• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ በዚህ ዓመት ለልማት የተፈለጉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ቤቶችን አፍርሼ ለልማት ነፃ አደርጋለሁ ካለው...

የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ በዚህ ዓመት ለልማት የተፈለጉ አካባቢዎች ላይ ያሉ ቤቶችን አፍርሼ ለልማት ነፃ አደርጋለሁ ካለው 75 በመቶውን እንዳያፀዳ ምክንያት የሆኑበት ችግሮችን የሚፈታ ውሣኔ በከተማ ካቢኔው እንደተላለፈለት ተናገረ፡፡ኤጀንሲው በዚህ ዓመት 540 ሄክታር መሬት ለልማት ነፃ ለማድረግ ወጥኖ ነበር፤ ይሁንና ምትክ የቀበሌ ቤት እጥረትና በሌሎችም ምክንያቶች 360 ሄክታሩን ለሚቀጥለው አመት ነፃ ለማድረግ ማሳደሩን የኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ አቶ ግርማ ብርሃኑ ለሸገር ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባን የመልሶ ማልማት ሥራ አዘግይተዋል ለተባሉ ችግሮች መላ ይሆናሉ የተባሉ ውሣኔዎችም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መተላለፋቸውን አቶ ግርማ ነግረውናል፡፡ከአያትና ከወላጆቻቸው ተረክበው የኪራይ ውል ሣይኖራቸው በቀበሌ ቤት ለረዥም ጊዜ ሲኖሩ የቆዩ የልማት ተነሺዎች የኪራይ ውል እየተሰጣቸው ከተገኘ የቀበሌ ቤት ወይንም የከተማ አስተዳደሩ ከሚገነባቸው ደረጃቸውን የጠበቁ መጠለያዎች እንዲሰጧቸው ተወስኖላቸዋል ተብሏል፡፡

 

ከ5 ዓመት በላይ በውጭ ሀገር የሚኖሩ የቀበሌ ቤት ተከራዬችን ግን መንግሥት ቤቱን ተረክቦ ለልማት እንዲፈርስ መወሰኑን ከአቶ ግርማ ሰምተናል፡፡ለልማት ከሚፈርሱ የቀበሌ ቤቶች ነዋሪ ሆነው ኑሯቸውን ለመደጎም ወደ አረብ ሃገር ለሚሄዱት ግን ምትክ ቤት እንዲሰጣቸው ካቢኔው ወስኗል፡፡

የሊዝ ይዞታ ያላቸውና ከደረጃ በታች ስፋት ያለው የመኖሪያና የንግድ ቦታ ያላቸውን ለማስተናገድ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ ተቸግሮባቸው ከቆዩ ጉዳዮች አንዱ መሆኑን የኤጀንሲው ምክትል ኃላፊ አስታውሰዋል፡፡በመሆኑም ከ75 ካሬ ሜትር በታች የሊዝ የመኖሪያ ቦታ ያላቸው 75 ካሬ ሜትር ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸውና ልዩነቱን ግን በሊዝ መነሻ ዋጋ እንዲከፍሉ ተወስኗል ተብሏል፡፡

ለድርጅት ከ150 ካሬ ሜትር በታች የሆነ የሊዝ ይዞታ የነበራቸው ምትክ 150 ካሬ ሜትር እንዲሰጣቸውና ልዩነቱንም በአማካይ የጨረታ ዋጋ እንዲከፍሉ ልዩነቱን መክፈል አንችልም ላሉት ደግሞ በጋራ ተደራጅተው ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው በከተማው ካቢኔ ውሣኔ አግኝቷል፡፡የውሣኔ ኃሣቦቹ በዚህ አመት ፈርሰው ለልማት ነፃ ይሆናል የተባለውን 186 ሄክታር መሬት ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማድረግ ያግዛል ተብሎ ተስፋ ተደርጓል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers