ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች
ሕዳር 22፣ 2012/ በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በኩል ለመካከለኛ ኢንዱስትሪ ሙያተኞች ሲሰጥ የቆየው የክህሎት ስልጠና ብዙም አላገዛቸውም ተባለ
የመካከለኛ ኢንዱስትሪ ሙያተኞች የቴክኒክ ክህሎት ስልጠና በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በኩል ሲሰጣቸው ቆይቷል፡፡ይሁንና ስልጠናው ከመካከለኞቹ ይልቅ በጥቃቅን እና አነስተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የሚጠቅም ሆኖ እንደተገኘ የፌደራል አነስተኛ እና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ማስፋፊያ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ መለሠ ለሸገር ነግረዋል፡፡ለመካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ግን ስልጠናው ብዙም ጠቃሚ ሆኖ አልተገኘም ብለዋል፡፡
እነዚህኞቹ ኢንዱስትሪዎች ወሰብሰብ ያለ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ እና የተሻለ የቴክኒክ ብቃት የሚፈልጉ እንደሆኑ አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡በዚህ ምክንያት አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል ያሉት አቶ አሸናፊ በመፍትሄነት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተወሰኑ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ማዕከላት በመምረጥ አቅማቸውን አሳድጎ ስልጠናውን እንዲሰጡ ለማድረግ ታቅዷል ብለዋል፡፡የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለስልጣን፣ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲና የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት የተመረጡትን 21 ማዕከላት አቅም በጋራ ለማሳደግ ከሰሞኑ ስምምነት መፈራረማቸው ተነግሯል፡፡
ንጋቱ ረጋሳ