• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ለአጥንት ህክምና ወደ ተለያዩ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እየቀነሰ ነው ተባለ

ለአጥንት ህክምና ወደ ተለያዩ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እየቀነሰ ነው ተባለ፡፡ምክንያቱ ህክምናው በአገር ውስጥ ለመስጠት ፈተና ሆኖ የቆየው የመሳሪያዎች እጥረት እየተቃለለ መሆኑ ተነግሯል፡፡ አሁን ግን እነዚህ መሳሪያዎች በብዛት ተገዝተው ወደ አገር ውስጥ እየገቡ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ የአጥንት ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብሩክ ላምቢሶ ተናግረዋል፡፡

በህክምናው የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች በአገር ውስጥ እንዲመረቱ ጥረቶች ተጀምረዋል ብለዋል፡፡መሳሪያዎቹ ከተሟሉ ያሉት ባለሙያዎች ህክምናውን በአገር ውስጥ መስጠት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ይህም ሰዎች ቤትና መኪናቸውን ጭምር በመሸጥ ለህክምናው ወደ ተለያዩ አገራት የሚሄዱበትን አሰራር ይቀንሰዋል ብለዋል፡፡በቅርቡ በተፈፀመው የቦምብ ጥቃት የተጎዱና በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች የቆሰሉ ዜጎችን ለመርዳት የማህበሩ አባላት ከፍተኛ ሙያዊ እገዛ ማድረጋቸውንም ሰምተናል፡፡የኢትዮጵያ የአጥንት ህክምና ባለሙያዎች ማህበር 13ኛ አመታዊ ጉባኤው በሸራተን አዲስ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት መስጠት በሚቻልበት መንገድ ላይ ውይይት ተደርጎ ውሳኔ ላይ እንደሚደረስ ዶክተር ቡሩክ ተናግረዋል፡፡በቅርቡ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶችና እዚህ አዲስ አበባ በነበረው የቦምብ አደጋ የተጎዱ ዜጎችን በመርዳት ግንባር ቀደም ተሳትፎ አሳይተዋል የተባሉ አባላቱንም ማህበሩ በጉባኤው ላይ ሸልሟል፡፡

ንጋቱ ረጋሳ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers