• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የካቲት 5፣2011/ የከተሞች የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ አሁንም መስተካከል አልቻለም ተባለ

ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ደረቅ ቆሻሻን የሚያስወግድና መልሶ የሚጠቀም ከተማ እስካሁን የለም፡፡አሰራሩን ተግባራዊ ለማድረግ ግን ከተሞች የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሥርዓትን ዘርግተዋል፡፡

ከ50 ሺህ ህዝብ በላይ መኖሪያ የሆኑ ከተሞች ቆሻሻን በዓይነት በመለየት፣ በማሰባሰብና መልሶ በመጠቀም ያሉበት ደረጃም ተፈትሸዋል፡፡የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ እንደሚያሳየው ከተመዘኑ 34 ከተሞች 15 ከተሞች ብቻ 80 በመቶ ስራውን ተግባራዊ እያደረጉ ነው፡፡ ከተሞች አልሆን ያላቸውን ሳይንሳዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማገዝል የ9 ከተሞች መረጃ እየተሰበሰበ ነው ተብሏል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers