• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሰኔ 3፣2011/ በኮልፌ ቀራንዮ በተለምዶ ቆሼ በመባል በሚታወቀው ስፍራ የመደርመስ አደጋ ደርሷል

ዛሬ ማለዳ ላይ በተደረመሰው ቆሻሻ ምን ያህል ሰዎች ህይወት እንዳለፈ አልታወቀም፡፡ከአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው እስካሁን የአንድ ሰው አስክሬን በፍለጋ ተገኝቷል፡፡የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደነገሩን ከሆነ ከአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን በተገኘ ስካቫተር ፍለጋው አሁንም ቀጥሏል፡፡

ቦታው ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ አደጋ ደርሶበት የበርካቶች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት አቶ ንጋቱ ማሞ አሁንም አደጋ ላይ ያሉ ወገኖች በቅርብ ርቀት እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ዛሬ በደረሰው የመደርመስ አደጋ ግን በላስቲክ ቤታቸውን ሰርተው በስፍራው የሚኖሩ ወገኖች ሕይወት ነበር አሳሳቢ የነበረው፣ እነሱ አደጋው በደረሰ ግዜ ከአካባቢው ሮጠው በማምለጣቸው በሕይወት አግኝተናቸዋል ብለዋል፡፡በፍለጋ የተገኘው አስክሬን የመንገደኛ ይሁን አይሁን ገና እየተመረመረ እንደሆነና ሌሎች በመደርመሱ አደጋ የተጎዱ ሰዎች ካሉ በሚል ፍለጋው እንደቀጠለ ከአቶ ንጋቱ ማሞ ሸገር ሰምቷል፡፡

አስፋው ስለሺ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers