• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 20፣2009

የኮርያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 858

የዛሬ 29 ዓመት በዛሬዋ እለት ከኢራቅ ባግዳድ ተነስቶ ወደ ሴኡል በማምራት ላይ የነበረው የኮሪያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 858 ወደ መዳረሻው ተቃርቧል፡፡

አብራሪው ሁለተኛው ማረፊያው ወደነበረችው ባንኮክ እንደተቃረበ በአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በሰላም እንደሚያርፍ የሬዲዮ መልዕክት ተለዋውጧል፡፡ ሁሉም ነገር አማን ነበር፡፡  አማን ሆኖ ግን አልዘለቀም፡፡

በዚያው ቅፅበት በአንዳማን ባሕር አናት ሲበር አየር ላይ ፈነዳ፡፡ ብትንትኑ ወጣ፡፡

በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ 113 ኮሪያውያንና ሁለት የሌሎች አገር ዜጐች በሙሉ አለቁ፡፡

አውሮፕላኑ በአየር ላይ ብትንትኑ የወጣው አስቀድሞ በተጠመደበት ፈንጂ ነበር፡፡

ግን ይሄን ያረገው ማን ይሆን ? ሲባል ነገሩ ወደ ሁለት ወንድና ሴት የሰሜን ኮሪያ የደህንነት ምልምሎች አመራ፡፡

ሁለቱ ኮሪያዎች ከታላቁ የኮሪያ ጦርነት አንስቶ የጐሪጥ ሲተያዩ፣ ሲጐነታተሉ ሲፎካከሩ ሲዛዛቱ ቆይተዋል፡፡

የአውሮፕላኑ ፍንዳታ ጉዳይም የሁለቱ አገሮች የባላንጣነትና የጠላትነት ቅጥያ ነበር፡፡

በጃፓን ፖስፖርት ሲዘዋወሩ የነበሩት ሰሜን ኮሪያውያን የደህንነት ምልምሎች አውሮፕላኑ በባግዳድ ሳዳም ሁሴን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳለ በትራንዚስተር ሬዲዮ ተመስሎ የተዘጋጀውን ፈንጂ በመንገደኛች እቃ ማስቀመጫ አኖሩ፡፡ ለፈንጂው ኃይል መጨመሪያ በመጠጥ አስመስለው ያዘጋጁትን ንጥረ ነገር አብረው እዛው ተው፡፡

አቡዳቢ ላይ ወረዱ፡፡ ከአቡዳቢ በአማን በኩል ወደ ሮም ለማምለጥ አሰቡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 19፣2009

የሴቶች የመምረጥና መመረጥ መብት ጉዳይ

የዛሬ 123 ዓመቷ የዛሬዋ ዕለት በዓለምም ሆነ በኒውዚላንድ ታሪክ የተለየ ቦታ አላት፡፡

የአገሪቱ ሴቶች ከወንዶች ዕኩል የሕዝብ እንደራሴዎችንና የአካባቢ ምክር ቤቶችን ተወካዮች የመምረጥ መብታቸው ስራ ላይ የዋለው የዛሬ 123 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ይህም የኒውዚላንድን ሴቶች በዘመናዊት ዓለማችን የመምረጥ መብትን በመጎናፀፍ የመጀመሪያዎቹ አድርጓቸዋል፡፡

አሁንም ድረስ በአንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ሴቶች እንደ መምረጥና መመረጥ ያሉ ፖለቲካዊ መብቶችን ተነፍገው የሚገኙትን ያህል ከ123 ዓመታት በፊት የኒውዚላንድ ሴቶችም የዚሁ ዕጣ ተጋሪ ነበሩ፡፡

ነገሩ ግን የብሪታንያ የቅኝ አገር በነበረችዋ ኒውዚላንድ የሴቶች የመምረጥ መብት የተረጋገጠው የዛሬ 123 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ቢሆንም ሴቶችን ለዚህ መብት ለማብቃት ጥረቱ የተጀመረው ከዚያ ጊዜ 20 ዓመታት ቀደም ብሎ ነው፡፡

እስከዚያን ጊዜ ድረስ ሴቶች ከማጀት አልፎ በአደባባይ ፖለቲካዊ ተግባራት መካፈል ዕድሉ አልነበራቸውም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 16፣2009

የአሜሪካ ምስረታ ጅማሮ

ከአሜሪካ ግዛቶች የነፃነት ትግል ስኬት በኋላ የመጨረሻው የብሪታንያ ቅኝ ገዢ ኃይል ወታደር ከኒውዮርክ የወጣው የዛሬ 233 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

በዘመኑ የብሪታንያ ፖርላማ በዚያ ላሰማራው ጦር ወጪ መሸፈኛው በ13ቱ የአሜሪካ የቅኝ አካባቢዎች ላይ የግብር ጫናውን አሸከማቸው፡፡

ግዛቶቹ ይሄ ከአቅማችን በላይ ነው ሲሉ አንገራገሩ፡፡

የብሪታንያ አካሎች ናችሁ እየተባልን እየተሸነገልን በፖርላማው ተገቢ ውክልና ሳይኖረን የምታሸከሙን ግብር ምን የሚሉትን ነው ብለው አምርረው ተከራከሩ፡፡ ተቃወሙ፡፡

እምቢታቸው ጉልበት እያበጀ መጣ፡፡ ለንደን ፍፁማዊ የቅኝ ገዢነት የበላይነቷን ለማፅናት ተነሳች፡፡

የማሳቹሴትሱን የራስ ገዝ አስተዳደር አፈራርሳ በጦሯ ሥር አዳሪ እንዲሆን አደረገችው፡፡

እምቢታቸውን ያበረቱት የአሜሪካ የቅኝ አካባቢዎች ብሪታንያን በብቃት ለመገዳደር እንዲያስችላቸው ኮንትኔንታል ኮንግረስ ያሉትን የጋራ ሸንጓቸውን መሠረቱ፡፡

ብቁ የሰለጠነ የጦር ኃይል አልነበራቸውም፡፡

በብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ላይ እመቢታቸው ሲያይል የሚሊሺያ ታጣቂ ጦሮቻቸውን አስታጠቁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 15፣2009

የሉሲ (ድንቅነሽ) መገኘት

በዓለም ዙሪያ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር ለመጐብኘት፣ መሬቷንም ለመርገጥ እንደ ዋና ምክንያትነት ትቆጠራለች - ሉሲ ወይም ድንቅነሽ፡፡

እማማ ሉሲ ከኢትዮጵያ ምድር እነሆ የሰው ዘር መገኛ የተባለችው የዛሬ 42 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

የመጀመሪያዋ የሰው ቅሪት አካል የሆነችው ሉሲ /ድንቅነሽ/ የተገኘችውም በአፋር ክልል ሀዳር በተባለ ቦታ ነው፡፡

የድንቅነሽ ፈላጊዎች አሰሳቸውን ያካሄዱት በስመ ጥሩ የሮክ ሙዚቃ ባንድ ዘ ቢትልስ ጆን ሌንን እና ፖል ማካርቲ የፃፉትና ያዜሙትን ዘፈን እያደመጡ ነበር፡፡

ዘፈኑም “ሉሲ ኢን ዘ ስካይ ዊዝ ዳይመንድስ” ይባላል፡፡

በዚያ የምርምር ካምፕ ሰርተው ነበርና ዘፈኑ እጅጉን ጮክ እያለ እየተመላለሰና እየተደገመ እንዲጫወት አደረጉት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ኀዳር 14፣2009

የ60 የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ባለስልጣኖችና ወታደራዊ መኰንኖች ያለፍርድ በግፍ መገደል

በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ አሰቃቂ የግፍና የግድያ ትውስታዎች ተመዝግበዋል፡፡

ነገር ግን ከዛሬ 42 ዓመታት በፊት ወታደራዊው መንግስት ደርግ በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመው ግድያ በአስቃቂነቱ በነውረኛነቱ ቀዳሚ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡

በ1967 ህዳር 14 ቀን ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ አምባገነኑ ወታደራዊ መንግስት 60 የሚሆኑ የቀድሞው መንግስት ባለስልጣኖችንና ወታደራዊ መኰንኖች ያለፍርድ በግፍ ገደላቸው፡፡

በጥቂት መኮንኖችና በአብዛኛው የበታች ሹማምንት ስብሰብ የተዋቀረው ደርግ በእጃቸው መከላከያ የሌላቸውንና በቁጥጥሩ ስር ያደረጋቸውን ባለስልጣናትና ወታደሮች ገድሎ በቀድሞው የአዲስ አበባ ወህኒ ቤት ግቢ ውስጥ በጅምላ ቀበራቸው፡፡

ደርግ የ66ቱን አመፅ በጠለፋና በአዝጋሚ ለውጥ ነጥቆ መስከረም 2 ስልጣኑን ከያዘ በኋላ አብዛኛው ታሪኩ የጭፍጨፋ ነው፡፡

የቀድሞ ባለስልጣኖች በአመፅ ግፊት ምክንያት በወታደሮች ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

አብዛኛዎቹ ሹማምንት ሃገራቸውን በጠላት ወረራ ጊዜ በአርበኝነት ደማቸውን ያፈሰሱ በዲፕሎማሲ ትግል ለሃገራቸው ክብርና ጥቅም የሰጡ፣ በሃገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ ወታደራዊ ተልዕኮ በክብር የተመሰገኑ ነበሩ፡፡

በአብዛኛው የመንግስት ፖለቲካ አስተዳደር ጨርሶ ግንዛቤ ያልነበራቸው የደርግ አባላት “ሕዝብ በድለዋል” በሚል የግል ስሜታቸው እየተነዱ አሰሩዋቸው፡፡

በባለስልጣናቱ ላይ አንዳችም ክስ አልተመሰረተባቸውም፡፡ እነሱው ከሳሽ እነሱው ፈራጅ በሆነው ስልጣናቸው የግድያ ውሳኔ ያሳለፉባቸው በዋዜማው በአንድ ቀን ስምምነት ነበር፡፡

ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሃገረ ገዥዎች የጦር ጄኔራሎች፣ ሚኒስትሮች የመገደላቸው ምክንያት የወቅቱ የደርግ ሊቀመንበር የሌተና ጄነራል አማን ሚካኤል አንዶም ማመፅና ተታኩሰው መገደላቸው ነው የሚሉ ፅሁፎች ታትመዋል፡፡

አቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤት ባቀረበው ማስረጃ ግን ግድያው እንዲፈፀም የቀደመ ዝግጅት መኖሩን አረጋግጧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)