• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

አቤት ሆስፒታል ድንገተኛ አደጋ ገጥሟቸው ለህክምና ከሚመጡት ትራፊክ አደጋ ተጐጂዎች የበዙ ናቸው አለ

አቤት ሆስፒታል ድንገተኛ አደጋ ገጥሟቸው ለህክምና ከሚመጡት ትራፊክ አደጋ ተጐጂዎች የበዙ ናቸው አለ፡፡የሆስፒታሉ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር እስማኤል ሸምሰዲን አምና ወደ ሆስፒታላችን ከመጡት 10 ሺህ የድንገተኛ ህሙማን ብዛት ያላቸው በመኪና አደጋ የተጐዱ ነበሩ ዘንድሮም የድንገተኛ አደጋው መጠን እየጨመረ በመሆኑ ከ25-30 ሺህ ሰዎችን ለማከም ተዘጋጅተናል ብለዋል፡፡

ዶክተር እስማኤል እንደነገሩን የትራፊክ አደጋ ተጐጂዎቹ ከአዲስ አበባም ከኦሮሚያ ክልልም ወደ አቤት የሚመጡ ናቸው፡፡ አሁን ሆስፒታሉ ያለነው በኪራይ ቤት ውስጥ ስለሆነ ወደፊት 500 አልጋዎች ያሉት የራሳችን ሆስፒታል ለመገንባት በዝግጅት ላይ ነን ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡

ወንድሙ ኃይሉ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers