• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ሰኔ 3፣2011/ በአዲስ አበባና ወደሌሎች የኮሌራ ወረርሽኝ ወደተከሰተባቸው አካባቢዎች የመድሃኒት አቅርቦት በአግባቡ እንዲደርስ እየተደረገ ነው ተባለ

የአተት/ኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በቂ የመድሃኒት ክምችት እንዳለው ተናግሮ ለህክምና የሚያስፈልጉ መድሃኒቶችንም እያሰራጨ መሆኑን ኤጀንሲው ተናግሯል፡፡እስካሁን ኮሌራን ለመከላከል በሽታው ይከሰትባቸዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ቦታዎችን በመለየት የኤጀንሲው ቅርንጫፎች በቂ የመድሃኒት አቅርቦት እንዲኖራቸው ተዘጋጅተዋል ሲሉ የኤጀንሲው የክምችትና ስርጭት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ ከፍተኛ የአቅርቦት ዘርፍ አማካሪ አቶ ዱፌራ ንግሳ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ኮሌራ ለተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚሆን በቂ የመድሃኒትና ለህክምና የሚያገለግሉ ግብዓቶች ክምችት አለ የተባለ ሲሆን ወረርሽኙ ወደተከሰተባቸው ቦታዎች የመድሃኒት እና ህክምና ግብዓት እያደረሱ ነው ተብሏል፡፡የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አዲስ አበባ ለሚገኙ ሰባት የጤና ተቋማት የህክምና ግብዓቶች እንዲደርስ በጠየቀው መሰረት መድሃኒቶች ለማድረስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ዱፌራ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሚሰጠው ጥቆማ መሰረትም የኮሌራ ወረርሽኝ ሊከሰት የሚችልባቸው አካባቢዎች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የኤጀንሲው ቅርንጫፎች በቂ የመድሃኒት እና የህክምና ግብዓት እንዲያገኙ ይደረጋል ተብሏል፡፡የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦ ኤጀንሲ ድንገተኛ ችግሮችን የሚከታተል ቡድን እንደተቋቋመ እና ወደ ኤጀንሲው ለሚመጡና እንደ ኮሌራ ላሉ ወረርሽኞች ሲከሰቱ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል፡፡የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚፈለጉ የመድሃኒት ግብዓቶች በጣም ተፈላጊ ከሆኑ መድሃኒቶች ውስጥ ሲሆኑ መድሃኒቶቹ በሀገር ውስጥ የመድሃኒት አምራቾች ጭምር የሚመረቱ በመሆናቸው የአቅርቦት ስጋት አያጋጥምም ሲል የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ተናግሯል፡፡

ምህረት ሥዩም

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers