• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በመጪው ሰኔ 30 ቀን 2010 የስልጣን ጊዜው የሚያበቃውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዲስ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ...

በመጪው ሰኔ 30 ቀን 2010 የስልጣን ጊዜው የሚያበቃውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዲስ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም የከተማዋን ቻርተር አዋጅ እንዲሻሻል ረቂቅ ቀርቦበት ዛሬ በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ተመክሮበታል፡፡

በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሳይከናወን የቀረውና የስራ ዘመኑ በመጪው ሰኔ 30 ቀን 2010 የሚያበቃው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምርጫ ባለመካሄዱ የምክር ቤቱ ሕጋዊነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል ተብሏል፡፡የምክር ቤቱና የስራ አስፈፃሚው አካል ሌላ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስም አሁን ባሉት አባላትና አካሄድ መቆየት እንዲችል የማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተነግሯል፡፡በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የሚመረጥበትንም ድንጋጌ ማሻሻያ እንዲደረግበት ሀሳብ ተካቶበታል፡፡

ምክትል ከንቲባ የሚመረጠው ከምክር ቤቱ አባል ብቻ መሆን አለበት የሚለው አሰራር ለቦታው ተገቢ የሆነና ብቃት ያለው ሰው ከምክር ቤቱ ውጪ ሊገኝ ስለሚችል ከምክር ቤት አባል ውጪ የሆነ ምክትል ከንቲባ እንዲሾምና ስራውም በአግባቡ እንዲሰራ ረቂቁም ማሻሻያ እንዲደረግበት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቧል ተብሏል፡፡ምክር ቤቱ የተሻሻለውን የከተማ አስተዳደሩም ቻርተር አዋጅ ለማሻሻል የወጣውን ረቂቅ ለዝርዝር እይታ ለሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርጧል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ የስደተኞች ጉዳይ ረቂቅ አዋጅም ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የመራ ሲሆን የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሥነ ምግባር ግድፈት አግኝቼባቸዋለሁ ባለቸው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞች ላይ ያሳለፈውን የስንብት ውሳኔ ለማፅደቅ ምክክር እያደረገ ነው፡፡

ምህረት ስዩም

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers