• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ትምህርት ሚኒስቴር ወደብ ላይ ያከማቻቸው ኮንቴነሮች ለወደብ ኪራይ ብቻ ከ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ያስከፍሉታል ተባለ

ትምህርት ሚኒስቴር ወደብ ላይ ያከማቻቸው ኮንቴነሮች ለወደብ ኪራይ ብቻ ከ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ያስከፍሉታል ተባለ፡፡እስከ 4 ዓመት ድረስ በደረቅ ወደቦች ላከማቻቸው 52 ኮንቴነሮች ለወደብ አገልግሎት ከሚከፍለው በተጨማሪ ለኮንቴኔሮቹ ኪራይም ሌላ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር በዶላር ቆጥሮ መክፈል ይፈጠበቅበታል ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት ለሸገር እንደተናገረው በተለያዩ ደረቅ ወደቦች ከተከማቹ 122 የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ኮንቴኔሮች መካከል 52ቱ የትምህርት ሚኒስቴር ናቸው፡፡

እቃዎቹ ለዓመታት በመከማቻታቸውም ወደቦቹ ምርታማ መሆን አልቻሉም ብለዋል በድርጅቱ የመረጃ አያያዝና ትንተና አስተባባሪው አቶ ብሩክ ባዛ፡፡በተጨማሪም ኮንቴኔሮቹ ከወደብ ሳይነሱ እስከ አራት ዓመት በመቆየታቸው ለወደብ አገልግሎት ብቻ የትምህርት ሚኒስቴር እስከ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ቆጥሮበታል፡፡ለኮንቴነሮቹ ኪራይ ደግሞ በዶላር መክፈል ይጠበቅበታል ብለዋል አቶ ብሩክ፡፡

የውጭ ምንዛሬ እጥረት አለብኝ የምትለው ኢትዮጵያ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በቸልተኝነት በአግባቡ ከወደብ የማያነሷቸው ኮንቴነሮች  በዘገዩ ቁጥርም ተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጪ ለማድረግ እየተገደደች ነው ተብሏል፡፡በደረቅ ወደቦች ከተከማቹ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ኮንቴኔሮች መካከል ትምህርት ሚኒስቴር በኮንቴኔሮቹ ብዛት የመጀመሪያውን ቦታ ይይዛል ያሉት አቶ ብሩክ ወደቦቹም በተከማቹ እቃዎች ብዛት ምርታማ መሆን አልቻለም ብለዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር እቃዎቹን በፍጥነት እንዲያነሣም ለወደብ አገልግሎት መክፈል ያለበትን ከ6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ በዱቤ እንዲያዝለትም የኢትዮጵያ ባህር ትራስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት መወሰኑን ለሸገር ተናግሯል፡፡የትምህርት ሚኒስቴር ናቸው ከተባሉና ለዓመታት በደረቅ ወደቦች ከተከማቹ 52 ኮንቴኔሮች መካከል 22ቱ በሞጆ፣ 17ቱ በሰመራ፣ 13ቱ ደግሞ በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በውስጣቸውም የተለያዩ መፅሐፍት፣ እንደ ፒያኖ ያሉ ለትምህርት ግብዓት የሚሆኑ መሣሪያዎችና በስጦታ የተገኙ የተማሪዎች አልባሳት ይገኙበታል፡፡ወደብ ላይ አራት ዓመትን አስቆጥረዋል ከተባሉ ኮንቴኔሮች መካከል 37ቱም ትምህርት ሚኒስቴር እራሱ በግዢ ያስመጣቸው መፀሐፎች መሆናቸውን ድርጅቱ ለሸገር ተናግሯል፡፡

ትዕግሥት ዘሪሁን

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers