• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በአዲስ አበባ ከተማ ባክኖና ተደፋፍቶ የሚቀረውን 40 በመቶ ያህል ውሃ መላ ያመጡለታል የተባሉ ሙያተኞችን ከነገ ጀምሮ እንደሚያሰማራ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ተናገረ

በአዲስ አበባ ከተማ ባክኖና ተደፋፍቶ የሚቀረውን 40 በመቶ ያህል ውሃ መላ ያመጡለታል የተባሉ ሙያተኞችን ከነገ ጀምሮ እንደሚያሰማራ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ተናገረ፡፡ባለ ሥልጣኑ እንደሚለው ፤ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሲቪል ምህንድስና ሙያንና ሌሎችንም ተጓዳኝ ሙያዎች ተምረው እስካሁን ሥራ የሌላቸው ወጣቶች ተመልምለው የከተማዋን የውሀ አቅርቦት ችግር እንዲፈቱ ለስምሪት ተልከተዋል፡፡

452 ያህል ሙያተኞችን ልዩ ሥልጠና ሰጥቼ፤ በሙያቸው ተደራጅተውና ንግድ ፈቃድም አውጥተው፤ ነባር የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮችን እንዲቆፍሩ፣ ቱቦዎችን እንዲቀብሩ፣ የውሃ እክል የሚገጥማቸውን አካባቢዎችንም አጥንተው መፍትሄ እንዲያበጁ ስራውን ከፍሎ መስጠቱን ባለሥልጣኑ ተናግሯል፡፡

ተመርቀው ሥራ ያላገኙ ወጣቶችን አሰባስቦ በቆጣሪ ንባብና በመሣሰሉት ዘርፎች ሥራ ለማከፋፈል መሥሪያ ቤቱ ኃሣብ እንዳለውም ነው፤ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አወቀ ሀ/ማርያም የተናገሩት፡፡የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ውሃ የማያገኘው በተለያዩ ምክንያቶች እንደሆነ የሚናገሩት ዳይሬክተሩ ፤ እዚህ ግባ በማይባሉ የመስመር እክሎች ሣይቀር ውሃ ሣይጠፋ ውሃ የሚያጣው ብዙ ማህበረሰብ ነው ይላሉ፡፡

የዛጉና የከረሙ መስመሮችን በአዲስ መስመሮች በመቀየርና ጥቃቅን ችግሮችን በማስተካከል ባክኖ የሚቀረውን 40 በመቶ ያህል ውሃ ፍጆታ በአግባቡ ማከፋፈል እንደሚገባ መሥሪያ ቤቱ ያምናል ተብሏል፡፡በዚህ ዓመት ብቻ የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት ለ10 ሺ የከተማዋ ሥራ አጥ ነዋሪዎች ሥራ እንሚያከፋፍል ባለሥልጣኑ ተናግሯል፡፡

ሕይወት ፍሬስብሃት

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers