• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሚያዝያ 7፣2011/ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የወረርሽኝ በሽታዎች የሚታዩ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ የጤና ኢንስቲቲዩት ተናገረ

ኢንስቲቲዩቱ እንደሚለው፣ 1.3 ሚሊየን የሚሆኑ በሶማሌ፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ሕዝቦች ክልል የሚኖሩ ዜጎችን ያጠቃል ተብሎ የተገመተውን የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት ታቅዷል፡፡በአፋር ክልልም፣ አዳር ወረዳ፣ በዓል ውሃ ከተማ፣ ችኩንጉኒያ በተባለ የትኩሳት በሽታ እስከ ሚያዝያ 3/2011 ድረስ አንድ ሺ ሰላሳ ሰባት ሰዎች ተለክፈዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በአሶሳ ዞን ሀሻ ወረዳ፣ ባምዳ ቀበሌ፣ 103 ዜጎች በአባ ሰንጋ በሽታ ተለክፈው፣ 93 የሚሆኑት ህክምና ተደርጎላቸው ድነዋል ተብሏል፡፡በደቡብ ኦሞ ዞን ሃመርና በናፀማይ ወረዳዎች፣ ወፎች በብዛት በመሞታቸው ምክንያቱን የሚመረምር የባለሙያዎች ቡድን ወደ ስፍራው መላኩ ተጠቅሷል፡፡የጤና ኢንስቲቲዩት ዛሬ በላከልን መግለጫ እንደጠቆመው በሀገራችን የተለያዩ ክልሎች ለተፈናቀሉት ወገኖች፣ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን መቋቋም የሚያስችል ማዕከል ተደራጅቷል፡፡

እሸቴ አሰፋ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers