• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የሸገር የሳይንስ ወሬዎች፦ጠፈረተኛ አላን ቢን

ጨረቃን በመርገጥ 4ኛው ሰው የሆነው አሜሪካዊው ጠፈረተኛ አላን ቢን በ86 ዓመቱ አረፈ፡፡በኋለኛው ሕይወቱ የተዋጣለት ሰዓሊ የሆነው አላን ቢን የሥዕል ሥራዎቹ መነሻ የሕዋ ጉዞው ነበር፡፡ከሁለት ሳምንታት በፊት መታመሙን የተናገሩት ቤተሰቦቹ ሀውስተን ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል በሰላም ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡

በሁለት የጠፈር ጉዞዎች ላይ ተጓዥ የነበረው ጠፈረተኛ ማይክ ማሲሚኖ ባልደረባው የነበረውን አላን ቢንን አስመልክቶ ሲናገር፣ “በሕይወቴ ካጋጠሙኝ አስደናቂ ሰዎች አንዱ ነው … የቴክኒክ ብቃት እና የኪነጥበብ ተሰጥኦ የታደለ ታላቅ ሰው ነበር” ብሏል፡፡የአሜሪካ ባህር ሃይል የሙከራ አብራሪ የነበረው አላን ቢን ናሳን የተቀላቀለው እ.ጎ.አ በ1963 ነበር፡፡

ወደ ሕዋ ሁለት ጊዜ የተጓዘው አላን ቢን ጨረቃን የረገጠው በመጀመሪው ጉዞው ወቅት እ.ጎ.አ በሕዳር 1969 ነበር፡፡

ከዚያ ደግሞ እ.ጎ.አ በ1973 ስካይላብ ትሰኝ ወደነበረችው የአሜሪካ የመጀመሪያ የሕዋ ጣቢያ ተጉዟል፡፡

ጠፈረተኛው በ1981 ከናሳ ጡረታ ከወጣ በኋላ የተሳካለት ሰዓሊ ለመሆን ችሏል፡፡
ከአላን ቀድመው ጨረቃን የረገጡት 3 ጠፈረተኞች ሲሆኑ እነሱም በሐምሌ 1969 በተካሄድ የአፖሎ 11 ተልእኮ ወቅት ጨረቃን የረገጡት ኒል አርምስትሮንግ እና በዝ አልድሪን እንዲሁም በአፖሎ 12 ተልእኮ ወቅት አብሮት ወደ ጨረቃ የተጓዘው ቻርለስ ኮንራድ ነው፡፡

ከአራቱ አሁን ላይ በሕይወት የሚገኘው የ88 ዓመቱ በዝ አልድሪን ነው፡፡

በአጠቃላይ 24 ሰዎች ወደ ጨረቃ ተጉዘው 12ቱ ጨረቃን ረግጠዋል፡፡

በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በፈረንሳይ አንድ ሚሊየን አጫሾች ሲጋራ ማጨስ ማቆማቸው ተሰማ…

ጥናቱን ያካሄደው የፈረንሳይ የማህበረሰብ ጤና ተቋም “ይህን ያህል ትልቅ የአጫሽ ቁጥር መቀነስ በአስር አመታት ውስጥ ያልታየ ነው” ብሏል፡፡

ጥናቱ እንዳሳየው በለጋ ወጣቶች እና አነስተኛ ገቢ ባላቸው ሰዎች ዘንድ ማጨስ ቀንሷል፡፡

ለተገኘው ውጤት ሰበቡ የሲጋር ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ፣ ሲጋራ የማይጤስበት ወር የተሰኘው ዘመቻ እና መሰል እርምጃዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት የተሰራ አንድ ጥናት፣ ምንም እንኳ በመላው ዓለም ሲጋራ አጫሽነትን ለመቆጣጠር እርምጃዎች ቢወሰዱም በሕዝብ ቁጥር መጨመር ሳቢያ የአጫሾች ቁጥር እንዲጨምር ሆኗል ይላል፡፡

በዓለማችን ከሚከሰቱ 10 ሞቶች የአንዱ ሰበብ ሲጋራ ማጤስ ሲሆን ከዚህም ውሰጥ ግማሹ በአራት የዓለማችን ሐገራት - ቻይና፣ ሕንድ፣ አሜሪካ እና ራሺያ የሚከሰት ነው፡፡

አጫሽነትን አስመልከቶ የተሰራ አንድ ጥናት ደግሞ “የአጫሽነት ወረርሽኝ ከሐብታም ሐገራት ወደ መካከለኛ ገቢ እና ዝቅተኛ ገቢ ሐገራት እየተዛወረ ነው” ሲል አስጠንቅቋል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ እንደሚለው በየዓመቱ ከ7 ሚሊየን በላይ ሰዎች በሲጋራ ሳቢያ ይሞታሉ፡፡ ከዚህም ውስጥ ከ6 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ሲጋራን በማጨስ ሳቢያ ሲሆን 890 ሺ ያህሉ ደግሞ አጭሰው ሳይሆን በሚጨስበት አካባቢ በመሆናቸው ብቻ ነው ይላል፡፡

ከዓለማችን 1.1 ቢሊየን ያህል አጫሾች 80 ከመቶ ያህሉ የሚገኙት በዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሐገራት ነው፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለው፣ በተለይም በሲጋራ ፓኬቶች ላይ የሚኖር በምስል የተደፈ የሲጋራን ጎጂነት የሚያሳይ ማስጠንቀቂያ አጫሾች ማጨስ እንዲያቆሙ እጅጉን ይረዳል ባይ ነው፡፡

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers