• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

ነሐሴ 8፣ 2011/ በ2011 በጀት አመት ከቱሪዝም ዘርፍ ለማግኘት ታቅዶ የነበረውን ገቢ ማሳካት አለመቻሉን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተናገረ

ሚኒስቴሩ ከውጪ ጎብኚዎች 5.1 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ወጥኖ እንደነበር ከአመቱ የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡ መሰብሰብ የቻለውም 3.1 ቢሊዮን ወይንም የእቅዱን 62 በመቶ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ይህ ገቢ የተገኘው ከ849 ሺ በላይ የውጪ ጎብኚዎች ነው ተብሏል፡፡ ለቱሪስት መዳረሻ ልማት የሚሰጠው ትኩረት ማነስና የመረጃ ሥርዓት አለመዘመን ለእቅዱ አለመሳካት በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡የቱሪዝም ዘርፍን በበቂ አለማስተዋወቅም የጎብኚዎች ቁጥር እንዳያድግ አድርጎብኛል ሲል ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስቴር በአመታዊ ሪፖርቱ የአገር ውስጥ ጎብኚዎችንም አካትቷል፡፡በዚህም መሰረት በአመቱ ከ23 ሺህ 600 በላይ የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ነበሩ ተብሏል፡፡ከታቀደው ጋር ሲነፃፀር ደግሞ አፈፃፀሙ 64 በመቶ መሆኑን ከሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡በአገር ውስጥ ጎብኚዎች ብዛት አማራና ደቡብ ክልሎች እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ የቀዳሚውን ደረጃ መያዛቸውን ሚኒስቴሩ ተናግሯል፡፡

በየነ ወልዴ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers