• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 18፣2009

ሩዝቬልትና ፖልዮ…

በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የነበሩት ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት ጥሩ ሰምና ዝና ከነበራቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች አንዱ ነበሩ፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከአጋሮቻቸው ኃያላን የአውሮፓ መሪዎች ጋር ሆነው የድል መምቻውን አዘጋጁ፡፡ በጋራ መክረውና ዘክረው ጦርነቱ በኅብረቱ ኃይሎች አሸናፊነት እንዲደመደም ያስቻሉ ናቸው፡፡

ፕሬዝዳንቱን ምንም እንኳ ዓለም አቀፍ ጀግና ሆነው ስማቸው ከአጥናፍ አጥናፍ ቢናኝም ተዋግተው ያላሸነፉት እንደልባቸው እንዳይነቀሳቀሱና እንዳይላወሱ እግራቸውን አሰሮ ያሰቀመጣቸው ጠላት ነበራቸው፡፡

ይህ ጠላታቸው ፖሊዮ የተባለው በሽታ ነው፡፡

የፖሊዮ በሽታ ተጠቂ የነበሩት እኚሁ ፕሬዝዳንት ጠላታቸው ፖሊዮ ለማጥፋት ለሚደረግ ጥረት የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት በማቋቋም ሰማቸው በቀዳሚነት ይነሳል፡፡
አሜሪካዊው የሕክምና ባለሙያ ጆናስ ሳልክ በጥረቱ የደረሰበት የመጀመሪያው የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ/ መከላከያ ክትባት ሙከራ በቬርጂኒያ ሻርመን 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረው የዛሬ 63 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

ካናዳና ፊላንድም የክትባት ፍተሻው የተካሄደባቸው ናቸው፡፡

በዓመቱ ገደማ ፍተሻው ውጤታማ እንደነበር ተመራማሪዎቹ አረጋገጡ፡፡ ይህም ለዓለም የምሥራች ሆነ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 16፣2009

እስራኤል እንደ አገር ከቆመች ወዲህ እንደ ግብፅና ሶሪያ ካሉ የአረብ አገሮች ጋር የተለያዩ ጦርነቶችና ቁርቋሶዎችን ስታደርግ ኖራለች፡፡

በተለይም ከ50 ዓመታት ገደማ በፊት የተካሄውና የስድስቱ ቀን ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው ውጊያ በታላቅነቱ ይነሣል፡፡

እስራኤል በዚህ ጦርነት የግብፅን የሲናይ ልሳነ ምድር ጨምሮ ሰፊ የአረብ ይዞታዎችን በእጇ ያስገባችበት ነበር፡፡

አይሁዳዊቱ አገር ከዚያ ወዲህ የሲናይ ልሳነ ምድርን ለግብፅ የመለሰችላት የዛሬ 35 ዓመት በዛሬዋ  ዕለት ነበር፡፡

እስራኤል ከፍልስጤማውያንና አባሪ ተባባሪ ሆነው ከተነሱባት የአረብ አገሮች ጋር ወደ ጦርነት የገባችው ከ69 ዓመታት በፊት የነፃ አገርነትዋ ከመታወጁ አስቀድሞ ነው፡፡

ነፃ አገርነትዋ ከታወጀ በኋላ ከአረቦቹ ጋር ድብልቅልቅ ያለ ጦርነት ውስጥ ገባች፡፡ በጦርነቱ በለስ ቀናት፡፡

ከ50 ዓመታት ገደማ በፊት በተፋላሚዎቹ መካከል ከባድ ጦርነት ተቀሰቀሰ፡፡

በታሪክም የስድስቱ ቀን ጦርነት በሚል ይታወቃል፡፡

በዚህ ጦርነት እስራኤል ፍልስጤማውኑን ጋዛ ሰርጥና ዌስት ባንክን፣ እንዲሁም ምስራቅ እየሩሳሌምን በእጇ አስገባች፡፡

የጎላንን ኮረብታ ከሶሪያ ነጠቀቻት፡፡

የግብፅን የሲናይ ልሳነ ምድር ተቆጣጠረችው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 13፣2009

ጄኔራል ሉዊስ ጋርሲያ ሜዛ

የደቡብ አሜሪካዋ አገር ቦሊቪያ ወደ ዴሞክራሲያዊ የአስተዳደር ዘይቤ እስከተመለሰች ድረስ አምባገነን መሪዎች ሲቀባበሏት ኖረዋል፡፡

ከ37 ዓመታት በፊት በመንግሥት ግልበጣ የአገር መሪ የሆኑት ጄኔራል ሉዊስ ጋርሲያ ሜዛ ሲጨቁኑ፣ ሲገድሉ፣ ሲዘርፉና ሲያሰቃዩ ኖረው በሰፈሩት ቁና የተሰፈሩት የዛሬ 24 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋርሲያ ሜዛን አመክሮ የሌለው የ30 ዓመት እስር ያከናነባቸው ያኔ በዚህ ቀን ነበርና፡፡

ጄኔራል ጋርሲያ ሜዛ ከ40 ዓመታት በፊት ወታደራዊ ሹመት ማዕረጋቸው በላይ በላዩ ሆነላቸው፡፡

እስከ ክፍለ ጦር አዛዥነትም ደርሰዋል፡፡

በክፍለ ጦር አዛዥነት ሳይወሰኑ ወደ አገር መሪነቱ ማማተር ጀመሩ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 12፣2009

በአጭሩ የተቀጨው የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ነገር…

ከ2ኛው የዓለም ጦርነት ባይስተካከልም ከ97 ዓመታት በፊት የተካሄደው የ1ኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ጥፋትና ውድመት አድርሷል፡፡

በጦርነቱ ሂደት ለሰላም የሚሞግትና ጥብቅና የሚቆም ዓለማዊ ድርጅት እንዲመሠረት ኃሳብ ቀረበ፡፡

ለዚህ ዓላማ የተቋቋመው ሊግ ኦፍ ኔሽንስ በአጭር የተቀጨውና ሕልውናው ያከተመው የዛሬ 71 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የ1ኛው የዓለም ጦርነት ጥፋትና ውድመት ያነቃቸው ወገኖች ስለ ሰላም የሚቆም፣ የሚከራከር፣ ለሰላም ጥበቃም ዘብ የሚቆም ዓለም አቀፍ ድርጅት እንዲቋቋም ጐተጐቱ፡፡

በ1ኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በፓሪስ በተካሄደው የሰላም ጉባዔ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ /የመንግሥታቱ ማኅበር/ ተመሠረተ፡፡

የሰላም ማኅበር ሲሉ የሚያቆላምጡትም ነበሩ፡፡

ይሁንና ብዙም ሳይዘልቅ ለዓላማው መቆም ተሳነው፡፡

ታላላቅ ጉልበተኛ አገሮች በአቅመ ደካሞቹ ላይ የግፍ ወረራ ሲፈፅሙና በማናለብኝነት ሲታበዩ ሐይ ማለት ተሳነው፡፡

ኢትዮጵያ የማኅበሩ አባል ሆና ሳለ በፋሽስቶች የግፍ ወረራ ሲፈፀምባት ላስጥልሽ ብሎ አልተነሳም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ሚያዝያ 10፣2009

የሂሳብና የፊዚክስ ሊቁ አልበርት አንስታይን ከሊቅነትም በላይ በሊቀ ሊቃውትነቱ ይታወቃል፡፡ይሄ ስሙም ዝናውም ስራውም የገዘፈ ሊቅ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የዛሬ 62 ዓመት በዛሬዋ እለት ነው፡፡አነስታየን ከአይሁዳዊ ቤተሰብ የተወለደው ጀርመን ውስጥ ነው፡፡
ሕፃን ተማሪ ሳለ አባቱ የአቅጣጫ ማመልከቻ የኪስ ኮምፓስ ያሳየዋል፡፡ ሕፃኑ አነስታየን መርፌ መሳይዋ የኮምፓሱ አቅጣጫ አመላካች ቀስት ወዲህ ወዲያ ስትል አስተዋለ፡፡
 
አንስታይን የአቅጣጫ አመላካቿ ወዲህ ወዲያ ማለት ያለ ምክንያት አይደለም አለ፡፡
 
ማሰላሰል መመራመሩን ተያያዘው፡፡
በወጣትነቱ በሲዊዘርላንድ በዙሪክ ፖሌቴክኒክ ኢንስቲትዩት ለማመር የመግቢያ ፈተና ወሰደ፡፡
 
አጠቃላይ ውጤቱ ወደ ተቋሙ ከሚያስገባው በታች ሆነ፡፡ ነገር ግን ፈተና ከወሰደባቸው የትምህርት አይነቶች በሂሳብና በፊዚክስ ያመጣው ውጤት በተቋሙ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ውጤት ነበር፡፡
 
አነስታይን ተቀጥሮ ያከናውናቸው ከነበሩ ስራዎች በተጓዳኝ በፊዚክስና ሂሳብ መስክ ወደ ሰፊ ጥናትና ምርምሩ ገባ፡፡
 
ከዙሪክ ዩኒቨርስቲም የዶክትሬት ዲግሪውን አገኘ፡፡
 
የአንፃራዊነት ንድፈ ኃሳብና ሌሎችም ለሳይንስ ታላቅ እርምጃ ማሳየት አሻራ ያኖሩ ስራዎቹ ዕውቅናና ክብሩን አገዘፉለት፡፡
 
ከ300 በላይ ከፍተኛ ሳይንሳዊ ዋጋ ያላቸውን የምርምርና የጥናት ፅሁፎችን አበረከተ፡፡
 
አነስታየን ስሙ ሊቀ-ሊቃውንት ለሚለው ቃል አቻ ፍቺ እስከመሆን ደረሰ፡፡
በፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሸልማት ባለክብርም ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Leza Vote Banner
Sheger 102.1 AudioNow Numbers