• United Bank S.C.

    ሕብረት ባንክ አ.ማ.

  • Slider Two

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

  • Sldier Three

    የምስል ተጓዳኝ መልዕክት

ሸገር ወሬዎች እና ልዩ ወሬዎች

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣የዜጐችን ደህንነት አስጠብቄ ሥምሪቱን ለመጀመር የአቅሜን እየጣርኩ ነው

የውጪ ሀገር የሥራ ስምሪትን መልክ ለማስያዝና የዜጐችን ደህንነት አስጠብቄ ሥምሪቱን ለመጀመር የአቅሜን እየጣርኩ ነው ያለው የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው… የሥራ ፈላጊዎችን ደህንነት የሚያስጠብቅ አዋጅም መውጣቱን ተከትሎ ለአፈፃፀሙ እንዲረዳ ደንብና መመሪያ እየተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡ በቅርቡም ተቋርጦ የነበረው የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ህግና ደንቡን ጠብቆ የዜጐች መብት ሳይጣስ እንደሚጀምር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳመነ ዳሮታ ተናግረዋል፡፡

በውጭ አገር ሄደው መሥራት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ህጉን ተከትለው ጥቅማቸውና ደህንነታቸውን እንዲጠበቅላቸው ከተለያዩ የአረብ አገሮች ጋር ስምምነቶችን እንደተፈራረመም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡ እስካሁንም ከኳታር፣ ኩዌትና ጆርዳን አገሮች ጋር በደህንነት ዙሪያ እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ጉዳይ ተፈራርሜያለው ብሏል መሥሪያ ቤቱ፡፡

ከሌሎች ተቀባይ አገሮች ከነዱባይ እና ሳዑዲ አረቢያ ጋርም ስምምነቱን ለመፈራረም መንገዶቼን እያጠናቀቅኩ ነው ብሏል፡፡ እግረ መንገዴንም በውጭ አገር ሥራ ለመሰማራት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን የሚደርሱበትን አገር ባህል እንዲያውቁ በፕሮጀክቴ አካትቼዋለው ማለቱን ሰምተናለ፡፡

 

ጐን ለጐንም እንጀራ ለሚያገኙበት የሥራ ዘርፍም በቂ ሥልጠና ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያውያንን መብት፣ ክብር፣ ጥቅም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ሲባል ስምምነት ወዳልተፈረመባቸው አገራት ኢትዮጵያውያን ለሥራ እንደማይሄዱ እወቁት ብሏል ሚኒስቴር መሥራያ ቤቱ፡፡

በተለያየ ጊዜም ህገ-ወጥ የውጭ አገር ላኪዎች ህጋዊ የሥራ ስምሪቱ ጀምሯል እያሉ ዜጐችን እያታለሉ ነው የተባለ ሲሆን ህጋዊ የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት ሲጀምር በይፋ እወቁት ብዬ እናገራለሁ ሲል የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ተናግሯል፡፡

ተህቦ ንጉሤ

በማኅበረ ሰብ ገጾች ያጋሩ

Submit to FacebookSubmit to Google PlusSubmit to TwitterSubmit to LinkedIn
Sheger 102.1 AudioNow Numbers