• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የሳይንስ መረጃዎች

ልጆች ከኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ እጅጉን እየጨመረ መምጣቱ ለዓይናቸው ጤንነት ትልቅ ችግር ደቅኗል…ቢቢሲ ይዞት የወጣው ይህ ዘገባ ልጆች ከኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ጋር የሚያሳልፉትን ጊዜ ቀንሰው ከቤት ውጪ ባሉ እንቅስቃሴዎች እንዲሳተፉ ማድረጉ ለአካል ብቃት ብቻ ሳይሆን ለዓይናቸውም ጤንነት ወሳኝ ነው ይላል…

በመላው ዓለም፣ በተለይም ባደጉት ሐገራት ዘንድ፣ “ማዮፒያ” የሚሰኘው እና ራቅ ያሉ ነገሮችን በጠራ ሁኔታ ለማየት ያለመቻል የዓይን ችግር በልጆችና በወጣቶች ዘንድ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ ነው፡፡ ለዚህ ምክንያት ነው የተባለው ደግሞ እንደስማርት ስልክ፣ ኮምፕዩተር እና የመሳሰሉት ላይ ረጅም ጊዜ ማሳለፍ ነው ተብሏል፡፡

ዘገባው እንደሚለው በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ራቅ ያለ ነገሮችን በጠራ ሁኔታ ለማየት የመቸገር የዓይን እክል በልጆች ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው፡፡ ይህን ችግር ለመከላከል ወላጆች ልጆቻቸውን ከቤት ውጪ እንዲጫወቱ ማበረታታት አለባቸው ተብሏል፡፡

ችግሩ በተለይም በምስራቅ የኤስያ ሐገራት በሆኑት በሲንጋፖር፣ ታይዋን፣ እና ደቡብ ኮርያ እጅጉን የከፋ መሆኑን የሚጠቅሰው ዘገባው እድሜያቸው 18 ዓመት ከሆኑ ወጣቶች 90 ከመቶዎቹ የችግሩ ተጠቂ ናቸው ይላል፡፡ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በሌሎች የዓለም ክፍሎችም ችግሩ በአደገኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው፡፡

ለማዮፒያ ዋንኛው ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው የተፈጥሮ ብርሃን አለማግኘት ነው የሚለው ዘገባው ለዓይን ጤንነት ወሳኝ የሆኑትን እንደ አቮካዶ፣ አረንጓዴ አትክልት እና አሳ መመገብ ተመራጭ ነው ይላሉ…

 

ባለሞያዎች እንደሚሉት … ልጅዎት ወደ ቴሌቪዥን ወይም ክፍል ውስጥ በሰሌዳው ላይ የተፃፈውን ከሩቅ መመልከት እየተሳነው ቀረብ ብሎ መቀመጥ ከጀመረ፣ ራስ ምታት እና የዓይን መድከም ከታየበት … እንዲሁም በተደጋጋሚ ዓይኑን ማሸት ካበዛ ለማዮፒያ ወይም ከርቀት ለማየት የመቸገር የዓይን እክል የመጋለጥ ምልክት ሊሆን ይችላል ይላሉ…

የሆነው ሆኖ … ያደጉት ሐገራትን እያዳረሰ ያለው ችግር እኛም ዘንድ እየመጣ ነውና ልጆች ወደ ውጪ ወጥተው በተፈጥሯዊ ብርሃን እንዲጫወቱ ማደረግ ለአካልም የነፍስ ብርሃን ለሚሏት ዓይናችንም ወሳኝ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል ነው መልዕክቱ…

ሰሞኑን ከተሰሙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መረጃዎች መካከል አንዱ ደግሞ የዛሬ ወር ግድም የጠፋችውን አንዲት የራሺያን ሳተላይት ይመለከታል…

የራሺያው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ከሰሞኑ ከሐገሪቱ መንግሥት ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናገሩ እንደተባለው ለሳተላይቷ መጥፋት ዋንኛው ሰበብ ሰው ሰራሽ ነው ተብሏል፡፡

ሳተላይቷ ቤይክኑር ከተባለ የሳተላይት ማምጠቂያ ቦታ ትመጥቃለች ተብሎ ታስቦ የነበረ ሲሆን - ኋላ ላይ ግን ሳተለይቷ ከሌላ የሳተላይት ማምጠቂያ ማዕከል እንድትመጥቅ ተደረገ፡፡ ችግሩ ግን ሳተላይቷ ላይ የነበረው የኮምፕዩተር ፕሮግራም የተቃኘው ከመጀመሪያው ማምጠቂያ ቦታ እንደምትመጥቅ ታስቦ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ - በዚህ ስህተት ታቢያ 58 ሚሊየን ዶላር የምታወጣው የዓየር ንብረት መከታተያ ሳተለይት የሕዋ ሲሳይ ሆና በጥልቁ ሕዋ ጠፍታ መቅረቷን ተናግረዋል፡፡

ከዚህች የራሺያ ሳተላይት ጋር አብረው የመጠቁ ንብረትነታቸው የሌሎች ሐገራት የሆኑ 18 ሳተላይቶችም ጠፍተው መቅረታቸው በራሺያ የሕዋ ቴክኖሎጂ ተቋም ላይ ትልቅ ወቀሳ አድርሶበታል…

በተያያዘ መረጃ … ለጥቂት ቀናት ጠፍታ የከረመችው እና ራሺያ ለአንጎላ አምጥቃት የነበረችው የአንጎላዋ ሳተላይት መገኘቷ ተሰምቷል፡፡

የራሺያዎቹ ሳይንቲስቶች ለቀናት ግንኙነቷ ተቋርጦ ከነበረው ሳተላይት ጋር ግንኙነት መፍጠር መቻላቸውን የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ባለፈው ማክሰኞ ራሺያ ለአንጎላ ያመጠቀችላት Angosat-1 የተባለችው ይህች ሳተላይት የአንጎላን የኢንተርኔት፣ የሞባይል፣ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭት ታፋጥናለች ተብላ ታላቅ ተስፋ የተጣለባት ነች፡፡

ወዲያው እንደመጠቀች ግንኙነቷ ተቋርጦ የነበረው ይህች ሳተላይት ለአንጎላውያን የብሄራዊ ኩራት ምንጭ ሁሉ ሆናለች ነው የተባለው፡፡

የሳተላይቷ ፕሮጀክት የተጀመረው እ.ጎ.አ በ2009 ሲሆን ከ286 ሚሊየን ዮሮ በላይ የፈሰሰባት ሳተላይት ነች፡፡

ሳተላይቷ ለ15 ዓመታት ያህል ታገለግላለች ተብሎ ተስፋ ተጥሎባታል፡፡
ጠፍተው የቀሩት 19 ሳተላይቶች እና የዚህች ለቀናት ያለችበት ጠፍቶ የነበረችው ሳተላይት ጉዳይ ለራሺያ የሕዋ ቴክኖሎጂው ተቋም ትልቅ ሐፍረት ሆኖበታል ነው የተባለው፡፡

ይህንኑም ተከትሎ የራሺያ መንግሥት ጉዳዮን እጄን አጣጥፌ አላየውም አጣራለሁ ማለቱ ተነግሯል…

ግሩም ተበጀ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers