• Slider One

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበዓሉ ዋዜማ ከፍተኛ ሀይል ከሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ጋር ተነጋገሬ ሀይል እንዳይጠቀሙ ላደርግ እችላለሁ አለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበዓሉ ዋዜማ ከፍተኛ ሀይል ከሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች ጋር ተነጋገሬ ሀይል እንዳይጠቀሙ ላደርግ እችላለሁ አለ፡፡በበአሉ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሀይል መቆራረጦችን አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥ አገር አቀፍ የጋራ ግብረ ሀይል አቋቁሜአለሁ ብሏል፡፡ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሶችን ጨምሮ የጥገናና የቴክኒክ ሠራተኞች እንዲሁም አመራሮችም በስራ ላይ ይሰማራሉ ተብሏል፡፡

ከፍተኛ የኤሌትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ከሆኑ የሲሚንቶና የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጋር ተነጋግሬ በዋዜማው ሀይል መጠቀም እንዲያቋርጡ ላደረግ እችላለሁ ያለው አገልግሎት ሰጪው መስሪያ ቤት ሌሎች መካከለኛ ሀይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎችም በበአሉ ዋዜማና እለት የተለመደውን ትብብር ጠይቋል፡፡

ሌሎች ደንበኞችም ለበአል ዝግጅት ከቀን ይልቅ በለሊት ብትጠቀሙ የተሻለ ሀይል ማግኘት ትችላላችሁ ብሏል፡፡ከኋይል መቋራረጥና ሌሎች ማንኛውም ከኤሌክትሪክ ጋር ለተገናኙ መረጃዎች በነፃ ስልክ መስመራችን 905 ደውሉልን ሲል አገልግሎት ሰጪው መስሪያ ቤት ነግራችኋል፡፡

አስፋው ስለሺ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers