ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች
በአርባ ምንጭ አባያ ሐይቅ ትናንት ሰዎችን በማጥመቅ ላይ የነበረ ግለሰብ በአዞ ተበልቶ ሕይወቱን አጣ
ከነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ ሀላፊ ከአቶ ሽመልስ ዘነበ ዛሬ እንደሰማነው ተከታዮቹ ፓስተር እያሉ የሚጠሩት የ45 አመቱ ጎልማሳ ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ በአባያ ሐይቅ ውስጥ ገብቶ ሰዎችን በማጥመቅ ላይ ሳለ ነው በአዞ ተበልቶ ሕይወቱን ያጣው ብለዋል፡፡
የአባያ ሐይቅ ብዛት ያላቸው አዞዎች መኖሪያ ሲሆን የዓሣ ሀብት ስለሌለው በውስጡ የሚገኙት አዞዎችም የምግብ እጥረት ስለሚያጋጥማቸው ያገኙትን ነገር ሁሉ ይመገባሉ ያሉት የብሔራዊ ፓርኩ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ከዚህ ቀደምም የሜዳ አህዮች፣ አጋዘኖች እና ብዛት ያላቸው የቤት እንስሳት ውሃ ለመጠጣት ወደ አባያ ሐይቅ እየቀረቡ በአዞ ተበልተዋል ሲሉም ነግረውናል፡፡ሰዎችን በማጥመቅ ላይ ሳለ አዞ የበላው ግሰለብ ከዚህ ቀደም በዓሣ አጥማጅነት ይተዳደር ነበር ተብሏል፡፡
ወንድሙ ኃይሉ