• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 10፣2009

የሆልት ነገር

ሃሮልድ ኤድዋርድ ሆልት 17ኛው የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

ሆልት በቼቪዮት የባሕር ዳርቻ በመዋኘት ላይ በነበሩበት ወቅት ሰምጠው እስከወዲያኛው ተሰወሩ፡፡ ከ3 ተከታታይ ቀናት ፍለጋ በኋላ በቃ ሆልት መሞታቸውን መቀበል አለብን የተባለው የዛሬ 49 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሃሮልድ ኤድዋርድ ሆልት በወጣትነታቸው ወቅት ከ80 ዓመታት በፊት በሕግ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመረቁ፡፡

ዘመኑ የታላቁ ዓለም አቀፍ የምጣኔ-ሐብት ምሥቅልቅል /ዘ-ግሬት ዴፕሬሽን/ ወቅት ስለነበር በተመረቁበት መሥክ ሥራ ማግኘት አልቻሉም፡፡

በዚህ ሁኔታ አስገዳጅነት በአንድ ቡና ቤት በሻይና በቡና አፍይነት ለመቀጠር ተገደዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ብዙም ሳይዘገዩ ዩናይትድ አውስትራሊያ የተሰኘውን የፖለቲካ ማኅበር ተቀላቀሉ፡፡

የፖለቲካ ማኅበራቸው ኋላ የሌብራል የፖለቲካ ፓርቲ ተሰኝቷል፡፡ ሆልት የፖለቲካ ማኅበሩን በተቀላቀሉ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በሹመት ላይ ሹመት ይነባበርላቸው ያዘ፡፡

በርካታ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በበላይነት መርተዋል፡፡

በመጨረሻም የአውሥትራሊያ የሥልጣን ጣራ ወደሆነው ጠቅላይ ሚኒስትርነትም ደርሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (2 Comments)

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 5፣2009

የባንግላዲሽ ነገር

የዛሬ 45 ዓመት የዛሬዋ ዕለት ባንግላዴሽ የተሰኘችዋን አገር ነፃነት በማረጋገጥ ረገድ ልዩ ቀን ተደርጋ ትቆጠራለች፡፡

ባንግላዴሽ በጊዜው ከጥቂት ወራት በፊት ያወጀችውን ነፃነት ለማስቀልበስ ወደ አገሪቱ የዘመቱት 90 ሺህ የፓኪስታን ጦር ወታደሮች አጃቸውን የሰጡት የዛሬ 42 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ሥር ያሣለፈችው ሕንድ ከ69 ዓመት በፊት ለነፃነት ስትበቃ ሕንድና ፓኪስታን በተባሉ ሁለት ነፃ አገሮች ተከፋፈለች፡፡

የአሁኒቱ ፓኪስታን በስተምዕራብ ሆና ዘመናዊቷ ባንግላዴሽ ደግሞ ምሥራቃዊ ማዶ ሆና በአንድ ፓኪስታን ሥር ቢጠቃለሉም በሁለንተናዊ ጉዳዮች ሥምምነት ራቃቸው፡፡

ምሥራቆቹ በምጣኔ-ሐብቱም በአስተዳዳራዊ ዕልቅናውም፣ በሹመት ድልድሉም በፖለቲካዊ ተሰሚነቱም ተበድለናል ተጨቁነናል ሲሉ ምሬት እሮሯቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡

ከ42 ዓመት በፊት ራሳችንን ከፓኪስታን ነጥለናል እሉ፡፡ ነፃ አገር መሆናቸውን አወጁ፤ አዲሲቱ አገራቸውንም ባንግላዴሽ ሲሉ ሰየሟት፡፡

ፓኪስታን ይሄ የማይሞከር ነው አለች፡፡

እጅግ ግዙፍ የሆነ ጦርና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ባንግላዴሽ አዘመተች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 4፣2009

“የታህሳሱ ግርግር” - የነብርጋዲየር ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ መፈንቅለ መንግሥት 56 ዓመት ሞላው

የኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ መኮንኖችና ተባባሪዎቻቸው የንጉስ አፄ ኃይለ-ስላሴን መንግስት ለመገልበጥ ሙከራ ካደረጉ ዛሬ 56ኛ ዓመቱን ደፈነ፡፡

የክቡር ዘበኛ ጦር አዛዥ የነበሩት ብርጋዲየር ጄኔራል መንግስቱ ነዋይና  ወንድማቸው ግርማሜ ነዋይ ዋነኞቹ  የግልበጣው ጠንሳሾች ሆኑ፡፡

ለሌሎች ተባባሪዎቻቸውንም ከጐናቸው አሠለፉ፡፡ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ኃላፊ ኰሎኔል ወርቅነህ ገበየሁና አንዳንድ ወጣት ምሁራን ዋነኛ ተባባሪና ደጋፊዎች ሆኑ፡፡

መፈንቅለ መንግስቱን የጠነሰሱት እነ ብርጋዲየር ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአፄው ስርዓተ ተብድሏል፡፡ ተረግጧል፡፡ ተጨቁኗል፡፡ ከዚህ ለመውጣትም ለውጥ ያሻዋል አሉ፡፡

ከ56 ዓመታት በፊት ንጉስ ነገስቱ አፄ ኃይለሥላሴ ለጉብኝት ወደ ብራዚል ማምራታቸውን  እነ ጄኔራል መንግስቱ ነዋይ የለውጥና የግልበጣ ውጥናቸውን ስራ ላይ ለማዋል እንደ መልካም አጋጣሚ ቆጠሩት፡፡

ታህሣስ 4/1953 ምሽት ላይ ቁልፍ ቁልፍ የንጉሱን ሹሞችና ባለሟሎችን ወደ ክብርዘበኛ ጽ/ቤት ጠርተው ሰበሰቧቸው፡፡  

ተጠሪዎቹን ሹማምንት አገቷቸው፡፡

ገልባጮቹ ያሠለፏቸው ወታደሮች የገንዘብ ሚኒስቴርን፣ የብሔራዊ ባንኩን እና  ሬዲዮ ጣቢያውን ተቆጣጠሩ፡፡

በጄኔራል መንግስቱ የሚታዘዙት የክቡር ዘበኛ ወታደሮች በከተማዋ የሚገኙ የሌሎች ክፍሎችን የጦር ሠፈሮች ከበቡ፡፡

የግልበጣው ጠንሳሾች አብዛኛውን የአዲስ አበባ ክፍል በእጃቸው እንዳስገቡ በያዟቸው በንጉሱ ልጅ አልጋወራሽ አስፋው ወሰን ድምፅ በብሔራዊ ሬዲዮ ጣቢያው በተሰራጨ መግለጫ የአፄ ኃይል ስላሴ መንግስት መወገዱ ታወጀ፡፡ አዲሱም መንግስት በአልጋ ወራሹ እንደሚመራ አሳወቁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 30፣2009

ሶቭየቶች የአቶሚክ ቦምብ ባለቤት እንዴት እንደሆኑ

አሜሪካና የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት እርስ በርስ መሰላለላቸው ከፍተኛ ነበር፡፡

ኒኩሊየራዊውን የአቶሚክ ቦምብ በመሥራት አሜሪካ ቅድምናውን ትወስዳለች፡፡

የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረትም አሜሪካን እግር በእግር በመከተል የቦምቡ ባለቤት ለመሆን ብዙ አላረፈደችም፡፡

አሜሪካን የአቶሚክ ቦምብ ባለቤት ስላደረጋት የማንሐተኑ ፕሮጄክት ለሶቪየት ኅብረት ሚስጥር ሲያሾልክ የነበረውን ግለሰብ ረድቷል የተባለው ሐሪ ጐልድ በ30 ዓመታት እሥራት እንዲቀጣ የተፈረደበት የዛሬ 65 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

አሜሪካ ወደ ዓለማችን ወታደራዊ ኃያልነቱ ስታማትር የአቶሚክ ቦንብ ባለቤትነቱ ታያት፡፡

በ2ኛው የዓለም ጦርነት ሂደት ምርምሩና የቦንቦቹ ሥራ ተጣደፈ፡፡ ተቀለጣጠፈ፡፡

ወደ ጦርነቱ ማብቂያ አሜሪካ የአቶሚክ ቦምብ ብቸኛ ባለቤትነቷን አረጋገጠች፡፡

ጦርነቱ ሊጠናቀቅ እንደተቃረበ “ብላቴናውና” “ወፍራሙ ሰው” የተሰኙ ቦንቦችን በጃፓኖቹ ሂሮሺማና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ በመጣል ከፍተኛ እልቂትና ውድመት አደረሰች፡፡

ለካ ይሄ ከመሆኑ በፊት የአቶሚክ ቦንቦች አጥፊነትም ሆነ እንዴት እንደሚሰሩ ለቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ሚስጥር አልነበሩም፡፡

እድሜ ለሰላዮቼ ብላ ስለ ማንሐተኑ የአቶሚክ ቦምብ ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ሚስጥሩን አብጠርጥራ አውቃዋለች፡፡ ሶቪየት ኅብረት የማንሐተኑን ውጥን እንዲሰልሉላት በአሜሪካ ካሰማራቻቸው እሳት የላሱ ከተፎ ሰላዮች መካከል ጃኮቭ ጐሎስ አንዱ ነበር፡፡

በኬሚስትሪ የላቦራቶሪ ባለሙያነት ሲያገለግል የነበረው ሐሪ ጐልድ ሰላይ ባይሆንም ስለ ማንሐተኑ ውጥን የሚያውቀውን ያየና የሰማውን ሁሉ ሚስጥር በቅድሚያ ለጐሎስ ከዚያም እርሱን ለተካው ሲሚዮን ሲሚዮኖቭ ዘረገፈላቸው፡፡

ሶቪየት ኅብረት በስለላ መረጃዎቹ ተረድታ የራሷንም ጥረት ጨምራበት በኒኩሊየር የጦር መሣሪያ የአሜሪካ ተፎካካሪ ለመሆን ከ5 ዓመታት የበለጠ አልጠየቃትም፡፡

ከዚያ 5 ዓመታት በኋላ ክላውስ ፌችስ የተባለ ሰላይ እንግሊዝ ውስጥ መያዙ በማንሐተኑ የስለላ ቀለበት ውስጥ የነበሩ አነፍናፊዎችም ጉድ ፈላባቸው፡፡

አንድ በአንድ እየተለቀሙ ተያዙ፡፡ የማንሐተኑ ውጥን የኬሚስትሪ የላቦራቶሪ ባለሙያ ሐሪ ጐልድ ሰላይ ባይሆንም ሚስጥሩን ለሶቪየት አነፍናፊዎች በማስታቀፉ የ30 ዓመት የእስር ቅጣት ውሣኔ የተላለፈበት የዛሬ 65 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡ የጐልድ መያዝም ሌሎች የሶቪየት ሰላዮች እንዲያዙ መንገድ መጥረጉን በተለያዩ ድርሳናት ተፅፎ ይገኛል፡፡

የኔነህ ከበደ
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 29፣2009

የእስራኤልና ፍልስጤም ነገር

ከ69 ዓመታት በፊት የፍልስጤም ምድር በእሥራኤላዊያንና በፍልስጤም አረቦች ይዞታነት ከተከፋፈለ አንስቶ አካባቢው ግጭትና ውጥረት ተለይቶት አያውቅም፡፡

ከዚያን ጊዜ አነስቶ ታላላቅ ጦርነቶች አስተናግዷል፡፡

ከጦርነቶቹም መካከል ከ49 ዓመታት በፊት የተካሄደውና በታሪክ የስድስቱ ቀን ጦርነት የተሰኘው ውጊያ አንዱ ነው፡፡

በጦርነቱ እሥራኤል አስደናቂ የተባሉ ድሎችን ተቀደጅታለች፡፡

በጊዘው በፍልስጤማውያን ይዞታነት የተከለሉትን ምስራቅ እየሩሳሌምን፣ የጋዝ ሰርጥንና ዌስት ባንክን ለመያዝ በቅታለች፡፡

ከሶሪያም የጐላን ኮረብታን ነጥቃለች፡፡ ከዚያ ወዲህ ፍልስጤማውየን እሥራኤልን በተደራጀና ባልተደራጀ ሁኔታ ሲፋለሟት፣ ሲተናነቋትና ሲገዳደሯት ቆይተዋል፡፡

ከትግል መንገዶቻቸው አንዱ የሆነውን የሲቪል እምቢታና አመፅን ያጣመረውንና የመጀመሪያውን ኢንቲፋዳ የተሰኘ ትግላቸውን የቀሰቀሱት የዛሬ 29 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ፍልስጤማውያን በተለያዩ የአስተዳደር ዘርፎች ለእሥራኤል ግብር አንከፍልም አሉ፡፡

እዚህም እዚያም በሥፋት ሥራ ማቆምን ተያያዙት፡፡ የእሥራኤልን ምርቶችና ሸቀጦችን ላለመግዛትም አደሙ፡፡ እነዚህ የኢንቲፋዳው ሰላማዊ ጐኖች ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)