• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ አስመጪና ላኪዎች እንዲሁም የጉዞ ወኪል ቢሮዎች በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሣታፊዎች ናቸው

በኢትዮጵያ የሚገኙ አንዳንድ አስመጪና ላኪዎች እንዲሁም የጉዞ ወኪል ቢሮዎች በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተግባር ተሣታፊዎች ናቸው ተባለ… የተሳሳተ ሰነድ በማዘጋጀት፣ ያልተጨበጠ ተስፋ በመስጠት በሀገር ውስጥ ደላሎች ዜጐች ወደማያውቁት እና ወዳልተመቻቸላቸው ሀገር እየተሰደዱ ለችግርና ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በአገር ውስጥ በህገ-ወጥ ሰዎች ዝውውር ወይም /ሂውማን ትራፊኪንግ/ ከሚያጧጡፉ መካከልም አስጐብኚ ድርጅቶችና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በተለያዩ ምክንያትና መንገድ ቁጥራቸው ይህን ያህል ነው ተብሎ የማይታወቅ ሰዎች ወደተለያዩ የአረብ ሀገራትና የዓለም ጥግ እንደሚሰደዱ ተነግሯል፡፡

ወሬውን የሰማነው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ከሚመለከታቸው ጋር በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳይ ላይ በመከሩበት ጊዜ ነው፡፡ በቦሌ አየር ማረፊያ በኩል፣ በሃጂና ዑምራ የጉዞ ቪዛ፣ በጉብኝት ቪዛ፣ በነፃ ቪዛ፣ በንግድና ትራንዚት ቪዛ፣ በሥራና በሌሎችም ቪዛ ዓይነቶች የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑትን ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ በምክክሩ ላይ የቀረበ ጥናት ተናግሯል፡፡ በየሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ ብዙ ኢትዮጵያውን ወደ ውጪ አገር ለመሄድ ሲወስኑ በደላሎች እጅ ላይ እየወደቁ ለተለያዩ እንግልትና መብት ጥሰት እየተዳረጉ ነው ብለዋል፡፡ ወደ ውጪ አገር ሄደው ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ ክብራቸው፣ ደህንነታቸው፣ የስነ-ልቦና እና አካላዊ ጥቃት ሳይደርስባቸው በህግ ማዕቀፍ የተጠበቀ እንዲሆን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የውጭ አገር የሥራ ስምሪትን ለማጠናከርና የዜጐችን ደህንነት ለማረጋገጥ ከዚህ ቀደም የወጣው አዋጅ ደንብና መመሪያም እየተዘጋጀለት ነው ተብሏል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ተቋርጦ የነበረውን የውጭ አገር ሥራ ስምሪት እንዲቀጥል  ዝግጅቶቼን እያጠናቀቅኩ ነው ሲል ተናግሯል፡፡

በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የቀረበው ጥናት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በዓለም ላይ በፍጥነት እያደገ ያለ ዘመናዊ የሰዎች ባርነት መሆኑን ጠቁሟል፡፡ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ከአደንዛዥ እፅና ከጦር መሣሪያ ንግድ ጋር ሲነፃፀር በጣም አትራፊ ኪሣራም የሌለው መሆኑን የጥናት ወረቀቱ ተናግሯል፡፡ በዓለም በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ 245 ሚሊዮን ሰዎች የጉልበት ብዝበዛ እየደረሰባቸው መሆኑ ተነግሯል በጥናቱ፡፡ በየዓመቱም አዳዲስ 1.2 ሚሊየን ሰዎች የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ተህቦ ንጉሴ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers