• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ታሪክን የኋሊት፣ጥር 5፣2009

የዛሬ 32 ዓመት በዛሬዋ ቀን የደረሰውና የ428 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የአዋሹ የባቡር አደጋ

ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ በዘግናኝነቱ ወደር የሌለው የአዋሽ ወንዙ የባቡር አደጋ የደረሰው የዛሬ 32 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡

ለክፉ እጣ የተፃፈው የመንገደኞች ባቡር የዛሬ 32 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ከድሬዳዋ 1 ሺህ ያህል ተሣፋሪዎችን ይዞ ሲነሳ ሁሉም ነገር አማን ነበር፡፡

ባቡሩ ከድሬዳዋ ሲነሳ መዳረሻውን አዲስ አበባ በማድረግ ነው፡፡

አዋሽ ድልድይ ጋ ሲደርስ መጥፎ እጣ ገጠመው፡፡

መጠምዘዣ ኩርባ ላይ አራት ፉርጐዎች ሐዲድ ስተው ወደ ገደል ተወረወሩ፡፡

የ428 መንገደኞችን ሕይወት ቀጠፈ፡፡

ሩቅ አላሚ ቅርብ አዳሪ አደረጋቸው፡፡

በአደጋው ሕይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ 500 ያህሉ ደግሞ የተለያየ ደረጃ የአካል ጉዳት ገጠማቸው፡፡

አደጋው የደረሰው ባቡሩ በመጠምዘዣ ሥፍራ በከፍተኛ ፍጥነት ይምዘገዘግ የነበረ መሆኑ በምክንያትነት ይነሳል፡፡

የአዋሹ የባቡር አደጋ በኢትዮጵያም ሆነ በመላው አፍሪካ አቻ ያልተገኘለት መሆኑ በተለያዩ መረጃዎች ሰፍሮ ይገኛል፡፡

እስከዚያን ጊዜም ድረስ በመላ ዓለም ከደረሱት የባቡር አደጋዎች ሁሉ በ3ኛ አሰቃቂ አደጋነት ይጠቀሳል፡፡

የኔነህ ከበደ

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ጥር 3፣2009

ፔሩን ያጋጠማት የሁአስካራኑ የበረዶና የቋጥኝ ናዳ

የላቲን አሜሪካዋ አገር ፔሩ በታሪኳ በርካታ የተፈጥሮ አደጋዎች አጋጥመዋታል፡፡

አገሪቱ ከ4 ሺህ ያላነሱ ሰዎች የጨረሰው ታላቁ የሁአስካራን የበረዶ ናዳና የመሬት መንሸራተት አደጋ የደረሰባት የዛሬ 55 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

የበረዶና የድንጋይ ናዳው መነሻ የሁአስካራን ተራራ የአንድስ ሰንሰለታማ ተራሮች አካል ነው፡፡

ከባሕር ወለልም የ6 ሺህ 768 ሜትር ከፍታ አለው፡፡

አካባቢው ከታላቁ ናዳም በፊት መሰል አጋጣሚዎች ተስተውለውባት ያውቃሉ፡፡

ከ55 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ዕለት የደረሰው ግን ከተራራው ግርጌ ላሉ ከተሞችና መንደሮች ነዋሪዎች የማሰቢያ ጊዜ አልተወላቸውም፡፡

አሰቃቂውና ያልተጠበቀው ነገር በአፍታ በመሆኑ ለብዙዎቹ የግርጌ ነዋሪዎች የመሸሻና ከለላ የመፈለጊያ ሽርፍራፊ ሴኮንድ አልቸራቸውም፡፡

በተራራው ላይ የደረሰ ስንጥቃት ሁአስካራንን የሸፈነውን ግግር በረዶ ብቻ ሳይሆን አለቱንም ፈነቃቀለው፡፡

ከተራራው የበረዶና የአለት ናዳ ቁልቁል ከመንደርደሩ አስቀድሞ ታላቅ የቁጣ ዓይነት አስፈሪ ድምፅ አሰማ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (1 Comment)

ታሪክን የኋሊት፣ጥር 2፣2009

የአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት

አሜሪካ እንደ አገር ከቆመች በኋላ ከአንድ ምዕተ ዓመት ባልበለጠ ጊዜ የመበታተን ስጋት ተጋርጦባት ነበር፡፡

አንድነቷ ፈተና ላይ ወደቀ፡፡

ያኔ ባሪያ አሳዳሪነት የሰሜንና የደቡብ ግዛቶች የልዩነት መነሻ ሆነ፡፡

ባሪያ አሳዳሪነትን እንደ ልዩ ምጣኔ ሐብታዊ ጠቀሜታ ያዩት ደቡባዊ ግዛቶች ለስርዓቱ መቀጠል ሽንጣቸውን ገትረው ቆሙ፡፡

አብዛኞቹ ሰሜናዊ ግዛቶች ባርነት መወገድ አለበት አሉ፡፡

ሰባት የባሪያ አሳዳሪ ስርዓት ደጋፊ ደቡባዊ የአሜሪካ ግዛቶች አንድ በአንድ በየፊናቸው ከሕብረቱ ተነጥለናል ማለቱን ተያያዙት፡፡

ደቡባዊቷ የፍሎሪዳ ግዛት ከአሜሪካ ህብረት ተነጥዬ ራሴን የቻልኩኝ ነኝ ብላ የተለየችው የዛሬ 155 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡ 

ደቡብ ካሮላይና፣ ሚሲሲፒ፣ አላባማ፣ ሉዊዚያና፣ ጆርጂያና ቴክሳስም በተመሳሳይ የመነጠል መንገድ ተጓዙ፡፡

ባርነት መቅረት የለበትም ብለው የቆረጡ ግዛቶች ራሳቸውን ከአሜሪካ ፌዴራላዊ ህብረት በመለየት ኮንፌዴራላዊ ጥምረት ፈጠሩ፡፡ ጀፈርሰን ዴቪስን ፕሬዝዳንት፤ ማዕከላቸውን አላባማ በማድረግ የተነጠለውን ኮንፌዴራላዊ መንግስት መሠረቱ፡፡

የፀረ ባርነት አቀንቃኙ አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን የአንድነቱን ደጋፊ የሰሜን ግዛቶች አስተባብረው ለፌዴራላዊ ኅብረት በፅናት ቆሙ፡፡

መነጣጠሉ ከተጀመረ ከጥቂት ወራት በኋላ የህብረቱ ኃይሎች ይዞታ በሆነው በፎርት ሳምተር ደቡባዊያኑ ያስጮኋት ጥይት የአሜሪካ የእርስ በርስ ጦርነት ማስጀመሪያ ፊሻካ ሆነች፡፡

ከፎርት ሳምተሩ ግጭት በኋላ አርካንሳስ፣ ሰሜን ካሮላይና ቴኔሲና ቨርጂኒያ ተገንጣዮቹን ግዛቶች በመቀላቀል ኮንፌዴራሊስቶቹ አስራ አንድ ደረሱ፡፡

ልዩነቱ እየሠፋና ቅራኔው እየተካረረ መጣ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ጥር 1፣2009

የደቡብ ሱዳን ነገር…

ደቡብ ሱዳናውያን ነፃነታቸውን በወጉ ማጣጣም የሚችሉበትን ዕድል አጨናገፉት እንጂ ውድ ዋጋ የተከፈለበት ነው፡፡

2ኛው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በደቡብ ሱዳኑ የጦርና የፖለቲካ ድርጅት SPLM እና በሱዳን መንግስት መካከል አጠቃላዩ የሰላም ስምምነት የተፈረመው የዛሬ 12 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ሱዳን ከ57 ዓመታት በፊት ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ከመላቀቋ በፊት ባዕዳኑ ሰሜኑንና ደቡቡን በነጣጥለህ ግዛው የአስተዳደር ፈሊጣቸው ለያይተውት ኖሩ፡፡

ቅኝ ገዢዎቹ አገዛዛቸው ባከተመ ጊዜ የአገሪቱን ነፃነት ሲያረጋግጡ የወሳኝነቱን የአድራጊ ፈጣሪነቱን አረባዊ ዝርያ ላላቸው ሰሜናውያኑ ተዉላቸው፡፡

የፖለቲካው፣ የአስተዳደሩ፣ የምጣኔ ሐብቱ አድራጊ ፈጣሪዎቹ በዚህ ግባ በዚህ ውጣ ባዮቹ፣ አዛዥ ናዛዦቹ ሰሜናዊያኑ ሆኑ፡፡

ደቡቦቹ ተገፉ፡፡ ተገለሉ፡፡ ተንገዋለሉ፡፡ ከቅኝ ግዛት በመላቀቂያው የሽግግር ድርድር ወቅት ነገሬ አልተባሉም ነበር፡፡

በዚህም የተነሳ ከአጠቃላይዋ ሱዳን ነፃነት ውሎ ሳያድር የመጀመሪያው የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት ተካሄደ፡፡

የዚያን ጊዜውን ዕልቂት ለማስቆም በተካሄደው ድርድር ከ44 ዓመታት በፊት ተፋላሚዎቹ የአዲስ አበባውን የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ታሪክን የኋሊት፣ታህሳስ 28፣2009

እማሆይ ቴሬሳ

ትውልደ አልባንያዊቱ እማሆይ ቴሬሳ በሩህሩሕነታቸውና በሰብዓዊነታቸው ዓለማችን ከምታውቃቸው የመልካምነት ተምሳሌቶች አንዷ ናቸው፡፡

እማሆይ ቴሬሳ የደግነትና የመልካምነታቸው ጫፍ ወደታየባት ሕንድ የገቡት የዛሬ 91 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

እማሆይ ቴሬሳ በመጀመሪያ ሕንድ የገቡት በካቶሊክ ሚሲዮን መምህርነት ነበር፡፡

በሂማላያ ተራራ አቅራቢያ በሚገኝ መንደር ማስተማራቸውን ተያያዙት፡፡

በማስተማር ተግባር ተሰማርተው ወዲህ ወዲያ ሲሉ በሕንድ በተለይም በካልካታ ያስተዋሉት ይህ ከዚህ ያልተባለ ፍፁማዊ ድህነት ያስጨንቃቸው ጀመር፡፡

አይተው እንዳላዩ ማለፉ አላስቻላቸውም፡፡

የተራቡትን ለማብላት፣ የታረዙትን ለማልበስ፤ የትም ለወደቁት መጠጊያ፣ለታመሙት ጤና መሻት አለብኝ ብለው ቢያስቡም፤ በእጃቸው ሰባራ ሳንቲም አልነበራቸውም፡፡

እማሆይ ለተራቡት ጉርስ፣ ለታረዙት ልብስ ይሆን ዘንድ ከቦርሳቸው ቤሳ ቤስቲን ባይኖርም ቤት ከቤት፤ ከስፍራ ስፍራ ተዘዋውረው በምንዱባኑ ስም ይለምኑ ገቡ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers