• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሚያዝያ 4፣2011/ በአዲስ አበባ የሰው ልጅ ሊመገበው የማይችለውንና ከጊዜ በኋላ ለከፋ የጤና ጉዳት የሚዳርገውን የእንጨት ፍቅፋቂ እና ሌሎች ምንነታቸው በውል የማይታወቁ ነገሮችን ምግቦች ውስጥ አደባልቆ የመሸጡ ነገር አሁንም የሚታይ ነው ተባለ

ምግብን ከባዕድ ነገሮች ጋር አደባልቆ መሸጥና ለተጠቃሚ የማቅረቡ ስራ ከአዲስ አበባ ይልቅ በክልሎች ላይ በብዛት እንደሚታይ ተነግሯል፡፡በአዲስ አበባ እንጀራ ጋግረን እናቀርባለን በሚሉ ተቋማት ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻም በማገዶ ነው የምንጠቀመው በማለት የእንጨት ፍቅፋቂ በመፍጨት ከጤፍ ጋር መቀላቀል፣ የደረቀ እንጀራ በድጋሚ በመፍጨት መጋገርና ማኛ ጤፍ በሚል ስያሜ ምንነቱ በላብራቶሪ ምርመራ ያልተረጋገጠ ነጭ ዱቄት በመቀላቀል የህብረተሰቡን ጤና በሚጎዳ መልኩ ህገ-ወጥ ስራዎች ሲሰሩ በጥቆማ ደርሼበታለሁ ሲል የኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ተናግሯል፡፡

መስሪያ ቤቱ ዛሬ በጽ/ቤቱ ጋዜጠኞችን ጠርቶ ሲናገር እንደሰማነው ምግብን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል የሚቀርቡ ተደጋጋሚ ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን በመከታተል ችግሩን የማጥፋት ዘመቻ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከእንጀራ በተጨማሪም እንደ ማርና ቅቤ ያሉት ላይ ከስኳር በተጨማሪ ምንነቱ የማይታወቅ ባዕድ ነገር በመቀላቀል በክልሎች ላይ የማጭበርበር ስራ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡እነዚህን አካላት በማስቀጣት ወደ ፍርድ ቤቶች ብሄድም ተገቢው የህግ ድጋፍ እየተሰጠኝ አይደለም ሲል መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡

ከህብረተሰብ ከሚደርሰው ጥቆማና መስሪያ ቤቱ በጀመረው ዘመቻ እስካሁንም በርካታ ተቋማት ላይ ፍተሻ በማድረግ አስገዳጅ የብቃት ማረጋገጫ እንዲያወጡ ተደርጓል ተብሏል፡፡ለምግብ ዝግጅት የሚደረግባቸው ቦታዎች ንፅህናቸው ያልተጠበቀ መሆኑ በተጨማሪ የሚታይ ችግር ሲሆን አሁንም እንደዚህ ዓይነት የሚያጠራጥሩ ነገሮችን በተመለከተ ማንኛውም ግለሰብ ጥቆማ ቢያደርሰኝ ሲል መስሪያ ቤቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ምህረት ሥዩም

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers