• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ግንቦት 14 201/ የምግብ መሰረቶች መመሳሰል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን ስጋት እየሆኑ ለመጡት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች አንደኛው መንስኤ ነው ተባለ

ተመሳሳይነት ያላቸውን የምግብ ዓይነቶች መመገብ ከመጠን በላይ ለሆነ የሰውነት ክብደትና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች እንደሚያጋልጥ የኢትዮጵያ ብዝሃ ሕይወት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፈለቀ ወልደየስ አለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን ዛሬ በሃገር ፍቅር ደረጃ አከባበር ላይ ተናግረዋል፡፡

ይህንን ችግር በመቅረፍ የምግብ መሰረቶችን ማስፋት ዋነኛው መፍትኤ ነው ብለዋል፡፡የምግብ መሰረቶች ተመሳሳይ መሆን በአለም አቀፍ ደረጃ 90 በመቶ የሚሆኑ የሰብል ዝርያዎችና 50 በመቶ የሚሆኑ የእንስሳት ዝርያዎች ከምድር እንዲጠፉ ምክንያት መሆኑንም ዶ/ር ፈለቀ ተናግረዋል፡፡18ኛ አለም አቀፍ የብዝሃ ሕይወት ቀን “ብዝሃ ሕይወታችን ምግባችንና ጤናችን” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው፡፡

ማህሌት ታደለ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers