• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በዘንድሮው በጀት ዓመት ከታክስ ገቢ ከሃምሳ ቢሊየን ብር በላይ ሳይሰበሰብ ሊቀር ይችላል ተባለ

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በ2011 የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት አድርጓል።የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም ተከሰተ ስለ ረቂቅ በጀት በምክር ቤቱ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
በመንግስት በጀት አፈጻጸም ረገድ በ2010 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የነበረውን የታክስ አሰባሰብም ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።እሳቸው እንዳሉት በጠዘኝ ወራቱ ከታክስ ፤ ታከስ ካልሆኑ ገቢዎችና ከውጭ ቀጥታ በጀት ድጋፍ 140 ቢሊየን ብር የፌዴራል መንግስት ገቢ ተሰብስቧል።
 
የተሰበሰበው ገቢ ለአጠቃላይ የበጀት ዓመቱ ከተያዘው ዕቅድ 58 ነጥብ 8 በመቶ ነው ብለዋል።አፈጻጸሙ ከባለፉት ዓመታት በተለየ ሁኔታ እጅግ ደካማ እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።ከሃምሳ ቢሊየን ብር በላይ ታክስ ሳይሰበሰብ ሊቀር ይችላልም ብለዋል፤እንደ ዶክተር አብረሃም - የታክስ አሰባሰቡ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን በመንግስት ወጪ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል፤የወጪ ንግድ አፈጻጸምም በዓመቱ መሰረታዊ ለውጥ አለማሳየቱን ተናግረዋል።
 
ለ2011 የተያዘው የታክስ ገቢ ግምት ከ2010 ጋግ ሲነጻጸር በጣም የተለጠጠ እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፤ዕቅዱ የታክስ አስተዳደሩን በልዩ ሁኔታ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።ግብር ከፋዮችም ለበጀት ዓመቱ የተያዘው የታክስ ገቢ ተሟልቶ እንዲሰበሰብ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፤የ2011 አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር እንዲሆን በረቂቁ ቀርቧል።
 
ከ2010 በጀት ዓመት በ12 ነጥብ 1 ብልጫ ያለው እንደሆነም ተነግሯል።ከበጀቱ 91 ነጥብ 7 ቢሊየን ብሩ ለመደበኛ ወጪዎች የተያዘ ሲሆን ፤ ለካፒታል ወጪዎች ደግሞ ብር 113 ነጥብ 6 ቢሊየን ተይዟል።ለክልል መንግስታት ድጋፍም 135 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የተመደበ ሲሆን ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያም ስድስት ቢሊየን ብር ተመድቧል።
 
ከአጠቃላይ የ2011 መደበኛ እና ካፒታል በጀት ውስጥ 66 በመቶው ለትምህርት ፤ መንገድ ፤ ግብርናና ገጠር ልማት ውሃ ፤ ጤና ፤ ኢንዱስትሪ ፤ ከተማ ልማት ፤ የከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራሞች የተመደበ መሆኑ ተነግሯል።
 
በአጠቃላይ በ2011 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ከሀገር ውስጥ የገቢ ምንጮች ፤እንዲሁም ከውጪ ዕርዳታ እና ብድር 287 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር -ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ሚኒስትሩ ዶክተር አብረሃም ተናግረዋል፤በታቀደው የፌዴራል ገቢ እና የወጪ በጀት መካከል የብር 59 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ጉድለት አለ ብለዋል፤ጉድለቱን ከሀገር ውስጥ ከሚገኝ ብድር ለመሸፈን መታሰቡን ተናግረዋል፤የሀገር ውስጥ ብድር መጠኑ ከአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንፃር 2 ነጥብ 3 በመቶ ነው ተብሏል።
 
ንጋቱ ረጋሣ
 
 

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers