• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ / እና የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር / ኦዴግ / ትናንት አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት አድርገዋል

ውይይቱ የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም ሁለቱ በጋራ በሚሰሩበት መንገድ ላይ ያተኮረ እንደነበር የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ /ኦ ቢ ኤን/ መረጃ ጠቅሷል፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደ ውይይት ነውም ብሏል፡፡
የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሣ የኦዴግ መሪዎችን እንኳን ወደ ሀገራችሁ በደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል፡፡ተቀራርቦ መስራቱ ከሌሎች የኦሮሞ የፖለቲካ ሃይሎች ጋርም እንደሚቀጥል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

ውይይቱ በጥላቻ ላይ ተመስርቶ የቆየውን የፖለቲካ ባህል የሚቀይር ነውም ብለዋል፡፡ለኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር /ኦዴግ/ አመራሮች በግላቸው ከፍ ያለ አክብሮት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር ፕሬዝዳንት አቶ ሌንጮ ለታ በበኩላቸው ወደ ሀገር ቤት እንዲለመሱ በኦሮሚያ ክልል እና በፌዴራል መንግስት ለተደረገላቸው ዕገዛ አመስግነዋል፡፡

በሀገሪቱ እየመጣ ባለው ለውጥ ውስጥ የራሳችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት መጥተናል ሲሉም አቶ ሌንጮ ተናግረዋል፡፡የኦዴግ አመራሮች በመንግስት የቀረበላቸውን የድርድር ግብዣ በመቀበል በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers