• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ነሐሴ 24, 2005:ታሪክን የኋሊት

ነሐሴ 24, 2005

በ2ኛው የዓለም ጦርነት አቀጣጣይነት አብይ ድርሻ የነበራት ናዚ ጀርመን እጅ ከሰጠች በኋላ በጦር ማግሥት ያስተዳድራት የነበረው የኅብረቱ ኃይሎች ምክር ቤት የተቋቋመው የዛሬ 68 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡

ጀርመን እንደ 2ኛው የዓለም ጦርነት ሁሉ የ1ኛውንም የዓለም ጦርነት በማስነሳትና በማቀጣጠል የአንበሳው ድርሻ ነበራት፡፡

በ1ኛው የዓለም ጦርነት ተሸነፈች ከሽንፈቱ አልተማረችም፡፡

በሂትለር የሚመሩት ናዚዎች ዓለምን የመቆጣጠርና በሥራቸው የማሣደር ክፉ ሃሳብ አደረባቸው፡፡

የጣሊያን ፋሽስቶችንና የጃፖን ሚሊተሪስቶችን ለዚሁ የጥፋት ዓላማቸው ተጓዳኞቻቸው አደረጉ፡፡

ጦርነቱን ከአድማስ አድማስ አቀጣጠሉ፡፡

ብዙ እልቂት አደረሱ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 23, 2005:ታሪክን የኋሊት

ነሐሴ 23, 2005

የአቶሚክ ነክ የጦር መሳሪያን በእጇ በማስገባት አሜሪካ ቅድምናውን የወሰደች አገር ነች፡፡

የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረትም፣ ከአራት ዓመት በኋላ፣ የተሳካ የአቶሚክ ቦምብ ሙከራ በማድረግ በሚስጥራዊው ስያሜው ቀዳሚው መብረቅ የተሠኘውን ቦምብ፣ በተሳካ ሁኔታ የሞከረችው የዛሬ 64 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡

በ1930ዎቹ የኒኩሊየር ቅንጣቶችን በመከፋፈልና ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል በታላላቆቹ አገሮች አማካይነት ምርምሮች ተጧጧፉ፡፡

ጀርመን እንግሊዝና አሜሪካ በዚህ ረገድ ቀዳሚዎቹ ነበሩ፡፡
ምርምሩ ጥልቀት ሲያገኝ በሳይንስ ጆርናሎች ላይ የሚወጡ ፅሁፎች ደብዛቸው ጠፋ፡፡

ምርምሮቹ በሚስጥር ይያዙ ጀመር፡፡
የድብብቆሹ መበርታት፣ የሩሲያው የፊዚክስ ተመራማሪ ጊዮርጊ ፍሌየሮቭ፣ አንዳች ነገር እንዲገነግኑ አደረገ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 22, 2005:ታሪክን የኋሊት

ነሐሴ 22, 2005

የአቶሚክ ነክ የጦር መሳሪያን በእጇ በማስገባት አሜሪካ ቅድምናውን የወሰደች አገር ነች፡፡የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረትም፣ ከአራት ዓመት በኋላ፣ የተሳካ የአቶሚክ ቦምብ ሙከራ በማድረግ በሚስጥራዊው ስያሜው ቀዳሚው መብረቅ የተሠኘውን ቦምብ፣ በተሳካ ሁኔታ የሞከረችው የዛሬ 64 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡በ1930ዎቹ የኒኩሊየር ቅንጣቶችን በመከፋፈልና ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል በታላላቆቹ አገሮች አማካይነት ምርምሮች ተጧጧፉ፡፡ ጀርመን እንግሊዝና አሜሪካ በዚህ ረገድ ቀዳሚዎቹ ነበሩ፡፡ ምርምሩ ጥልቀት ሲያገኝ በሳይንስ ጆርናሎች ላይ የሚወጡ ፅሁፎች ደብዛቸው ጠፋ፡፡
ምርምሮቹ በሚስጥር ይያዙ ጀመር፡፡ የድብብቆሹ መበርታት፣ የሩሲያው የፊዚክስ ተመራማሪ ጊዮርጊ ፍሌየሮቭ፣ አንዳች ነገር እንዲገነግኑ አደረገ፡፡ ፍለየሮቭ ነገሩ፣ ወደ አቶሚክ ጦር መሳሪያ ሊያመራ እንደሚችል ገመቱ፡፡ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ሂደት፣ ለዘመኑ የሶቪየት ህብረት

መሪ ጆሴፍ ስታሊን በመስኩ ምርምር እንዲካሄድ የሚጠይቅ ደብዳቤ ፃፉ፡፡

የሶቪየት ህብረት ሲቪልና ወታደራዊ የስለላ ተቋማት በዚህ በኩል በየአገሩ ሚስጥሮችን ማነፍነፍና የአቶሚክ መሳሪያዎችን ምርምር ዱካ እግር በእግር ተከታተሉ፡፡

አሜሪካ፣ በማንሐተኑ ፕሮጄክት፣ በሎስ አላሞስ በርሃማ ስፍራ፣ የተሳካ የአቶሚክ ቦምብ ሙከራ አደረገች፡፡

ከዚህ በኋላ፣ ጥያቄው ቦምቡ እማን ላይ ይጣል? የሚል ሆነ፡፡

በአውሮፓ ግንባር የጀርመን ናዚዎች የአሜሪካ የአቶሚክ ቦምቦች ከመሞከራቸው ጥቂት ወራት በፊት እጅ መስጠታቸው በጃቸው፡፡

በእስያ ግንባር ግን ጦርነቱ ገና አልተቋጨም ነበር፡፡

የጃፓን ከተሞች ሂሮሺማና ናጋሳኪ የቦምቡ ጥፋት ገፈት ቀማሽ ሆኑ፡፡ አሠቃቂ እልቂትም ደረሰባቸው፡፡

አሜሪካ በየግንባሩ ሸንፈት በሸንፈት እየተደራረበባት በመጣው ጃፓን ላይ ይሄን አደገኛ የጦር መሳሪያ መጠቀም አልነበረባትም፤ የሚሉ አስተያየቶች ይበዛሉ፡፡

በቀዳሚዎቹም ጊዜያት፣ በዚህ ጉዳይ ያላንቀላፋችው ሶቪየት ህብረት በአንድ በኩል ስለላውን በማቀለጣጠፍ በሌላ በኩል ለአቶሚክ ምርምርና ለጦር መሳሪያው ግንባታ  ፍጥነቷን ጨመረች፡፡

ልክ የዛሬ 64 ዓመት፣ በዛሬው እለት በሚስጥራዊ ስሙ ቀዳሚው መብረቅ የተሰኘውን የአቶሚክ ቦምብ፣ ሴሚፓላቲንስክ በተባለው ስፍራ በተሳካ ሁኔታ ሞከረች፡፡

ከዚያን ጊዜ አንስቶ፣ በቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት ኃላም በሩሲያና በአሜሪካ መካከል፣ የኒኩሊየር የጦር መሳሪያ እሸቅድምድሙ አላባራም፡፡
አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 20, 2005:ታሪክን የኋሊት

ነሐሴ 20, 2005

ቅኝ ገዢዎች የአፍሪካን አገሮች በተቃረጡበት ዘመን የምዕራብ አፍሪካዋ ቶጐ ላንድ በጀርመን የአገዛዝ ሥር ወደቀች፡፡የአንጀናው የዓለም ጦርነት ሲቀሰቀስ የቅኝ አገሮችንም ማዳረሱን ያዘ፡፡የጀርመን ተቀናቃኞች የሆኑት ፈረንሳይና እንግሊዝ በጀርመን ሞግዚትነት ሥር የነበረችውን ቶጐ ላንድን ወረው የያዙት የዛሬ 99 ዓመት በዛሬዋ ዕለት ነበር፡፡የ1ኛው የዓለም ጦርነት ጀርመንና ኦስትሮ ሃንጋሪ በአንድ በኩል ፤ ከነሱ በተፃራሪ ደግሞ እንግሊዝ ፣ ፈረንሳይና ሩሲያ በሌላው ወገን በመሆን ጭፍራ ተከታዮቻቸውን አሰልፈው ተፋለሙ፡፡
በጦርነቱ የነጀርመን ወገን ተሸነፈ፡፡ የኅብረቱ ሃይሎች ድል አደረጉ፡፡ታዲያ ጦርነቱ ከአውሮፖ በተጨማሪ በሩቁ የዓለም ክፍል የቅኝ አገሮችን ጭምር ያዳረሰ ነበር፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)

ነሐሴ 16, 2005:ታሪክን የኋሊት

 ነሐሴ 16, 2005

በምድረ አሜሪካ ጥቁሮች ከቀደመው ዘመን  አንስቶ፣ በቆዳ ቀለማቸው መነሻ በባርነት፣ በዘር መድልኦና መገለል  የከፉ በደሎች እንደተፈፀሙባቸው የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ያ ሁሉ አልፎ በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በአፍሪካ አሜሪካዊው ባራክ ኦባማ ፕሬዝዳንትነት ለመመራት በቅታለች፡፡ በቀደመው ዘመን ጥቁሮች በቆዳ ቀለማቸው የተነሳ የዘር መድልኦ ሰለባዎች በነበሩባቸው ዓመታት ይሄን የዘር ግድግዳ ጥሰው አንቱ ያሠኛቸውን የክብር አክሊል የደፉት የበዙ ናቸው፡፡ ከነዚህ የበዙ አፍሪካ አሜሪካውያን ባለክብሮች፣ ዝነኛዋ የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች አልቲያ ጊብሰን አንዷ ሆና ትነሳለች፡፡

ጊብሰን፣ በዓለም አቀፍ የሜዳ ቴኒስ ፉክክር የመጀመሪያዋ ጥቁር ተወዳዳሪ የሆነችው የዛሬ 63 ዓመት በዛሬዋ እለት ነበር፡፡  

አሊሲያ፣ በደቡብ ካሊፎርኒያ ብትወለድም እድገቷ በኒውዮርክ ከተማ ነው፡፡
ገና አዳጊ ልጃገረድ ሳለች ወደ ሜዳ ቴኒስ ስፖርት አዘነበለች፡፡

በ15 ዓመቷ በአሜሪካ ቴኒስ ማህበር የበላይ ጠባቂነት በተካሄደው የሴቶች ነጠላ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ማሸነፏ የድል አንድራጊነቷን ጥርጊያ ያቀናችበት ነበር፡፡

የዛሬ 63 ዓመት፣ በኒውዮርክ ፎረስት ቢል በተካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፋ የመጀመሪያዋ ጥቁር የሜዳ ቴኒስ ተጫዋጭ ለመሆን በቃች፡፡
ከዚያ በኋላ፣ በተለያዩ ዓለም አቀፋዊነት በተላበሱ የሜዳ ቴኒስ ውድድሮች፣ የድል አዝመራዋን ሰብስባለች፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ...

አስተያየት ይፃፉ (0 አስተያየት)
Sheger 102.1 AudioNow Numbers