• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በኦሮሞያና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች ለተነሳው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ጉባዔ ሊጠራ መሆኑ ተሠማ

በኦሮሞያና በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልሎች ለተነሳው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ጉባዔ ሊጠራ መሆኑ ተሠማ፡፡በዚሁ ጉዳይ ለመምከር በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ መሪነት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሁለቱ ክልሎች አመራሮችና የፀጥታ አካላት ሲመክሩ ውለዋል፡፡

በጉባዔው ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪዎች የሚመሯቸውና የሁለቱም ክልል ሕዝቦች የሚሳተፉበት ጉባዔዎች እንዲካሄዱ የሁለቱም ክልሎች አመራሮች የግጭቱ መንስዔ የሆኑ ግለሰቦችን አጋልጠው እርምጃ እንዲወሰድ እንዲያደርጉ መስማማቱን ኢዚአ ዶክተር ነገሬ ሌንጮን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡በግጭቶቹ አካባቢዎች በተሽከርካሪዎች ላይ መስተጓጎልና ምርቶች ወደ ውጭ ለመላክ ችግር መፈጠሩን የጠቀሱት ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ከዚህ በኋላ የየትኛውም ክልል የፍትህም ሆነ የፀጥታ አካል ኬላ ላይ አቁመው እንዳይፈትሹ ታስቧል፡፡

በኬላ ፍተሻ የማድረጉን ተግባር የሚያከናውኑት የፌዴራል የፀጥታ አካላት እንዲሆኑ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡የተፈናቀሉ ዜጎችን በተመለከተ ዘላቂና ወቅታዊ መፍትሄ የሚያመጡ መላዎችን አፈላልጓል፡፡ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ተዘዋውረው የመስራት መብታቸው የተጠበቀ እንዲሆን፣ በግጭቱ የቆሰሉ ህክምና እንዲደረግላቸው፣ የተዘረፉት ንብረታቸው እንዲተካላቸውና የተፈናቀሉት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ የክልሉና የፌዴራሉ መንግሥታት እገዛ እንዲያደርጉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ስብስባ ተስማምቷል፡፡

የሁለቱም ክልሎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች በመሄድ ስጋት የገባቸው መሆኑን በመገንዘብ ለተማሪዎች ጥበቃ እንደሚደረግና ትምህርት ሚኒስቴርም የጀመረው አሰራር ስላለ ስጋት እንዳይገባቸው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ተናግረዋል ተብሏል፡፡

እሸቴ አሰፋ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers