• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 14፣2009

ቻይና እና አሜሪካ ጉዳይ

በቻይና በሊቀመንበር ማኦ ሴቱንግ የተመሩት ኮመኒስት የሸምቅ ተዋጊዎች ከ64 ዓመት በፊት የሻንጋይ ሼክን አስተዳደር ከአህጉራዊዋ  ቻይና አባረሩት፡፡

ሻንጋይ ሼክ ወደ ታይዋን በመሸሽ የቻይና ሪፖብሊክ የተሠኘውን  አስተዳደራቸውን መሠረቱ፡፡

አሜሪካ ቤጂንግ ላይ ጥርስ ነከሰችባት፡፡ ማኦ በሊቀመንበርነት ለሚመሯት  ኮሚኒስት ቻይናም እውቅና ነፍጋት ቆየች፡፡

የታይዋን አይዞሽ ባይ ሆነች፡፡

የዋሽንግተንና የቤጂንግ ግንኙነት በፍፁም ጠላትነት ተሞላ፡፡

በኮሪያ ጦርነት ወቅትም ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ወገነች አሜሪካ ደግሞ በተቀራኒው ከደቡብ ኮሪያ ጐን ተሠለፈች፡፡

በቬየትናም ጦርነት ሁለቱ አገሮች ወገንተኝነታቸው ለየቅል ሆነ፡፡

ቅራኔና ጠላትነታቸው የመረረ ሆነ፡፡ 

ከ46 ዓመታት በፊት በዛሬዋ እለት ይህን የግንኙነት ገፅታ የሚለውጥ ክስተት ተፈጠረ፡፡

የዚያን ጊዜው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን በቻይና ኦፊሴላዊ ጉብኝት ለማድረግ ቤጂንግ የገቡት የዛሬ 46 ዓመት በዛሬው እለት ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 9፣2009

ሔዝቦላ

ከመካከለኛው ምሥራቅ ስመ ገናና የጦር የፖለቲካ ድርጅቶች የሊባኖሱ ሄዝቦላህ አንዱ ነው፡፡

ሄዝቦላህ ከተመሠረተ ዛሬ 32ኛ ዓመት ሞላው፡፡

ለሄዝቦላህ መመስረት መነሻው በጊዜው እሥራኤል በሊባኖስ ላይ ያካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ነበር፡፡

አብዩ መነሻው እሥራኤል በዘመቻዋ ከያዘችው የደቡብ ሊባኖስ ግዛት ለማስወጣት የሽምቅ ውጊያ ማካሄድ አብዩ ዓላማው ነበር፡፡

በሊባኖሱ የእርስ በርስ ጦርነት ዘመን በዚያ የሰፈሩ የአሜሪካ ወታደሮችንም ለማስወጣት ግፊት ማድረግ ሌላኛው የቅርብ ግቡ እንደበር ይነሳል፡፡

እሥራኤል ደቡብ ሊባኖስን ለ18 ዓመታት ተቆጣጥራ በቆየችባቸው ጊዜያት በፊት ለፊትና በሽምቅ ተፋልሟታል፡፡

የደፈጣ ጥቃትንና መደበኛ ውጊያን ያፈራርቃል፡፡

ከበድ ከበድ ያሉ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም ከመካከለኛው ምሥራቅ ጦርና የፖለቲካ ድርጅቶች ቅድምናውን ይወስዳል፡፡

ካቱሻ የተሰኘው ሩሲያ ሰራሽ ሮኬት ማስወንጨፊያ መሣሪያ የልዩ መታወቂያው ያህል ነው፡፡ ባለ ሚሳየልም ነው፡፡

የሽምቅ ጥቃትንና የመደበኛ ውጊያን መላ ከማፈራረቅ በተጨማሪ የደፈጣ ግድያና እገታ የሚጠቀምባቸው መንገዶች ናቸው፡፡

የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃትም ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

በሺአ ማኅበረሰብ ኃይማኖታዊ መሪዎች አነሳሽነት የተመሠረተው ሄዝቦላህ ባለመንታ ክንፍ ነው፡፡

በአንድ በኩል የፖለቲካ ማህበር ሲሆን በሌላው ጐኑ የጦር ድርጅት ሆኖ ይገኛል፡፡

የሺአዎቹ አገር ኢራን ዋነኛዋ አለሁልህ ባዩ መሆኗ ይነገራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 7፣2009

የስታሊን ነገር

የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት መላ እስትንፋሷና ሕይወቷ ከኮሚኒስት የፖለቲካ ማህበሩ መልካም ፈቃድና አድራጊ ፈጣሪነት ጋር የተሳሰረ ነበር፡፡

የፖለቲካ ማህበሩ የዛሬ 61 ዓመት በዛሬዋ እለት የጀመረው ታላቅ ሸንጐ በሞት የተለየው የአገሪቱ መሪ ጆሴፍ ስታሊን ጉድ የተዘከዘከበት ሆነ፡፡

ጆሴፍ ስታሊን ከቭላድሚር ኤሊች ሊኒን ሞት በኋላ የአገር መሪነቱን ጨብጦ በፍፁማዊ አምባገነናዊ የአስተዳደር ዘይቤ አገሪቱን በብረት መዳፉ አስገብቶ  ሕዝቡን ሰጥ ለጥ አሰኝቶ ገዝቷል፡፡

የኮሚኒስት የፖለቲካ ማህበሩ ሰዎች ሳይቀሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጐች የሕዝብ ጠላት ‹‹የአብዮት ጠላት›› የሚል ቅፅል እየተለጠፈባቸው ተረሽነዋል፡፡ በየእስር ቤቱና በየግዞት ስፍራው ተወርውረዋል፡፡

በስታሊን እግር የተተኩት ኒኪታን ኩርቺየቭ ይሄ ሁሉ ሲሆን የስታሊን የቅርብ ሰውና የቀኝ እጅ ነበሩ፡፡

እሳቸውም እንደ አብዛኞቹ የስታሊን ዘመን ሹሞች ሲጠራቸው አቤት ሲልኳቸው ወዴት ነበሩ፡፡ ‹‹ስታሊን ለዘላለም ይኑርን›› ሲፈክሩ ኖረዋል፡፡

ከስታሊን ሞት በኋላ የነበረውን የስልጣን ሽኩቻ አልፈው በስታሊን ወንበር ተቀመጡ፡፡

በ20ኛው የፖለቲካ ማህበሩ አገራዊ ሸንጐ የሚታወቁ ግን ሳይነገሩ የቆዩ የስታሊንን ግፎች ዘከዘኩ፡፡

ሐጢያቱን ዘረዘሩ፡፡

በአምባገነኑ መሪ አምልኮተ ሰብ ውስጥ ወድቀን ነበር አሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 6፣2009

ጀርመን ዳግም ስትዋሃድ

ጀርመን ከ2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አጋጥሟት የነበረ የምስራቅ ምዕራብ ክፍፍል አብቅቶ ሁለቱ ጀርመኖችና አራቱ ሃያላን አገሪቱ መልሳ እንድትዋሃድ የተስማሙት የዛሬ 27 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ የጀርመን ናዚዎች ምርጥ ዝርያዎች ነን የዘሮች ሁሉ የበላይ ነን የሚል ክፉ ስሜት አደረባቸው፡፡

የጦርነት አባዜ ተጠናወታቸው፡፡

ከዓላማ ተመሳሳዮቻቸው ጋር የእብሪት ጉድኝት አደረጉ፡፡ ዓለምን በእጃችን እናስገባለን ብለው ሌሎች አገሮችን ወረሩ፡፡

የ2ኛውን የዓለም ጦርነት ቀሰቀሱ፡፡

ገደሉ፣ አሠሩ፣ ቁም ስቅል አሳዩ፡፡ ዘረፉ፡፡ አወደሙ፡፡

ብዙ ብዙ ግፍ ፈፀሙ፡፡

ናዚ ጀርመኖች በሌሎች ላይ የለኮሱት እሳት እነሱንም አነደዳቸው፡፡ አቃጠላቸው፡፡

አገራቸው በአሸናፊዎቹ የሕብረቱ ኃይሎች ሞርኮ ውስጥ ወደቀች፡፡

የሕብረቱ ኃይሎች በየፊናቸው የጀርመን ግዛት በምዕራብ ምስራቅ ከፋፍለው በተፅዕኖ ክልልነት ተቃረጡት፡፡

በአንግሎ አሜሪካና በፈረንሳይ ይዞታ ስር የቆየው የጀርመን ምዕራባዊ ግዛት የጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ተብሎ ራሱን የቻለ መንግስት ሆነ፡፡

በሶቪየቶች ስር የነበረው ምስራቃዊ የጀርመን ክፍል በፊናው የጀርመን ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ተሠኘ፡፡

አንዲት ጀርመን ለሁለት ተከፈለች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ ጥር 15፣2009

በጥፋት ተወዳዳሪ የሌለው የመሬት ነውጥ

በዓለም ላይ ለቁጥር የበዙ ርዕደ መሬቶች ደርሰዋል፡፡

በታሪክ ተመዝግበው ከሚገኙት በቻይና የደረሰውና የሻንዚው ርዕደ መሬት የሚባለው በአጥፊነታቸውና አውዳሚኒታቸው ከሚጠቀሱ የመሬት ነውጦች አንዱ ነው፡፡

የሻንዚ ርዕደ መሬት የደረሰው የዛሬ 461 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

የርዕደ መሬቱ መነሻ ስፍራ የሻንዚ ግዛት ቢሆንም ሄናን፣ ጋንሱ፣ ሻንዶንግ፣ ሁቤይ፣ ሁናን፣ ጂያንግሱና ሌሎችንም ግዛቶች መትቷል፡፡

በዘመኑ የርዕደ መሬት መለኪያ ባይኖርም ነውጡ የከባድ ከባድ እንደነበረ ይገመታል፡፡

የመስኩ ጠበብት ከአንዳንድ ቅሬት መረጃዎች በመነሳት ነውጡን በርዕደ መሬት መለኪያ 7 ነጥብ 9 እንደሚደርስ አስልተውታል፡፡

ርዕደ መሬቱ በአገሪቱ በ800 ኪሎ ሜትር መጠነ ዙሪያ ያለን ስፍራ አካሏል፡፡

ከንዝረት ማዕከሉ እስከ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ያሉ አካባቢዎች ክፉኛ ተርገፍግፈዋል፡፡

በአንዳንድ አካባቢዎችም ርዕደ መሬቱ ያስከተላቸው የመሬት መሰንጠቆች እስከ 20 ሜትር ጥልቀት ያላቸውን ገደሎች ፈጥረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers