• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ግንቦት 16፣2011/ የትራፊክ አደጋን ሳይጨምር ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ብቻ በተለያዩ አደጋዎች የ68 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለሸገር እንደተናገረው በተጠቀሰው ጊዜ 423 አደጋዎች ተከስተዋል፡፡ከመካከላቸው 299 ያህሉ የእሳት ቃጠሎ ሌሎቹ የጎርፍ፣ በግንባታ ስራ ላይ የሚያጋጥም አደጋና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡በአደጋዎቹ 68 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በ96 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል፡፡

በኮሚሽኑ የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ ለሸገር እንደተናገሩት ለሰዎች ሕይወት መጥፋት በአንደኛ ደረጃ የሚጠቀሰው ለካባ ተብለው ተቆፍረው ሳይደፈኑ የሚተዉ ጉድጓዶች ናቸው ብለዋል፡፡ በግንባታ ስራ ላይ የሚያጋጥም አደጋ በአዲስ አበባ በአደጋዎች ሕይወታቸው ለሚያልፍ ሰዎች በሁለተኛ ደረጃ በምክንያትነት ይጠቀሳል ብለዋል፡፡ በሶስተኛ ደረጃ የእሳት አደጋ የሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ ነው ተብሏል፡፡አቶ ንጋቱ እንዳሉት 90 በመቶዎቹ አደጋዎች በጥንቃቄ ጉድለት የደረሱና መከላከል የሚቻሉ ነበሩ ብለዋል፡፡

ትዕግስት ዘሪሁን

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers