ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች
በዛሬው ዕለት በቤተ መንግሥት አካባቢ የሆነውን በተመለከተ…ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ዛሬ ውይይቱን ያካሄዱት ለተለያየ የፀጥታ ማስከበር ተግባር በአዲስ አበባ ዙሪያ የነበሩ የልዩ ኃይል አባላት መሆናቸው ተነግሯል
በዛሬው ዕለት በቤተ መንግሥት አካባቢ የሆነውን በተመለከተ…ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ዛሬ ውይይቱን ያካሄዱት ለተለያየ የፀጥታ ማስከበር ተግባር በአዲስ አበባ ዙሪያ የነበሩ የልዩ ኃይል አባላት መሆናቸው ተነግሯል፡፡ የልዩ ኃይል አባላቱ ወደ ካምፓቸው ከመመለሳቸው በፊት በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየት እንፈልጋለን ማለታቸው ተነግሯል፡፡በውይይቱ ላይም በዘላቂነት ህይወታቸውን የሚመሩበት ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል ተብሏል፡፡ በተቋማቸው ውስጥ ያሉ የአሰራር ክፍተቶች እንዲፈተሹ መጠየቃቸውም ተነግሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በበኩላቸው የደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ቢነሳም ዘላቂ ምላሽ የሚያገኘው በጥናት ላይ ተመስርቶ እንደሆነ መናገራቸውን መንግስታዊው የቴሌቭዥን ጣቢያ ባሰራጨው መረጃ ላይ ጠቅሷል፡፡ ጥያቄውን ለማቅረብ በቤተመንግስት አካባቢ የተገኙት ወታደሮች በርከት ያሉ እና የጦር መሳሪያ የታጠቁ በመሆናቸው ግምትን መሰረት ያደረጉ እና ትክክል ያልሆኑ መረጃዎች በማህበራዊ ትስስር ገፆች መውጣታቸውም ተነግሯል፡፡
ንጋቱ ረጋሳ