• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በአከራዮችና ተከራዮች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ያስቀራል ያለውን የቤት አስተዳደር አዋጅ ማዘጋጀቱን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስቴር ተናገረ

በአከራዮችና ተከራዮች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ያስቀራል ያለውን የቤት አስተዳደር አዋጅ ማዘጋጀቱን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስቴር ተናገረ፡፡ሚንስትሩ ረቂቅ አዋጁን ለሚንስትሮች ምክር ቤት መላኩን ሰምተናል፡፡የከተማ ልማትና ቤቶች ሚንስትሩ አቶ ዣንጥራር አባይ እንደተናገሩት ከሆነ አዋጁ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ከነዋሪዎች ጋር ውይይት የሚያደርግበት መሆኑን አቶ ዣንጥራር ተናግረዋል፡፡አዋጁ የቤት ልማትና የግብይት ስርዓት እንዲሁም አከራይ ከተከራይ ጋር ሊይዛቸው ስለሚገቡ ውሎች የተካተተበት ነው ብለዋል፡፡ስለቤቶች ደረጃና የኪራይ ክፍያቸው መጠን በአዋጁ ስለመካተቱ የተጠየቁት አቶ ዣንጥራር አከራዮች በፈለጉበት ወቅት ያከራዩትን ቤት ልቀቁ እንዳይሉ የሚከለክል እንጂ የቤቶች የኪራይ ተመንን አያካትትም ብለዋል፡፡

በየነ ወልዴ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers