• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 16፣2009

የጓንታናሞ ነገር

የኩባው የጓንታናሞ ቤይ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ሰፈር ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሸብር ተጠርጣሪዎች እሥር ቤትነቱ ዓለም ያውቀዋል፡፡

ቁም ስቅል ማሳያም ነው ተብሎ ስሙ በክፉ ይነሳል፡፡

አሜሪካ የጓንታናሞ ቤይን ለባሕር ኃይሏ ጦር ሰፈርነት ከኩባ በሊዝ የተከራየቻት የዛሬ 114 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ጓንታናሞ ቤይ በኩባ ደሴት ደቡባዊ ምሥራቅ ጫፍ ይገኛል፡፡

የ120 ካሬ ኪሎ ሜትር ሥፋት አለው፡፡

ለአሜሪካም ከግዛቷ ውጭ ካሉ የጦር ሰፈሮቿ በእድሜ አንጋፋው ተደርጐ ይቆጠራል፡፡

አሜሪካ ከስምምነቱ አንስቶ ለ31 ዓመታት ለጓንታናሞ ቤይ የሊዝ ኪራይ በየዓመቱ ለኩባ 2 ሺህ ዶላር ስትከፍላት ቆይታለች፡፡

ከዚያ በኋላ ዓመታዊ የሊዝ ክፍያውን ወደ 4 ሺህ ዶላር እንዳሳደገችላት በተለያዩ መረጃዎች ሰፍሮ ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 15፣2009

ዛሬ ላይ ታሪክ የሆነው የአንጎላው የእርስ በርስ ጦርነት

አንጐላ ከ40 ዓመታት በፊት በከፍተኛ ተጋድሎና ትንቅንቅ ከፖርቱጋል ነፃነቷን ብትቀዳጅም ለረጅም ጊዜ የነፃነቷን ትሩፋት ሳታጣጥም ቆይታለች፡፡

ለአንጐላ ነፃነት ድርሻ የነበራቸው ኤም.ፒ.ኤል.ኤ ና ዩኒታ የተሠኙት የጦርና የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ እርስ በርስ ቁርቋሶ የገቡት ከነፃነቱ ጊዜ አስቀድሞ ነበር፡፡

ከነፃነት በኋላ ኤም.ፒ.ኤል.ኤ በአንጐላ ፈላጭ ቆራጭ ዩኒታ ደግሞ አማፂ ቡድን ሆኖ ለ30 ዓመታት ገድማ ሲተጋተጉ ኖረዋል፡፡

አንጐላ ከአታካቹ የእርስ በርስ ጦርነት የተገላገለችው የዩኒታ አማፂ ቡድን መሪ የነበሩት ጆናስ ሳቪምቢ የዛሬ 15 ዓመት በዛሬዋ እለት ከተገደሉ በኋላ ነው፡፡

ሳቪምቢ በወጣትነት ዕድሜቸው ወደ ቻይና አቀኑ፡፡ በዚያ የቻይናን ቀይ ጦር የሽምቅ ውጊያ ስልቶች ቀስሙ፡፡

አንቱ የተሰኙ የጦር መላ አዋቂ ሆኑ፡፡ የቻይኖቹን የኮሚኒስታዊ ፍልስፍና ዝንባሌ እርግፍ አድርገው ትተው የውጊያ ስልታቸውን ብቻ ወሰዱላቸው፡፡

ሳቪምቢ የሶቪየቶች ተቀጥላ ነበር የሚባለውን የኤም. ፒ. አል. ኤን መንግስት ለመውጋት ሁነኛው ሰው ሆነው ስላገኟቸው ምዕራባዊያን አይዞዎ ከጐንዎ ነን እንደግፎታለን አሏቸው፡፡

እጃቸው ከገቡ ግዛቶች የሚያፍሱትን አልማዝ በኮንትሮባንድ እየቸበቸቡ የሽምቅ ውጊያ ቡድናቸውን ዩኒታን እስከ አፍንጫው አስታጠቁት፡፡ በአንጐላ መንግስት ወታደሮች ላይ ታላላቅ ድሎችን ጨበጡ፡፡ በአንድ ወቅት ርዕሠ ከተማዋን ሉዋንዳን እስከመክበብ ደረሱ፡፡

ጦርነቱ አሸናፊና ተሸናፊ ቢጠፋው ተፋላሚ ወገኖቹ ተኩስ አቁመን ወደ ምርጫ እንግባ ተባባሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 14፣2009

ቻይና እና አሜሪካ ጉዳይ

በቻይና በሊቀመንበር ማኦ ሴቱንግ የተመሩት ኮመኒስት የሸምቅ ተዋጊዎች ከ64 ዓመት በፊት የሻንጋይ ሼክን አስተዳደር ከአህጉራዊዋ  ቻይና አባረሩት፡፡

ሻንጋይ ሼክ ወደ ታይዋን በመሸሽ የቻይና ሪፖብሊክ የተሠኘውን  አስተዳደራቸውን መሠረቱ፡፡

አሜሪካ ቤጂንግ ላይ ጥርስ ነከሰችባት፡፡ ማኦ በሊቀመንበርነት ለሚመሯት  ኮሚኒስት ቻይናም እውቅና ነፍጋት ቆየች፡፡

የታይዋን አይዞሽ ባይ ሆነች፡፡

የዋሽንግተንና የቤጂንግ ግንኙነት በፍፁም ጠላትነት ተሞላ፡፡

በኮሪያ ጦርነት ወቅትም ቻይና ከሰሜን ኮሪያ ጋር ወገነች አሜሪካ ደግሞ በተቀራኒው ከደቡብ ኮሪያ ጐን ተሠለፈች፡፡

በቬየትናም ጦርነት ሁለቱ አገሮች ወገንተኝነታቸው ለየቅል ሆነ፡፡

ቅራኔና ጠላትነታቸው የመረረ ሆነ፡፡ 

ከ46 ዓመታት በፊት በዛሬዋ እለት ይህን የግንኙነት ገፅታ የሚለውጥ ክስተት ተፈጠረ፡፡

የዚያን ጊዜው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ኒክሰን በቻይና ኦፊሴላዊ ጉብኝት ለማድረግ ቤጂንግ የገቡት የዛሬ 46 ዓመት በዛሬው እለት ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 9፣2009

ሔዝቦላ

ከመካከለኛው ምሥራቅ ስመ ገናና የጦር የፖለቲካ ድርጅቶች የሊባኖሱ ሄዝቦላህ አንዱ ነው፡፡

ሄዝቦላህ ከተመሠረተ ዛሬ 32ኛ ዓመት ሞላው፡፡

ለሄዝቦላህ መመስረት መነሻው በጊዜው እሥራኤል በሊባኖስ ላይ ያካሄደችው ወታደራዊ ዘመቻ ነበር፡፡

አብዩ መነሻው እሥራኤል በዘመቻዋ ከያዘችው የደቡብ ሊባኖስ ግዛት ለማስወጣት የሽምቅ ውጊያ ማካሄድ አብዩ ዓላማው ነበር፡፡

በሊባኖሱ የእርስ በርስ ጦርነት ዘመን በዚያ የሰፈሩ የአሜሪካ ወታደሮችንም ለማስወጣት ግፊት ማድረግ ሌላኛው የቅርብ ግቡ እንደበር ይነሳል፡፡

እሥራኤል ደቡብ ሊባኖስን ለ18 ዓመታት ተቆጣጥራ በቆየችባቸው ጊዜያት በፊት ለፊትና በሽምቅ ተፋልሟታል፡፡

የደፈጣ ጥቃትንና መደበኛ ውጊያን ያፈራርቃል፡፡

ከበድ ከበድ ያሉ የጦር መሣሪያዎችን በመጠቀም ከመካከለኛው ምሥራቅ ጦርና የፖለቲካ ድርጅቶች ቅድምናውን ይወስዳል፡፡

ካቱሻ የተሰኘው ሩሲያ ሰራሽ ሮኬት ማስወንጨፊያ መሣሪያ የልዩ መታወቂያው ያህል ነው፡፡ ባለ ሚሳየልም ነው፡፡

የሽምቅ ጥቃትንና የመደበኛ ውጊያን መላ ከማፈራረቅ በተጨማሪ የደፈጣ ግድያና እገታ የሚጠቀምባቸው መንገዶች ናቸው፡፡

የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃትም ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይነገርለታል፡፡

በሺአ ማኅበረሰብ ኃይማኖታዊ መሪዎች አነሳሽነት የተመሠረተው ሄዝቦላህ ባለመንታ ክንፍ ነው፡፡

በአንድ በኩል የፖለቲካ ማህበር ሲሆን በሌላው ጐኑ የጦር ድርጅት ሆኖ ይገኛል፡፡

የሺአዎቹ አገር ኢራን ዋነኛዋ አለሁልህ ባዩ መሆኗ ይነገራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣የካቲት 7፣2009

የስታሊን ነገር

የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት መላ እስትንፋሷና ሕይወቷ ከኮሚኒስት የፖለቲካ ማህበሩ መልካም ፈቃድና አድራጊ ፈጣሪነት ጋር የተሳሰረ ነበር፡፡

የፖለቲካ ማህበሩ የዛሬ 61 ዓመት በዛሬዋ እለት የጀመረው ታላቅ ሸንጐ በሞት የተለየው የአገሪቱ መሪ ጆሴፍ ስታሊን ጉድ የተዘከዘከበት ሆነ፡፡

ጆሴፍ ስታሊን ከቭላድሚር ኤሊች ሊኒን ሞት በኋላ የአገር መሪነቱን ጨብጦ በፍፁማዊ አምባገነናዊ የአስተዳደር ዘይቤ አገሪቱን በብረት መዳፉ አስገብቶ  ሕዝቡን ሰጥ ለጥ አሰኝቶ ገዝቷል፡፡

የኮሚኒስት የፖለቲካ ማህበሩ ሰዎች ሳይቀሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጐች የሕዝብ ጠላት ‹‹የአብዮት ጠላት›› የሚል ቅፅል እየተለጠፈባቸው ተረሽነዋል፡፡ በየእስር ቤቱና በየግዞት ስፍራው ተወርውረዋል፡፡

በስታሊን እግር የተተኩት ኒኪታን ኩርቺየቭ ይሄ ሁሉ ሲሆን የስታሊን የቅርብ ሰውና የቀኝ እጅ ነበሩ፡፡

እሳቸውም እንደ አብዛኞቹ የስታሊን ዘመን ሹሞች ሲጠራቸው አቤት ሲልኳቸው ወዴት ነበሩ፡፡ ‹‹ስታሊን ለዘላለም ይኑርን›› ሲፈክሩ ኖረዋል፡፡

ከስታሊን ሞት በኋላ የነበረውን የስልጣን ሽኩቻ አልፈው በስታሊን ወንበር ተቀመጡ፡፡

በ20ኛው የፖለቲካ ማህበሩ አገራዊ ሸንጐ የሚታወቁ ግን ሳይነገሩ የቆዩ የስታሊንን ግፎች ዘከዘኩ፡፡

ሐጢያቱን ዘረዘሩ፡፡

በአምባገነኑ መሪ አምልኮተ ሰብ ውስጥ ወድቀን ነበር አሉ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers