ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች
የዛሬ ጥቅምት 28፣2010 የሸገር ወሬዎቻችን
Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.
- የስኳር ህሙማን የህመሙ ታማሚ መሆናችንን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘን መድኃኒት ለመግዛት ብንጠይቅም ከሀኪም ማዘዣ አምጡ ተብለን ተቸግረናል አሉ፡፡ መንግሥት በበኩሉ የሀኪም ማዘዣው የሚጠየቀው ለራሳቸው ለህሙማኑ ሲባል ነው ብሏል፡፡ (ንጋቱ ሙሉ)
- የአለም ወጣቶች ቀን ሰሞኑን እየተከበረ ነው፡፡ መሪ ቃሉም “መነጋገር አለብን” የሚል ነው፡፡ (ቴዎድሮስ ብርሃኑ)
- ለካንሰር የጨረራ ህክመና የሚያገለግሉ በአይነታቸው አዲስና ዘመናዊ የጨረራ መሣሪያ /ራዲዮ ቴራፒ/ ማሽኖች ተገዝተው ሃገር ቤት መግባታቸውን የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡ (ምሥክር አወል)
- የኢትዮጵያ አየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ማኅበር 28ኛውን የአፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ያካሂዳል ተባለ፡፡ (ምህረት ስዩም)
- የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፉት 3 ወራት ከቀረቡልኝ አቤቱታዎች ለ116ቱ መፍትሄ ሰጥቻለሁ አለ፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)
- የግል ትምህርት ቤቶች የመማሪያ መፃሕፍት ችግር አሁንም አልተቃለለም ተባለ፡፡ (ትዕግሥት ዘሪሁን)
- ኢትዮጵያን ጨምሮ የኢጋድ አባል አገሮች የሕገ-ወጥ የዱር እንስሳት አደንን ለመከላከል በአዲስ አበባ መላ ሊመቱ ነው፡፡ (ወንድሙ ኃይሉ)