሰደ፡፡
 
አጠቃላይ ውጤቱ ወደ ተቋሙ ከሚያስገባው በታች ሆነ፡፡ ነገር ግን ፈተና ከወሰደባቸው የትምህርት አይነቶች በሂሳብና በፊዚክስ ያመጣው ውጤት በተቋሙ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ውጤት ነበር፡፡
 
አነስታይን ተቀጥሮ ያከናውናቸው ከነበሩ ስራዎች በተጓዳኝ በፊዚክስና ሂሳብ መስክ ወደ ሰፊ ጥናትና ምርምሩ ገባ፡፡
 
ከዙሪክ ዩኒቨርስቲም የዶክትሬት ዲግሪውን አገኘ፡፡
 
የአንፃራዊነት ንድፈ ኃሳብና ሌሎችም ለሳይንስ ታላቅ እርምጃ ማሳየት አሻራ ያኖሩ ስራዎቹ ዕውቅናና ክብሩን አገዘፉለት፡፡
 
ከ300 በላይ ከፍተኛ ሳይንሳዊ ዋጋ ያላቸውን የምርምርና የጥናት ፅሁፎችን አበረከተ፡፡
 
አነስታየን ስሙ ሊቀ-ሊቃውንት ለሚለው ቃል አቻ ፍቺ እስከመሆን ደረሰ፡፡
በፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሸልማት ባለክብርም ሆኗል፡፡
ከ84 ዓመት በፊት አነስታይን ወደ አሜሪካ አቀና፡፡ በአገሩ ጀርመን ናዚዎች ፖለቲካዊ ተፅዕኗቸው እየበረታ መምጣቱ ስጋቱን አበረታው፡፡ እዛው አሜሪካ ለመቅረት ወሰነ፡፡
እጆቿን ዘርግታ የተቀበለችው ታላቋ አገር ታላቁን ሰው ወዲያውኑ ዜጋዋ አደረገችው
 
አነስታይን እንደፈራው ናዚዎቹ በጥቂት ዓመታት ውስጥ የ2ኛውን የዓለም ጦርነት ማቀጣጠሉን ተያያዙት፡፡
ወደ አሜሪካ የተሰደዱ የሐንጋሪ ሊቃውንት ለዘመኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት ብርቱ ማሳሰቢያ ፃፉ፡፡
 
ማሳሰቢያውም ናዚዎቹ የኒኩሊየር ጦር መሳሪያ ባለቤት ለመሆን እየተጣደፉ መሆኑን ሹክ የሚል ነበር፡፡ በሊቃውንቱ ደብዳቤ ላይ የአነስታይንም መልዕክትና ፊርማም ማረፉ ጉዳዩ ከብዶ እንዲታይ አደረገው፡፡
ሩዝቤልት ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን አልፈለጉም፡፡
 
አሜሪካ የማንሐተን ፕሮጄክት በመባል በሚታወቀው ውጥን ለአቶሚክ ቦምብ ባለቤትነት ፈጠነች፡፡
ከማንም አገር ቀድማ የአቶሚክ ቦምቦ ባለቤት ሆነች፡፡
 
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተቃረበም ጊዜ አሜሪካ ቢሂሮሺማና ናጋሳኪ ላይ ቦንቦቹን ጣለቻቸው፡፡ እስከዚያ ዘመን ታይቶ የማይታወቅ ጥፋት ሆነ፡፡
 
አንስታየን ወደ ሕህወት ዘመኑ መጨረሻ ግድም አሜሪካ የአቶሚክ ቦምብ እንድትሠራ ለሩዝቬልት ደብዳቤ መፃፌን እንደ ታላቅ ስሕተት እቆጥረዋለሁ አለ፡፡ ተፀፀተ፡፡
ግን እኮ’ንም ጨመረበት፡፡
 
ይሄን እንዳብሰለሰለ ከዓመት በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
 
አልበርት አንስታይን በበዙ የሳይንሳዊ ምርምርና የጥናት ስራዎቹ አሁንም ድረስ በሊቀ ሊቃውንትነቱና በአዕምሯዊ ምጥቀቱ የሚነሳ ታላቅ ሰብዕና ሆኖ ይጠቀሳል፡፡
 
የሂሳብና የፊዚክስ ሊቁ አልበርት አንስታይን ከሊቅነትም በላይ በሊቀ ሊቃውትነቱ ይታወቃል፡፡
ይሄ ስሙም ዝናውም ስራውም የገዘፈ ሊቅ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የዛሬ 62 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡
 
አነስታየን ከአይሁዳዊ ቤተሰብ የተወለደው ጀርመን ውስጥ ነው፡፡
ሕፃን ተማሪ ሳለ አባቱ የአቅጣጫ ማመልከቻ የኪስ ኮምፓስ ያሳየዋል፡፡ ሕፃኑ አነስታየን መርፌ መሳይዋ የኮምፓሱ አቅጣጫ አመላካች ቀስት ወዲህ ወዲያ ስትል አስተዋለ፡፡
 
አንስታይን የአቅጣጫ አመላካቿ ወዲህ ወዲያ ማለት ያለ ምክንያት አይደለም አለ፡፡
 
ማሰላሰል መመራመሩን ተያያዘው፡፡
በወጣትነቱ በሲዊዘርላንድ በዙሪክ ፖሌቴክኒክ ኢንስቲትዩት ለማመር የመግቢያ ፈተና ወሰደ፡፡
 
አጠቃላይ ውጤቱ ወደ ተቋሙ ከሚያስገባው በታች ሆነ፡፡ ነገር ግን ፈተና ከወሰደባቸው የትምህርት አይነቶች በሂሳብና በፊዚክስ ያመጣው ውጤት በተቋሙ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ውጤት ነበር፡፡
 
አነስታይን ተቀጥሮ ያከናውናቸው ከነበሩ ስራዎች በተጓዳኝ በፊዚክስና ሂሳብ መስክ ወደ ሰፊ ጥናትና ምርምሩ ገባ፡፡
 
ከዙሪክ ዩኒቨርስቲም የዶክትሬት ዲግሪውን አገኘ፡፡
 
የአንፃራዊነት ንድፈ ኃሳብና ሌሎችም ለሳይንስ ታላቅ እርምጃ ማሳየት አሻራ ያኖሩ ስራዎቹ ዕውቅናና ክብሩን አገዘፉለት፡፡
 
ከ300 በላይ ከፍተኛ ሳይንሳዊ ዋጋ ያላቸውን የምርምርና የጥናት ፅሁፎችን አበረከተ፡፡
 
አነስታየን ስሙ ሊቀ-ሊቃውንት ለሚለው ቃል አቻ ፍቺ እስከመሆን ደረሰ፡፡
በፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሸልማት ባለክብርም ሆኗል፡፡
ከ84 ዓመት በፊት አነስታይን ወደ አሜሪካ አቀና፡፡ በአገሩ ጀርመን ናዚዎች ፖለቲካዊ ተፅዕኗቸው እየበረታ መምጣቱ ስጋቱን አበረታው፡፡ እዛው አሜሪካ ለመቅረት ወሰነ፡፡
እጆቿን ዘርግታ የተቀበለችው ታላቋ አገር ታላቁን ሰው ወዲያውኑ ዜጋዋ አደረገችው
 
አነስታይን እንደፈራው ናዚዎቹ በጥቂት ዓመታት ውስጥ የ2ኛውን የዓለም ጦርነት ማቀጣጠሉን ተያያዙት፡፡
ወደ አሜሪካ የተሰደዱ የሐንጋሪ ሊቃውንት ለዘመኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት ብርቱ ማሳሰቢያ ፃፉ፡፡
 
ማሳሰቢያውም ናዚዎቹ የኒኩሊየር ጦር መሳሪያ ባለቤት ለመሆን እየተጣደፉ መሆኑን ሹክ የሚል ነበር፡፡ በሊቃውንቱ ደብዳቤ ላይ የአነስታይንም መልዕክትና ፊርማም ማረፉ ጉዳዩ ከብዶ እንዲታይ አደረገው፡፡
ሩዝቤልት ሰምተው እንዳልሰሙ መሆን አልፈለጉም፡፡
 
አሜሪካ የማንሐተን ፕሮጄክት በመባል በሚታወቀው ውጥን ለአቶሚክ ቦምብ ባለቤትነት ፈጠነች፡፡
ከማንም አገር ቀድማ የአቶሚክ ቦምቦ ባለቤት ሆነች፡፡
 
ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተቃረበም ጊዜ አሜሪካ ቢሂሮሺማና ናጋሳኪ ላይ ቦንቦቹን ጣለቻቸው፡፡ እስከዚያ ዘመን ታይቶ የማይታወቅ ጥፋት ሆነ፡፡
 
አንስታየን ወደ ሕህወት ዘመኑ መጨረሻ ግድም አሜሪካ የአቶሚክ ቦምብ እንድትሠራ ለሩዝቬልት ደብዳቤ መፃፌን እንደ ታላቅ ስሕተት እቆጥረዋለሁ አለ፡፡ ተፀፀተ፡፡
ግን እኮ’ንም ጨመረበት፡፡
 
ይሄን እንዳብሰለሰለ ከዓመት በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
 
አልበርት አንስታይን በበዙ የሳይንሳዊ ምርምርና የጥናት ስራዎቹ አሁንም ድረስ በሊቀ ሊቃውንትነቱና በአዕምሯዊ ምጥቀቱ የሚነሳ ታላቅ ሰብዕና ሆኖ ይጠቀሳል፡፡
 
የኔነህ ከበደ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers