• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የመንግሥት ባለ በጀት መሥሪያ ቤቶች በህዝብ ገንዘብ ቅንጡ ተሽከርካሪዎችን እንዳይገዙ፣ ድል ያለ ድግስ እንዳይደግሱና...

የመንግሥት ባለ በጀት መሥሪያ ቤቶች በህዝብ ገንዘብ ቅንጡ ተሽከርካሪዎችን እንዳይገዙ፣ ድል ያለ ድግስ እንዳይደግሱና ወጪያቸውን እንዲቆጥቡ የሚያደርግ መመሪያ ተላለፈላቸው…መመሪያውን ያወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሲሆን መመሪያውን ያስተላለፈው ደግሞ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ነው፡፡

የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ሃጂ ኢብሳ እንደነገሩን ከተያዘው ወር መጀመሪያ አንስቶ ተግባራዊ ይሆናል በተባለው መመሪያ መሠረት የባለ በጀት መሥሪያ ቤቶቹ ከዚህ በኋላ የቀን መቁጠሪያ ካላንደር፣ አጀንዳ፣ መፅሔቶችን፣ የደስታ መግለጫ ካርዶችን ጨምሮ አላስፈላጊ ናቸው የተባሉ ሕትመቶችን ማሳተም አይችሉም፡፡

ከዚህ ቀደም አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት በውጭ ምንዛሬ እጅግ የተሞላቀቀ አጀንዳ በግል ስማቸው ሁሉ ያሳትሙ ነበር ያሉት አቶ ሃጂ ከእንግዲህ ግን እንዲህ  ያለው ቅብጠት አይታሰብም ነው ያሉት፡፡ከመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊዎችና የሌሎች ተቋማት ኃላፊዎች በቀር የሞባይል ካርድ ገዝቶ መሙላት የተከለከለ ሲሆን ለመካከለኛ አመራሮችና ሠራተኞችም በመደበኛ የመሥመር ስልክ በተመጣጣኝ ወጪ ይጠቀሙ ተብሏል፡፡

 

የውጭ ሀገር ጉዞም የሚፈቀደው በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ታይቶ ሲፀድቅ ብቻ ነው ያለው መመሪያው ከዚህ ውጭ በመካከለኛ አመራርና ባለሞያዎች ደረጃ የሚደረጉ የውጭ ሀገር ጉዞዎች የውጭ ጉዞውን ሊያስገኝ የሚችለውን ጠቀሜታ በአግባቡ በመገምገም የትራንስፖርትና የውሎ አበል ወጪን መቀነስም ያስፈልጋል ተብሏል፡፡ባለ በጀት መሥሪያ ቤቶች አዲስ ቢሮ መከራየት አይችሉም ሲል መመሪያው ከልክሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ተከራይተው ከፍተኛ ወጪ እየከፈሉ ያሉ መሥሪያ ቤቶችም ቢሆኑ ወጪው የሚቀንስበትን መንገድ መፈለግ እንዳለባቸውም በመመሪያው ተደንግጓል ብለዋል፡፡መመሪያው ከአዲስ ሠራተኛ ቅጥር ጋር ተያይዞ የሚያስፈልግ ቋሚ የዕቃ ግዢ ካልሆነ በቀር የቋሚ ዕቃ ግዢ ማከናወንም ክልክል ነው ብሏል፡፡

በተጨማሪም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ለሚደረጉ ስብሰባዎች ቦርሣ፣ ቲሸርት፣ ካኒቴራ፣ ኮፊያ፣ ሻርፕ፣ የባህል ልብሶችን መግዛት አይቻልም ተብሏል፡፡

ዮሐንስ የኋላወርቅ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Leza Vote Banner
Sheger 102.1 AudioNow Numbers