• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ግንቦት 14፣2011/ እስከ አራት መቶ ኮንቴነር የሚደርስ መድሃኒት በሞጆ ደረቅ ወደብ ተከማችቶ ይገኛል ተባለ

በመድሃኒት ግብይት ስርዓት ብዙ ተዋንያን በመኖራቸው እና የተቀላጠፈ ባለመሆኑ መድሃኒት ተግዝቶ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ በደረቅ ወደብ ለረዥም ጊዜ ተከማችቶ እንዲቆይ ሆኗል ተብሏል፡፡ይህንን ያለው የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ነው፡፡በሌሎች አገሮች የመድሃኒት ግዢ ከግምሩክ ሥርዓት አያልፍም የተባለ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን በጉምሩክ ሥርዓት እንዲያልፍ መደረጉና ንግድ ባንክም ቶሎ ክፍያ ስለማይፈፅም መድሃኒቱን አስገብቶ ለማሰራጨት ረዥም ጊዜ እየወሰደ ነው ተብሏል፡፡
መድሃኒቶች በሞጆ ደረቅ ወደብ በኮንቴነር ታሽገው እስከ 1 አመት ድረስ የሚቆዩበት ጊዜ አለ ያሉት በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጎይቶም ጊጋር ናቸው፡፡

ይህም የመድሃኒቶች የፈዋሽነት አቅም እንዲቀንስና የመጠቀሚያ ግዚያቸው ቶሎ እንዲደርስ ምክንያት ይሆናል ብለዋል፡፡ይህ ሁኔታ ተስተካክሎ መድሃኒቶች በፍጥነት ገብተው የሚሰራጩበት አሰራር እንዲፈጠር መንግስት ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ወሬውን የሰማነው የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ከኤጀንሲው የስራ ሀላፊዎች ጋር ሲወያይ ነው፡፡ባለፉት 9 ወራት 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ሕይወት አድንና መሰረታዊ መድሃኒቶች እንዲሁም የህክምና መሳሪያዎች ግዥ ተፈፅሟል፡፡

ይህም የእቅዱ 80 በመቶ ሲሆን አሁንም በህክምና ተቋማት ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት መኖሩን ባደረግሁት ምልከታ አረጋግጬአለሁ ብሏል ቋሚ ኮሚቴው፡፡ስለ ጉዳዩ ምላሽ የሰጡት ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ጎይቶም በበኩላቸው የመድሃኒት የግዢ ስርዓቱ አለመዘመንና አለመቀላጠፍ እንዲሁም ሰንሰለቱ አጭር አለመሆኑ አንዱ ምክንያት መሆኑን አስታውሰው የዶላር እጥረትም ከፍተኛ ፈተና እንደሆነ አስረድተዋል፡፡በሌላም በኩል የአገር ቤት መድሃኒት ፋብሪካዎች ማቅረብ ከሚጠበቅባቸው የመድሃኒት መጠን 33 በመቶ ብቻ እያቀረቡ መሆኑ ሌላው ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers