• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ከፍተኛ ተቃውሞ በህዝብ ዘንድ ያስነሳው የአህያ ቄራ በአስቸኳይ እንዲዘጋ የቢሾፍቱ አስተዳደር ውሣኔ አሣለፈ

ከፍተኛ ተቃውሞ በህዝብ ዘንድ ያስነሳው የአህያ ቄራ በአስቸኳይ እንዲዘጋ የቢሾፍቱ አስተዳደር ውሣኔ አሣለፈ፡፡በ80 ሚሊዮን ብር በቢሾፍቱ ከተማ ቃጅማ ቀበሌ አካባቢ ተገንብቶ በቀን 200 ያህል አህዬችን አርዶ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ውጥን የነበረው ሻንግ ዶንግ ዶንግ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ስለገጠመው እንዲዘጋ ተወስኗል፡፡
 
የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ለዚሁ ኩባንያ ባለፈው አርብ ደብዳቤ መላኩንም ሰምተናል፡፡የከተማ አስተዳደሩን ኃላፊዎች አነጋግረን እንደተረዳነው ከኢትዮጵያዊያን ወግና ልማድ ያፈነገጠ፣ ከመነሻውም የህዝብን ድጋፍ ያላገኘ ህዝብ ተወያይቶም ይሁንታ ያልሰጠው ተግባር በመሆኑ የአህያ እርድ ማከናወኛ ቦታው በአፋጣኝ እንዲዘጋ ደብዳቤ ተልኳል፡፡ በተለይም የቃጅማ ቀበሌ ነዋሪዎች ይህ አስነዋሪ ተግባር እንዲቆም በተደጋጋሚ ለከተማ አስተዳደሩ አቤት ማለታቸውን የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሉሉ አለሙ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
 
የአካባቢው ነዋሪ ባለሃብቶቹን አልጠላም የሚሉት የከተማው ኃላፊዎች ሻንግ ዶንግ ዶንግ ýሮጀክቱን እንዲቀይር ተማፅኖውን አቅርቧል ይላሉ፡፡የአህያ እርድ አገግሎት ከመጀመሩ በፊት በተደጋጋሚ የእርድ ቦታውን ለማውደም ብዙ ጊዜ ማህበረሰቡ መቃጣቱን ኃላፊዎቹ አልደበቁም፡፡የተለያዩ ስብሰባዎች ከቢሾፍቱ ነዋሪዎች ጋር ሲካሄዱ የተቃውሞ ድምፅ ያይል እንደነበር ተናግረዋል፡ ፡በዚህ መነሻነት የህዝቡን ድጋፍ ያላገኘው፣ ባህልና እሴትን የጣሰ እንደሆነ የታመነበት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተቋቋመው የአህያ ቄራ ከሥራው እንዲታቀብ ውሣኔ ተላልፏል ነው ያሉን ያነጋገርናቸው፡፡
 
ሸገር የአህያ እርድ መከወኛ ቦታ እንዲከፈት መጀመሪያውኑ እንዴት ፈቃድ ተገኘ? የአሁኑ ውሣኔስ የሚያዛልቅ ነው ወይ? ሲል ጠይቋል በወቅቱ የነበሩ የኢንቨስትመንት አመራሮች የፈጠሩት ክፍተትና ሥህተት መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ተናግሮ ለውጭ ሀገር የኢትዮጵያን አህዬች አርዶ የማቅረቡ ሥራ ዳግም እንዳይከፈት ሆኖ ይዘጋል የሚል መልስ ሰጥቶናል፡፡ በቀን 200 አህዬችን አርዶ ስጋቸውን ለቬትናም ቆዳቸውን ደግሞ ወደ ቻይና ለመላክ በማሰብ ሥራ የጀመረው የሻንግ ዶንግ ዶንግ ኩባንያ በከተማ አስተዳደሩ ውሣኔ ላይ ያለውን ኃሣብ ለማካተት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሣካም፡፡
 
በማንኛውም አካባቢዎች ለየትኛውም የአየር ንብረት ሣይበገሩ የኢትዮጵያን ህዝብ በማገልገል የክፉ ጊዜ መወጫ ጭምር የሆኑት የኢትዮጵያ አህዬች በቁጥራቸው ከፍተኛነት ከአለም ቀዳሚውን ቦታ የዘዋል፡፡ የአሁን ጊዜ ቁጥራቸው ከ7 ሚሊዮን በላይ እንደሆነም የአህዬችን መብትና አኗኗር እንዲጠበቅ የሚሟገቱ አለም አቀፍ ድርጅቶች ይፋ አድርገዋል፡፡
 
ሕይወት ፍሬስብሃት

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers