• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በጌድዮ እና ጉጂ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎችን ሁኔታ የሚያጠና የልዑካን ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ መላኩ ተሠማ

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን እና ደቡብ ክልል ጌድዮ ዞን አዋሳኝ አካባቢ ያሉ ዜጎች በስብጥር ይኖራሉ፡፡ በአካባቢው የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ግን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በዶንጎሬ ባህላዊ ስነ ስርዓት ዕርቅ ከተፈጸመ በኋላ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀዬቻቸው ተመልሰው እንደነበር - በፌዴራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስቴር የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ዘላቂ መፍትሄ ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ንጋቱ አብዲሣ አስታውሰዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ወደ ቀዬያቸው ከተመለሱ በኋላም ግን ሌላ ግጭት ተከስቶ ዳግም መፈናቀል አጋጥሟል ብለዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም የልዑካን ቡድን ለሶስተኛ ጊዜ ወደ አካባቢው እንደተላከ ከአቶ ንጋቱ ሠምተናል፡፡ ቡድኑ ተፈናቃዮቹን ሊያጋጥም የሚችል የጤና ችግር አለ ወይስ የለም የሚለውን ይገመግማል ብለዋል፡፡ ቡድኑ ፍትሃዊ የዕርዳታ ክፍፍል ስለመኖሩ እንዲሁም በግጭቱ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው ሰዎች ወደ ህግ ስለሚቀርቡበት መንገድም ያጣራል ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት የተላኩት ሁለት የልዑካን ቡድኖች ስለ ግጭቱ መንስኤ እና ተፈናቃዮቹ ስላሉበት ሁኔታ አጣርቶ እንደተመለሰ ዳይሬክተር ጄኔራሉ ነግረውናል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers